ከቆምንበት ቦታ ፥ ቆሜ አንቺን አስባለው፤
ቁጭ ብለን ካወጋንበት ፥ ቁጭ ብዬ እተክዛለው፤
ጨዋታ እና ሳቅሽን አስታውሼ ፥ እህ እላለው፤
እተክዛለው [አስባለው።]፪*
እንግዲያው አንቺም ፥ ከተለየሽ ከራቅሽኝ፤
አስታውሽኝ፤
በፍቅር ከልብ ቆንጂት ከሆድሽ ውስጥ ፥ አታውጪኝ፤
እንዳልረሳሁሽ አደራ አንቺም ፥ አትርሽኝ፤
አስታውሽኝ፤
ፍቅሬ [አስቢኝ]፪* አስታውሽኝ።
እንደምነሽ ፥ ኸረ እንዴት ነሽ፤
[እንደምነሽ]፪*
ከተሰናበትሽኝ ፥ ከሄድሽ እኮ ቆየሽ፤
እጠብቅሻለው ፥ መች ትመለሻለሽ።
ለብቸኝነቴ ለብቸኝነቴ ፥ ለአዲሱ እንግዳዬ፤
ትካዜ ብቻ ነው ፥ መስተናገጃዬ፤
እንደምነሽ ብዬ ፥ ሁሌ አስብሻለው፤
[በቃልኪዳን ፅናት ፥ እጠብቅሻለው።]፫*
አልዋሽም ፥ ስበላ አሰብኩሽ፤
አልዋሽም ፥ ስጠጣ አሰብኩሽ፤
አልዋሽም ፥ ሲመሽ አሰብኩሽ፤
ሲነጋ ፥ አሰብኩሽ፤
አልዋሽም ፥ እኔ አልዋሽም፤
የእምነት የእውነት ቃሌን ፥ ክጄ አላበላሽም።
ከቆምንበት ቦታ ቆሜ አንቺን ፥ አስባለው፤👫
ቁጭ ብለን ካወጋንበት ቁጭ ብዬ ፥ እተክዛለው፤🙇♂
ጨዋታ እና ሳቅሽን አስታውሼ ፥ እህ እላለው፤🤦♂
እተክዛለው ፥ አስባለው [አስባለው።]፪*🙇
እንደምነሽ ፥ ኸረ እንዴት ነሽ፤
[እንደምነሽ]፪*
ከተሰናበትሽኝ ፥ ከሄድሽ እኮ ቆየሽ፤
እጠብቅሻለው ፥ መች ትመለሻለሽ።
[ናፍቆትሽ በአይኔ ላይ]፪* ፥ ከተመላለሰ፤
የፍቅር እመቤቴን ፥ አንቺን ካስታወሰ፤
እንደምነሽ ብዬ ፥ አስታውስሻለው፤
[ጤና ሰላምሽን ፥ እመኝልሻለው።]፫*
አልዋሽም ፥ ስበላ አሰብኩሽ፤
አልዋሽም ፥ ስጠጣ አሰብኩሽ፤
አልዋሽም ፥ ሲመሽ አሰብኩሽ፤
ሲነጋ ፥ አሰብኩሽ፤
[አልዋሽም ፥ እኔ አልዋሽም፤
የእምነት የእውነት ቃሌን ፥ ክጄ አለሰበላሽም።
@Edom_G_Flash