World Philosophy & Secret Knowledge


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


_ ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች እንኳን ወደ ሚሥጥረ ኢትዮጵያ ሀገራዊ ቻናል በደህና መጣችሁ እያልኩኝ በዚህ ቻናል ውስጥ በይበልጥ
+ ሀገራዊ ጉዳዮች
+ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች
+ መንፈሳዊ ጉዳዮች
+ ታሪካዊ ጉዳዮች
+ እንዲሁም የተለያዩ አሳታፊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ቻናል ሲሆን እናንተም የቻናላችን ቤተሰብ በመሆን ለሌሎችም በማጋራት ኢትዮጵያዊነትን እናስፋፋ እላለሁ 🙏 አመሰግናለሁ 🙏

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


አንድ Group ለይ ነው አሉ

- እውነት የሆነው ነገር ምንድነው¿

- የመጨረሻ ነገር!

- Define

-ሁሉም ነገሮች በጅምራቸዉ ፍፁም አይደሉም ወይም ታዐማኒነት የላቸዉም የመጨረሻ ዉጤታቸዉ መጨረሻ ላይ የሚይዙት ቅርፅ ነዉ እዉነት!

ለዛም ነዉ እዉነትን ከሶክራተስ እስከ ፕሌቶ ከፕሌቶ እስከ አርስቶትል:ዲዮጋን:ኒቸ:ማርከስ:ኦሾ  ወዘተ ጥያቄ የሆነባቸዉ የራሳቸዉን ግንዛቤ የሰጡት:: የሰጡበት ምክንያትም በራሳቸዉ እይታ ጥረዉ ጥረዉ የመጨረሻ ግባቸዉ ነዉ እዉነት ብለዉ ያቀረቡት    

ለኔም እዉነት የሆነዉ ነገር የመጨረሻዉ ነገር ነዉ!!!!

- እውነት ላንተ የመጨረሻ ነገር ከሆነ ያንተ መጨረሻ ሞት መሆኑ ነው..

- በዚህ ምድር እንደሞት ፍፁም እዉነት የለም!!!!!

- ምንም ሊገባኝ አልቻለም እየሞትክ ነው ወይንስ ሞተኣልም ስለሞት ያወራኸው¿

- አንድ ቀን ባደርኩ ቁጥር ለሞት እየቀረብኩ እንደሆነ ስለሚሰማኝ!!!!

- ይህ በቂ መልስ አይደለም የምታወራውን ታምነዋለ?

ጥያቄ ነው

- አዎ

- አመሰግናለሁ ጥያቄ ከሌለ ሰላም እደር

- አጥጋቢ መልስ አልሰጠዉህም እንዴ!!

- Word chess ነው እናም ordinary ቃል ነው

እናም በስተ መጨረሻ ሀሳባቸውን ሳይቋጩ ውይይታቸው አቆመ


እንቅልፍ ሞትን ልምምድ ነዉ ብዬ አምናለሁ አንድ ሰዉ እንቅልፉን ሲወስደዉ ይሙት ይኑር አያዉቅም እንኳን ሌላ ህልም እያየ ቢሆን ራሱ በህይወት መኖሩን ማወቅ አይችልም ምክንያቱም ሚያየዉ ነገር አይኑን ገልጦ አይደለም ህልሙን ሚያየዉ ። እንቅልፍ የህልም አፓራንት ነዉ! የኔ እምነት ነዉ!!!!!!

ደህና እደሩ


ወ ረ ኛ ሆነ እኮ አይደለም ሁሉም ሰው ወረኛ ነው! አንተ ግን የት . . . ቦታ ምን ሰዓት. . . ማውራት ያለብህን አለማወቅህ ነው።


[አራት ዓይነት እብደት ]

.

ብቸኝነት ብርዱ ገላህን ቀዝቅዞ
ከሰው መሀል አንተን ለብቻህ ሰቅዞ
መጠየቅ ስትጀምር ...
ለምን!...እንዴት?...ስትል?
ጥያቄህ በራሱ እብደት ነው የሚባል
ኡፍፍፍ...
አቋመ ቢስ መሐል ለብቻችን ነቅተን
አቦ ተሰቃየን!
.

መጠየቅ ሰልችቶህ ከሕዝቦች ስትርቅ
በራስህ ዓለም ላይ ህሊናህ ሲራቀቅ
አፍህ ዝም ባለ
እብድ መባል አለ።
ኤጭ!...
አቋመ ቢስ መሐል ለብቻችን ነቅተን
አቦ ተሰቃየን!


የሕዝብ ሁሉ ሀሳብ የእብደት ሲመስልህ
ያንተ አሳብ የእውነት....
እውነት እንደሆነ ውስጥህን ሲሰማህ
እብዱ ትባላለህ።
ኤዲያ!...
አውቆ የሚተኛ ሕዝብ መሀል ነቅተን፣
አቦ ተሰቃየን!


ዓለሙም እብድ ነው!
ግና ያለም እብደት ካንተ የሚለየው
አንተ የምታብደው ለዓለም ስትል ነው
ዓለሙ ያበደው አንተን ሊያሳብድ ነው።
ወገን ተሰቃየን!
አውቆ በተኛ አቋመ ቢስ መሐል...
ለብቻችን ነቅተን
አወይ ተሰቃየን!!

______

ኤፍሬም ሥዩም ( ኑ ግድግዳ እናፍርስ!)


የትዝታ ክምር
ዴቪድ ሂውም

ከፊት ለፊትህ ባዶ የቲያትር መድረክ አለ፤ አሮጌ መጋረጃዎች ያሉት፤ መሬቱ ለብዙ ጊዜያት ባለመጠረጉም  አቧራ ለብሷል። ድንገትም ከጀርባ ወደ ቴያትር መድረኩ አንድ ሰው መጣ፡፡ እናትህ ነች፤ በሰባት አመትህ ሳለ ተረት ታነብልህ እንደነበረው አሁንም እያነበበች ነው፡፡ ድንገትም እናትህ ከመድረኩ ተሰወረች ፤ ሌላም ሰው መጣ። አንተን ይመስላል ፤ ይህንንም መጽሐፍ እያነበበ ነው፡፡ መመሳሰላችሁ ከፊትህ ያለን መስታወት የማየት ያህል ነው፡፡ ድንገት መድረኩን ብርሃን ወረሰው፤ ተመልሶም ባዶ ሆነ...

ዴቪድ ሂውም የሰው ማንነቱ ትዝታዎቹ ናቸው ይለናል። የምታስታውሳቸው ሃሳቦች፣ እናትህ የመከረችህ ምክሮች፣ ከጓደኞችህ ጋር የነበረህ ጨዋታ.... በሕይወትህ ያሳለፍከው ነገር ሁሉ አሁን ላይ ያለህን ማንነት ይቀርጸዋል። ወደ ምድር ስትመጣም ልክ እንደ ባዶ የቲያትር መድረክ ነበርክ፣ አሁን ግን በብዙ ትዝታዎች ተሞልተሃል።

“እኔ ማን ነኝ ለሚለው ጥያቄህም መልስ የሚሆነው ትዝታዎችህ ነህ ይሆናል። ልክ በድስት ውስጥ ያለ እና ሲንተከተክ እንደሚናወጥ ወጥ ነህ፡፡ በአእምሮ ውስጥ ያሉ ትውስታዎች እና ልማዶች ተደባልቀው ልክ እንደወጡ ሁሉ የሆነ ማንነት ይሰጡሃል። ይህ ወጥ በመጀመሪያ ሽንኩርት፣ ዘይት እና በርበሬ ብቻ ነበር... እየቆየ ሲሄድ ግን አይነቱ ይቀየራል፡፡ ምናልባትም መጨረሻው ስጋ ወጥ ወይም ሽሮ ወጥ መሆን ይሆናል፡፡ ሆኖም እያንዳንዱ ወደ ድስቱ የገባ ግብዓት የመጨረሻውን የወጥ ማንነት ይሰጠናል። ያንተም ማንነት እንደዚያው ነው፡፡ ቁጡነትህ፣ እርጋታህ፣ ፍቅርህ፣ ጥላቻህ፣ ችኮላህ፣ ትዕግስትህ፣ መወላወልህ፣ ቆራጥነትህ... ሁሉም ወደ አእምሮህ ከገቡ እና ካሳለፍካቸው ሁነቶች ይመነጫሉ፡

ለሂውም ሰዎች ሁሉ አንድ አይደሉም፡፡ ወጥ ሁሉ የተለያየ ቃና እንዳለው፣ ሁሉ ሰው የመጣበት መንገድ ይለያያል እና ፍጹም የተለያየ ማንነት ይኖረናል፡፡ ከሌላው ጋር አንድ የሚያደርገንም ነገር የለም፡፡ አንተ እራስህ የትውልድ ቦታህን ወይም የተወለድክበትን ጊዜ ቀይረህ ብትወለድ ፍጹም የተለየ ማንነትን ትይዛለህ፡፡ አዲስ በሌላ ጊዜ ወይም ቦታ ላይ የሚወለደው “አንተ” እና አሁን ላይ ያለኸው አንተ አንድ አይነት ሰው አትሆኑም።

እናም ሂውም አንተ የሃሳቦችህ እና የትዝታዎችህ ክምር ነህ ይልሃል። የእኔ ማንነትም የቱ ነው ካልክ፣ ወደ ባዶ የቲያትር መድረክ አፍጥጥ። አእምሮህ በምድር ላይ ያሳለፍከውን ሕይወት በዳግም ምልሰት ያስቃኝሃል፡፡ በአእምሮህ ከተቀረጹ ሃሳቦች ውጪ ማንነት የለህም። ማንነትህን እነርሱ ብቻ ይወስኑልሃል።


“A fool is known by his speech, and a wise man by silence.”

`` ሞኝ በንግግሩ ጠቢብ ደግሞ በዝምታው ይታወቃል! ``


፦ Pythagoras


ሳይንስ ፤ ፍልስፍናና ስነ-ፅሁፍ

በሕዋ (Universe) ውስጥ አእምሮ በዕውቀትና ክህሎቱ ሰፍሮ የማይጨርሰውና መርምሮ የማይደርሰው ብዙ ተአምር አለ። እንደ ግል እይታዬ ይህ ያልተደረሰበት ተአምር ለሳይንስ፤ ለፍልስፍናና ለሥነ-ጽሑፍ አለፍ ሲልም ለእምነት ...የተተወ የተንጣለለ የኀሰሳ ሜዳና የቀና ዕድል ነው። እምነት ያው “ማመን” ስለሆነና አንጻራዊነት ስለሚጫነው እዚሁ ጋር እንተወው

ሳይንስ ለመከራው ማብቂያ ፣ለፍዳው መገላገያ የለውም። በቀን ያስጨንቃል፣ በሌት ያባንናል። ዓመታት ፈጅቶ የተደረሰበት መደምደሚያ እንኳ በቋፍ እንደተቀመጠ ብርጭቆ ነው። በሌላ መደምደሚያ “ተሳስተሃል” ይባላል — Disprove ይደረጋል። የአመታት እውነት በአንድ ሌት ውሸት ሆኖ ሊያድር ይችላል። ሳይንስ ነጻነት አይሰጥም። ሳይንስ የምርምር ንድፍና ሰርቶ ማሳያ ከሚሆኑ ፈጠራዎች ባለፈ “ቢሆንስ?” ለተባለና ላልተጨበጠ ምናብ የተተወ እንግዳ መቀበያ የለውም በእርግጥ አስተውሎት (observation) በሳይንስ ቤት ያለው ቦታ የማይናቅ ነው።

ጠልለው የተቀመጡ፤ ተመርምረው የተሰደሩ  ውጤቶቹን ባየሁ ቁጥር ለተመራማሪዎቹ አዝንላቸዋለሁ። ወዲህም የሰው አእምሮ አጀብ እላለሁ። ከሳይንስ ሁሉ ጊዜና ቦታን ጠቅልሎ የያዘው ሕዋ ላይ የሚደረግ ምርምር ደግሞ በእጅጉ ያባብለኛል። በአንድ ጫፍ የሰው ልጅ አፉን በመዳፍ ሸፍኖ ለሐሜት በሚተጋበት ምድር ላይ፤ በሌላው ጫፍ ሮኬት እንደፈረስ ጠምዶ ተመርምረው የተሰደሩ ጨረቃን ይረግጣል።

ፍልስፍና በመጠኑ መለስ ያለ የሕይወት ምርመራና፤ የትርጉም ኀሰሳ ነው። ፍልስፍና አንዳንድ የሀገሬ ሰው እንደሚያስበው የብሶተኛ ሮሮ ወይም ጥራዝ- ነጠቅ ምክንያታዊነት አይደለም። ምድር የምትመራው በሳይንስ ሳይሆን በፍልስፍና ነው። ርዕዮተ-ዓለሞች የሚረቅቁት፤ የመንግሥት ስርዓቶች የሚዋቀሩት፣ ግለሰባዊው ሰው የኑሮ ምርጫውን የሚዘረጋው ወደደም አልወደደም በኖረበት ማኀበራዊ እሴት ለስልሶና፤ በአፈንጋጭ የሕይወት መጠይቆቹ ሻክሮ ነው።

ሳይንስ ለጥቂቶች ብቻ የተሰጠ ቢሆንም ለፍልስፍና ወድቆ ይገዛል። ረባም አልረባም የጊዜው አየር ላይ ከሚነፍሰው ፕሮፖጋንዳ ሥር ያሸበሽባል። ዲሞክራት ነን የሚሉ ሀገራት ሕዝቡን ያለ እውቅናው ጠምዝዞ ለመቆጣጠር፤ መውጪያና መግቢያውን ለመለየት፤ ተፈጥሮን በሰው ልጅ ጡንቻ ሥር ለማሰገድ ያውሉታል። ከሞኝ ሀገራት ደጅ ሞፈር ለመቁረጥ፣ ጥሬ ዕቃ ለመበዝበዝ፣ በምርትና አምራችነት ስም ራሳቸውን ለማበልጸግ፣ እንዲሁም ለሰው ተስማሚ የሆኑ አማራጭ ዓለማትን ለመፈለግ ያውሉታል።

አምባገነን ሀገራት ለጦር ኃይላቸው መዘመን፣ ኒውክለር ለማብላላት፣ ጸጥ ረጭ አድርገው ለመግዛት ከዲስኩርና ከሌሎች ስልታዊ ማደንዘዣዎች ጎን ለጎን ሳይንስን ይጠቀሙታል። ቀን በቀንም ቴክኖሎጂው እየዘመነ ኑሮ እየቀለለ እንዳለ ሁሉ፣ ለመጠፋፋትም እንዲሁ አቋራጭ ስልቶች እዚህም እዚያም ብቅ ማለት ጀምረዋል።

ሦስተኛውና “ያ” ክፍት ቦታ የተተወለት ዘርፍ ሥነ-ጽሑፍ ነው። በተለይ ልብ-ወለድ (Fictional) ሥነ-ጽሑፍ ከሁለቱ በተሻለ መልኩ ዕድሉ የቀና ነው። ለምን? ሥነ-ጽሑፍ ምናብን አቅፎ ይቀበላል። እውነትና ውሸትን ቢቀይጥ ከልካይ የለውም። እንዲሁም ነጻነት ከሌለው ሳይንስና፤ ደረቅ ከሆነው የትርጉም ሐቲት አውጥቶ ቢፈለጉ በማይገኙ ሰዎችና እንዳሻው በፈጠረው ዓለም ውስጥ
ሕይወትን ይፈትሻል።

ከሀገር ያጣ ሞት
ድርሰት - ሄኖክ በቀለ


“ሀገር ያጣ ሞት” ራሱ እንደሚhው “ከቅኝት ትዝታ፣ ከስሜትም ኀዘን” የሚገንንበት ፤ ሀዘኑ አንባቢን የሚወርስ፣ እንደ ዐፈር ግድግዳ የሚንድ፤ የሚያፈራርስ፤ መሪር ሂዩመሩ hሣቅ የተገለጠ ጥርስ በመሸማቀቅ አግጥጦ የሚያስቀር፣ ለፈገግታ የተዛና የጉንጭ ቆዳን በኀፍረት የሚሸበሽብ፤ የገዛ ስጋ ወደሙን ከአንባቢ የሚያዋሕድ ኃያል ድርሰት ነው፡፡"

@Zephilosophy




እብድ ነህ " ለሚሉኝ አዎ ሆኖ መልሴ
  ግራ ቢገባቸው ለእብደት መኮፈሴ
ከንፈር መጠው ሄዱ ከንፈር ስላቅ ከንፈር
ያሳፍራል እንዲህ በእበደት አለማፈር ?

አዎ እኔ እብድ ነኝ
ገደብ ያልከለለኝ
ድንበር ያልወሰነኝ
መንገድ ዳር የጣሉት የፌስታል ጌጠኛ
አዎ እኔ እብድ ነኝ...
ከረሳኝ የሰው ዘር  የማይከዳን ውሻ አቅፌ ምተኛ።


p h o t o : Diogenes 📷


አብዛኛው ሰዎች ባለመረዳታቸው በድጋሚ የተለቀቀ



ምዕራባውያን ስለ ስነ-ፍጥረት ፍልስፍናቸውን እንዲህ ብለውን ነበረ“ God created man and man created Satan ”

`` እግዚአብሔር ሰውን ፈጠረ ሰው ደግሞ ሰይጣንን ፈጠረ ``

ታድያ ምን ማለታቸው ነው ስንል Satan የምንለው ነገር የሀሳባችን ውጤት ነው ወደሚል ጥያቄ ያንደረድረናል. . . ይህ ለሀይማኖተኞች ትልቅ ቅራኔን ያስነሳል፤ እለት እለት `` እክህደከ ሰይጣን `` ብለው መሃላቸውን ያሰሩ እነዚህ ሃይማኖተኞች ሰይጣን የለም ቢባሉ.. ምንድንር ነው መልሳቸው ?


እሩቅ መራመድ በመተው ከሀገራችን ሊቆች አንዱና ዋነኛውን በዚህ ስነ-ፍጥረት ላይ እንመልከት ምን አለ መሰላችሁ ..

`` የአምን ወይገኒ
ኵሉ ዓለም በዘፈጠረ ለሊሁ፣
ብዙኃን እንዘ ይገንዩ ይሰግዱ ቅድሜሁ፣
ለነጽሮ ዝኒ ከመ እሥራኤል ይፍርሁ፣
ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ፣
ወ ፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ። ``

( ታላቁ  የቅኔ  ሊቅ  እና  ፈላስፋ ተዋነይ ዘጉንጂ)

ይህን ምን ትሉታላችሁ ትልቅ ድፍረት ወይንስ ትልቅ ጥበብ ?


እኩይ ነኝ ከፊል ማንነቴን ያጣው። ፈቃደ-ሰብነቴን ለእርካታዬ የገበርኩ፤ አቦል ደንግባቴን በአጽናፍ እፆታ ላይ ያፈሰስኩ... ወጣት ጸደይነቴ በምድር ብራ የሆነ፤ እኩይ ነኝ የተሰጠኝ ሲሳይ ለማንም የተበነ!።

ም ን ድ ነ ኝ ¿
በሰማይ የምንቀዋለል ከርታታ ኮበብ ምሳሌ፤ በራሴ ጅራፍ 'ራሴን የምገርፍ የማልማር ከትናንት ቁስሌ። አስመሳይነት የዋጠኝ ለመኖር ብዬ ልክ እንደተርታ፤ ሰውን ሳይሆን እኔ እኔን በመርሳት ደዌ የተመታ . . .

ልቤ የሚያደላ ወደቆሰሉ ወደ ወደተወጉ፤
አንዳች የሌለኝ ብቻን የሆንኹህ መፃጉ...

እ ኩ ይ : ነ ኝ!


....አዳም የበሰበሰ በለስ ውጦ ከዚህች ኤደን ነው ያወጣን? ወደ ሞት ወደ ጦርነት ወደ ደም ወደ አርበኝነት ወደ ባንዳነት? 😕😕……. ያቺ ሴት ያቺ ቂልና ቀልቃላ ሴት፡፡ ያቺ ሄዋን የምትባል ሀጠራው!......

ህማማትና በገና /Book Excerpt


#አዳም_ረታ


እ ን ዲ ሁ እ ን ደ ዘ በ ት ጊዜ ሲፈራረቅ የቀዳውት ቡና አቦልነቱን ሲሰክን ይታየኛል። ፍሬ ሊያፈሩ ያሉ ዛፎች ያለወቅታቸው ሲረግፉ የሚወርደው ደረቅ ቅርፊት 🍂 ከእድሜዬ እየጨመርኩ ሳይሆን እየቀነስኩ እንደሆነ በግልፅ ብሩሽ እኔነቴን ይስላሉ። ሲኦልነት አንዱ የማረፍ መንገድ ነው። እኔ አልጸደኩም አልረከስኩም፤ ፍጹም ፅዳቴ ላይ ቆሽሻለው፣ በዝምታዬ ውስጥ ብዙ ጫጫታዎች አስደተናግጃለው፤ ከራሴጋር አወራለው ከራሴጋር አይደለውም፣ ብቻ የእግዜር ሴጣን. . .


2 0 1 1 ዓ.ም . .ሻማና:በገና /የተወሰደ ✍🏽


አህያ ሁን አለኝ ፡ አህያ ሆንኩለት
አሰሱን ገሰሱን ፡ እንድሽከምለት።
መጋዣ ሁን ብሎ ፡ ፈረሱ አደረገኝ
በየዳገቱ ላይ ፡ ወስዶ እሚጋልበኝ።
እንጃ ግን ሰሞኑን ፡ በግ ነህ ተብያለሁ
ሊያርደኝ ነው መሰለኝ ፡ አሁን ፈርቻለሁ!።


“Coins always make sound but currency notes are always silent, so when ever your value increases keep yourself calm and silent.”


፦ William Shakespeare


[R e p o s t ]


የቁጣ ስሜት!!!

ከቁጣ ጋር የተያያዘ ችግር የነበረበት ጓደኛ ነበረኝ። አንድ ቀን፦" የቁጣ ስሜት ከቁጥጥሬ ውጪ ሆኖ እየረበሸኝ ነው። ምንም ነገር ሳላደርግ ልቆጣጠረው የሚያስችለኝ መንገድ አሳየኝ። ከአቅሜ በላይ ስለሆነ የሆነ ነገር ማድረግ እችላለሁ ብየ አላስብም። በራሴ ጥረት ከዚህ ችግር እላቀቃለሁ ብየ አላስብም።" በማለት ችግሩን ነገረኝ።
...
"አሁን እየተቆጣሁ ነው።" የሚል ፅሁፍ የሰፈረበት ወረቀት ሰጠሁትና "ይህን ወረቀት ኪስህ ውስጥ ያዘውና ቁጣ በተሰማህ ቁጥር አውጥተህ በማንበብ መልሰህ ወደ ኪስህ ክተተው። ቢያንስ ይሄን ማድረግ ትችላለህ።" አልኩት። እሱም እንደሚሞክር ነግሮኝ ተለያየን።
...
ከሁለት ወይም ሶስት ወራት በኋላ ተገናኘንና፦ "ምን ተከሰተ?" ብዬ ጠየኩት። እሱም እንዲህ አለኝ "በጣም ተገርሜያለሁ። ይህ ወረቀት ልክ እንደ ማንትራ ነው የሰራው። ቁጣ በተሰማኝ ቁጥር ከኪሴ አወጣዋለሁ ያኔ እግርና እጄ ሀይል ያጣሉ። ልክ እጄን ወደ ኪሴ ስከት የቁጣ ስሜት እየተሰማኝ መሆኑን እገነዘብና መለስ እላለሁ፣ ተቆጣጥሮኝ የነበረው ቁጣም ይጠፋል። እጄ ወደ ኪሴ ሲሄድ ዘና እላለሁ እናም ወረቀቱን ማንበብ ሁላ አያስፈልገኝም።" አለኝ ከዛም "ይህ ወረቀት የዚህ አይነት ውጤት እንዴት ሊኖረው ቻለ? ምክንያቱ ምንድን ነው?" ሲል ጠየቀኝ።
...
እኔም "ምንም ሚስጥር የለውም በጣም ቀላል ነው። ንቁ ባልሆንክበት ጊዜያቶች ሁሉ የአይምሮ ሁከቶች ይቆጣጠሩሀል። ንቁ በሆንክ ቅፅበት ግን ሁሉም ነገር ይጠፋል።" አልኩት።

   
፦Osho


“ Discover yourself, otherwise you have to depend on other people’s opinions who don’t know themselves.”

`` እራስህን አግኝ፤ አለበለዚያ እራሳቸውን በማያውቁት በሌሎች ሰዎች አስተያየት ላይ ጥገኛ ትሆናለ!። ``


፦ O s h o


ድንገት ጭር ያለ ቦታ ሳለሁ ብዙ ምልክት ሳያሳይ ወይ እኔ ሳላስተውለው  አላቅም ብቻ ዶፍ ዝናቡን ለቀቀው ። የቱም ቦታ የታየኝ  መጠለያ አልነበረም ።

በቅርቡ ወለም ያለኝ እግሬ መሮጥ ስላላስቻለኝ በተቻለኝ መጠን ለመራመድ ሞከርኩ

በቲሸርት መሆኔን ፣ መራመድ አለመቻሌን ከምንም ሳይቆጥር ዝናቡ  ያለርህራዬ ቀጠቀጠኝ

አለቀስኩ ......።

ደብሮኝ ነበራ!!!

አጥንትን የሚፍቅ ድብርት ውስጥ ነበርኳ ፣ ማንም ሊያድነኝ ከማይችል ዱካክ ውስጥ ነበርኳ

በችግር ውስጥ ማለፍ ፣ በችግር ማደግ የሚያስተምረው ችግር ሲመጣ አለመቸገርን አይደለም  ችግሩ  እንደሚያልፍ  መረዳትን እንጂ !

የጠዋት ፀሃይ ውስጥ ተስፋ ማየት እያቆምኩ ነበር ፣ የምሰማው ነገር ሁሉ አልጥም ስላለኝ ማንንም ላለመስማት ከብቻዬ ጋ ብቻ ለመሆን እየታገልኩ ነበር ...

በዚህ ሁኔታዬ ዝናቡ ሲቀጠቅጠኝ ሆድ ባሰኝ ፤ አለም ላይ ሁሉም ሊያጠቃኝ የተዘጋጀሁ የመስዋዕት በግ የሆንኩ መሰለኝ ።

ዝናቡ እያባራ መጣ ፣ እምባዬም እየደረቀ ሄደ

ከዛ ዶፍ ዝናብ በኋላ
መጠለያ ከማጣት በኋላ
ሁኔታዬን ሳያገናዝብ ከቀጠቀጠኝ በኋላ
ከአለ'ማንም  አይዞህ ባይ  ከተደበደብኩኝ በኋላ

ዝናቡ ቀጥ አለ!!!

በማያሳምን ፍጥነት ፀሃይ ወጣች ።  የፀሀይ አወጣጧ የተደበደበው ልብሴን እንደሚያደርቀው ፣ የበረደው አካሌን እንደሚያሞቀው ተስፋ ሰጠኝ ።

ከዶፎ ዝናብ ቀጥሎ የወጣችው ፀሃይ ሳያት የሆነ ሚስጥር እንደነገረቺኝ አይነት ፈገግ አልኩ ።

ፀሃዬ ❤


Some people will never like you because your spirit irritates their demons. ”

`` አንዳድ ሰዎች መቼም ቢሆን ሊወዱህ አይችሉም፤ ምከንያቱም መንፈስህ ሰይጣናቸውን ስለሚያበሳጭባቸው!። ``

፦ Denzel Washington


ዲበ- አካላዊነት (Metaphysics)

ዲበ አካል የፍልስፍና ጥናት (Metaphysics) በአብዛኛው የሚያጠናው ስለመጨረሻው እውነት ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ የሚነሱት ቁልፍ ጥያቄዎች እውነታ ምንድን ነው ? እውነት ምን ማለት ነው ? የሚሉት ሲሆኑ እነዚህ ጥያቄዎችም ሌሎች ጥያቄዎችን ይወልዳሉ ፡፡

ለምሳሌ እውነታ ማለት የሆነ ነገር ማለት ነው? እውነት አንድ ነው ወይስ ብዙ? እውነት አንድ ብቻ ከሆነ በዙሪያችን ያሉ እውነት የምንላቸው ነገሮች እንዴት በዙ? የመጨረሻውን እውነት በአምስቱ የስሜት ህዋሶቻችን አማካኝነት ልናረጋግጥ እንችላለን? ወይስ ልዕለ ተፈጥሯዊና ዘመን ተሻጋሪ ነው የመጨረሻው እውነት የሚባለው ነገር ምንድን እና የቱ ነው? የመሳሰሉ ጥያቄዎች ይነሣሉ፡፡

አንዳንዴ የዲበ አካላዊነት የትኩረት ነጥብ በጠባቡ ሲታይ ይስተዋላል፡፡ ይሄ ከቃሉ አፈጣጠር ይመስላል፡፡ በአማርኛ ዲበ አካላዊ የምንለው ጥናት በአሁኑ ዘመን የፍልስፍና ሙያዊ ፍች ሜታፊዚክስ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ሜታፊዚክስ (Metaphysics) ደግሞ ከሁለት የግሪክ ቃላት ውህድ የተገኘ ቃል ነው፡፡ ሜታ እና ፊዚካ ከሚሉ፡፡ የመጀመሪያው ቃል ባሻገር የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ሁለተኛው ቃል ደግሞ የሚታይ ማለት ነው፡፡ ተደምሮ ሲነበብም ከሚታይ ነገር ባሻገር የሚል ትርጉም ያለው ነው ዲበ አካላዊነት፡፡ ከዚህ አንጻር የመጨረሻው እውነታ በአምስቱ የስሜት ህዋሳት ልንደርስበት የማንችለውና ከምናዬው ነገር ባሻገር ያለ ነው የሚል ጠባብ አረዳድ አንዳንዴ ይታያል፡፡

ከመጽሐፉ የተወሰደ

™የፍልስፍና መግቢያ
በደሳለኝ ስዩም
©ጃዕፈር መጻሕፍት

Показано 20 последних публикаций.

216

подписчиков
Статистика канала