እውቀት ከተግባርም፣ ከስራም ቀዳሚ ነው።


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


﴿ وَقُل رَبِّ زِدني عِلمًا﴾
@tofikalhabashy1

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


"አስገራሚው ነገር የራስህን ስራ አብዝተህ እያየህ የሰዎችን ደግሞ አሳንሰህ ማየትህ ነው።" ቢሽር ቢን አልሃሪስ
حلية الأولياء 8/348.


" ሳይጠይቁት መመለስ፣ የማይመልስን መጠየቅና ለማያዳምጥ ማውራት አደብ አይደለም።" ኢማሙ አዘሀቢይ
سِير أعلام النبلاء(٦/ ٤٠٨).


የቀን ገቢህ ስንት እንድሆን ትፈልጋለህ? 5000 ወይስ 100,000 ወይስ 3ሚሊዬን??

- አንድ ገፅ (ፊት) ቁርአን ስትቀራ 5000 አጅር ታገኛለህ።
- አንድ ጁዝ ብትቀራ ደግሞ 100,000 (መቶ ሺህ) አጅር ታገኛለህ።
- ቁርአን ስትጨርስ (1 ጊዜ ስታኸትም) 3 ሚሊዬን አጅር ታገኛለህ።
ቁርአን ከመቅራት ከተሳነፍክ ይችን አስታውስ።


አራት ቦታዎች ባሪያ ለጌታው ያለው ቦታ እና ውዴታ ይለካባቸዋል:
1, ማታ ጎኑን በሚያሳርፍበት ጊዜ - የአላህ ወዳጅ ጌታውን ሳያወሳ ፈፅሞ አይተኛም -
2, ከእንቅልፋ ሲነቃ - ጌታውን አውስቶ የተኛ ሲነቃ ጌታውን ከማውሳትና ከማጥራት ቀድሞ የሚያስታውሰው ነገር
አይኖርም -
3, ወደ ሶላት ሲገባ - ሶላት ኢማን የሚለካባት ባሪያዎች ለጌታቸው ያላቸው ቅርበት የሚታይባት ዒባዳ ናት-
4, በችግር እና በመከራ ጊዜ - በችግር ጊዜ ልብ በጣም የሚወደውን እንጅ አያስታውስም ወደሚያልቀው እንጅ አይሸሽም- ኢብኑልቀይም
طريق الهجرتين


አጭር ክርክር
ሸህ አልባኒ አንድ ሁሉንም አውቃለሁ ሚስጥር አይጠፋኝም የሚል ሰው ጋር ሲከራከሩ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ? አሉት ምን? አላቸው ጥያቄውን ካላወክ ምኑን ሁሉን አወከው ብለው ክርክሩ ተቋጨ።


  {أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ}.
                “አታስተነትኑምን?!"
[19] ሸረሪት:
﴿وَإِنَّ أَوهَنَ البُيوتِ لَبَيتُ العَنكَبوتِ﴾
[العنكبوت: ٤١]
   (ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡)
– ሸረሪት ቤቷን ለመስራት በሆዷ ውስጥ ድር የሚያመርት ዕጢ አላት፣ እያንዳንዱ የሸረሪት ድር ከአራት ድሮች የተጣመረ ሲሆን አራቱ ደግሞ እያንዳንዳቸው የአንድ ሺህ ድር ውጤቶች ናቸው። ያ ማለት አንድ የሸረሪት ድር የአራት ሺህ ድሮች ድምር ነውማለት ነው።
   አስገራሚው አራት ሚሊዮን የሚሆኑ የሸረሪት ድሮች ከአንድ የሰው ልጅ የፀጉር ዘለላ አይወፍሩም።
   – ሸረሪት እነዚህን አስገራሚ ድሮች በጥንቃቄ እና አስገራሚ በሆነ መልኩ በማጠላለፍ ቤቷን ትሰራለች በመቀጠልም በሚያጣብቅ ፈሳሽ ትቀባዋለች ይህ ፈሳሽ የተለያዩ ነፍሳቶች ሲያርፋ ይይዛቸዋል ሸረሪቷም ከቤቷ በቅርብ ርቀት ሁና በመከታተል ቤቷ ላይ የሚያርፋ ነፍሳቶችን መጀመሪያ በመርዝ ትገላቸዋለች ከዚያም በውስጣቸው ያለውን ፈሳሽ በመምጠጥ የእለት ጉርሷን ታገኛለች።
   – ከብዙ ድሮች የተሰራው እና በሚያጣብቅ ፈሳሽ የሚዋበው የሸረሪት ቤት እድሜው አንድ ቀን ብቻ ነው ለሁለተኛው ቀን ማጣበቂያው ደርቆ ቤቱም ከጥቅም ውጭ ይሆናል።
– የሸረሪት ትዳር: በሸረሪቶች ዓለም ቤት የምትሰራው ሴቷ ሸረሪት ናት፣ ቤቱ ሲጠናቀቅ ከቤቷ ደጅ ላይ በመሆን ወንድ የሚያማልሉ የተላያዩ እንቅስቃሴዎችን ታደርጋለች በተጨማሪም ማራኪ የሆኑ ድምፆችን ታስከትላለች ወንዱም በሁኔታው በመማረክ ወደ እንስቷ ቤት ያቀናል፣ መስተንግዶው ግን ውሎ አያድርም ሸረሪቷ ከወንዱ የፈለገችውን ካገኘች በኋላ ነፍሴ አውጭኝ ብሎ ካላመለጠ ወዳው ትበላዋለች፣ ልጆቿንም ሸሽተው ካልሄዱ ትበላቸዋለች፣ ልጆቿም ከእናታቸው የወረሱትን ከፊላቸው ከፊሉን ይበላል።
• የሸረሪት ቤት ከአሰራሩ ድክመት ባሻገር ትዳርም የማይሰምርበት በሁሉም መልኩ የድክመት ጥግ ነው።
موسوعة الإعجاز القرآني286 -2/285.


"የልብ በሽታ ያለበት ሰው ከንግግር ሁሉ እየመረጠ ለበሽው የሚስማማውን ነው የሚወስደው"። ኢብኑ ተይሚያህ
جامع المسائل


ሳትሞት የማይሞት ስራ ይኑርህ
"ልክ እንደበላሁ ነው።" የሚል ስያሜ የተሰጠው የ400 ዓመት እድሜ ጠገብ መስጅድ ግንባታ ሚስጥር እንድህ ነበር:

አንድ ታልቅ ባለሀብት ነበር ከእለታት አንድ ቀን በርከት ያለ የወይን እሸት ገዝቶ ወደቤት ለሰራተኛው ይልካል፣ ቀኑን በስራ አሳልፎ ማታ ወደቤቱ ሲመለስ ትንሽ አረፍ ብሎ እስኪ ከወይኑ እሸት ስጡኝ ሲል ሚስቱን ጠየቀ። ባለቤቱም በልተነዋል የቀረ የለም አለችው። ሰውየውም መልስ ሳይሰጥ በድንገት ብድግ ብሎ ከቤቱ ወጣ ባለቤቱ ብትጠራውም አልሰማ፣ ወደ ትልቅ የመሬት ደላላ ቤት አመራ ደላላውን ከተማው ላይ ቆንጆ የሆነ ቦታ መግዛት እፈልጋለሁ አለው። ደላላው ካቀረበለት አማራጮች የተሻለውን ገዛ፣ ወዲያውኑ መስጅድ የሚሰራ ኮንትራክተር ፈለገና እዚህ ቦታ ጥሩ መስጅድ እንዲሰራ እፈልጋለሁ አለው ስምምነቱን ወዲያው ጨረሱ፣ ባለሀብቱም አሁኑ ሲጀመር ማየት አለብኝ አለ፣ ኮንትርክተሩም ሰራተኞችን አሰባስቦ አስጀመረ፣ ባለ ሀብቱም መስጅዱ መጀመሩን አይቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ። ባለቤቱ የት ሂደህ ነው ብላ ጠየቀችው?
አሁን ብሞትም አይቆጨኝ እናንተ በህይዎት እያለሁ አንድት ፍሬ የወይን እሸት ለማስቀመጥ ካላስታወሳችሁኝ እንዴት ነው ከሞትኩ በኋላ በሶደቃ እና በመልካም ዱዓ የምታስታውሱኝ?! አላት።


اللهم صل وسلم على نبينا محمد
"አንድ ሰው በእስትንፋሱ ልክ በነብዩ ላይ ሶላትን ቢያወርድ ሐቃቸውን አይወጣም።" ኢብኑልቀይም
جلاء الأفهام 344.


"ወንጀልህን እንደምትደብቅ ሁሉ መልካም ስራህንም ደብቅ፣ በስራህም አትደነቅ እድለኛ ትሆን እድለ ቢስ ስለማታውቅ።" አቡ ሃዚም
شعب الإيمان 9/195.


የነብዩ ሚስቶች እና የአማኞች እናቶች
1, ኸድጃ ቢንት ኹወይሊድ: በመካ መልክተኛው በ25 ዓመታቸው አገቧት፣ በአርባ ዓመታቸው መልክተኛ ሲሆኑም ከሰው ቀድማ አመነችባቸው፣ ለጥሪያቸውም የእውነት አጋር ነበረች ወደ መድና ከመሰደዳቸው 3 ዓመት ቀደም ብሎ ሞተች።
ኸድጃ ከሌሎቹ የነብዩ ባለቤቶች ለየት የሚያደርጓት በርካታ ነገሮች አሉ ከእነርሱም መካከል:
1, እስክትሞት ድረስ ሌላ ሚስት አላገቡም
2, ከኢብራሒም ውጭ ያሉት ስድስቱም ልጆቻቸው ከእሷ ነው የተወለዱት
3, ከሴቶች ሁሉ የላቀች ሴት ናት
4, ታላቁ ጌታችን እንዲሁም የመላኢኮች አይነታ የሆነው ጂብሪል ሰላምታ አቅርበውላታል
ኢማሙል ቡኻሪይ አቡሁረይራን ዋቢ አድርገው እንደጠቀሱት ጂብሪል ወደ ነብዩ መጥቶ ኸዲጃ እቃ ይዛ ወደ አንተ እየመጣች ነው ስትደርስ ከጌታዋ እንዲሁም ከእኔ የሆነን ሰላምታ አቅርብላት ጀነት ውስጥ ባለ ቤትም አበስራት ብሏል። ቡኻሪይ 3609
5, መልክተኛውን አንድ ቀን እንኳ አስቆጥታም ሆነ አስከፍታቸው አታውቅም እሳቸውም አንድም ቀን ወቅሰዋትም ሆነ እርቀዋት አያውቁም።
6, ከሰዎች ሁሉ ቀድማ መጀመሪያ ጥሪያቸውን የተቀበለች እና ያመነችም ኸድጃ ናት።
ኢብኑል ቀይም
جلاء الأفهام 264.


"መይሙን ቢን ሚህራን - አላህ ይዘንላቸውና- ሰዎችን በባለስጣኖች በር ላይ ተሰባስበው ተመለከቱና ባለስልጣናቶች ዘንድ ጉዳይ ኑሮት ለመግባት የተከለከለ የአላህ ቤቶች ክፍት ናቸውለት መጥቶ ሁለት ረከዓ ሰግዶ ጉዳዩን ይጠይቅ አሉ።"
مجموع رسائل ابن رجب 3/127.


"ሙስሊሞች ላይ በሚደርስ ጉዳት መደሰትና በችግራቸው መሳለቅ ከታላላቅ ወንጀሎች ይመደባል።" ኢብኑልቀይም
مدارج السالكين 1/402.


የስስት ጥግ😂
አንድ በጣም ስስታም የሆነ ሰው እንግዳ መጥቶበት ልጁን ስጋ ቤት ሂደህ ቀቆንጆውን መርጠህ ለእንግዳችን ግማሽ ኪሎ ገስተህ ና ብሎ ይልከዋል ልጁም የአባቱ ልጅ ነውና ሂዶ ቆይቶ ሳይገዛ ተመለስ አባትም ለምን ሳትገዛ ሲለው ስጋ ቤት ሂጀ ካለህ ስጋ ቆንጆውን መርጠህ ግማሽ ኪሎ ስጠኝ አልኩት ባለስጋውም አብሽር ቂቤ የሆነ ስጋ ነው የምሰጥህ ሲለኝ ለዚህ ለዚህማ ለምን ቅቤ አልገዛም ብየ ቂቤ ተራ ሒጀ ከቆንጆ ቂቤ ግማሽ ኪሎ ስጠኝ ስለው አብሽር ማር የሆነ ቂቤ ነው የምሰጥህ አለኝ እኔም እንድህማ ከሆነ ባንድፈቱ ለምን ማር አልገዛም ብየ ማር ተራ ሔድኩ ባለማሩን ከቀንጆው ማር ግማሽ ኪሎ ስጠኝ ስለው አብሽር ወለላ ውኃ የመሰለ ማር ነው የምሰጥህ አለኝ ውኃማ እኛ ቤት አለ ብየ ጥየ መጣሁ አለ።
አባትም እሰይ የኔ ብልህ ጥሩ ነው የሰራኸው ግን አንድ ነገር አጥፍተሀል አለው። ልጅም ፈጥኖ ምን? ሲል ጠየቀ
አባትዮውም ይሄን ሁሉ መንገድ ስትሄድ ጫማ መጨረስህን አላሰብክም አለው።
ፈጣኑ ልጅ ፈገግ ብሎ የእንግዳውን ጫማኮ ነው አርጌ የሄድኩት አለ።


"የብዩን - ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - ሱና ካገኛችሁ ተከተሏት ወደ ሌላ አትዙሩ ።" ኢማሙ አሻፊዒይ
حلية الاولياء (١٠٧/٩)


"ጠቃሚ ዕውቀትን የሚፅፍ ሰው ፁሁፋ እስካለ ድረስ የፃፈውን የሚያነቡ የሚፅፋ እና በተግባር የሚያውሉ ሰዎችን ሁሉ አጅር ይጋራል።" ኢማሙል ሙንዚሪይ
الترغيب والترهيب 1/65.


"የዱሓ ሶላት (ረፋድ ላይ የሚሰገድ ሶላት) የለይል ሶላት ተኝቶ ላልሰገደ ሰው ምትክ ይሆንለታል። " ኢብኑ ተይሚያህ
مجموع الفتاوى 22/284.
የለይል ሶላት ባትሰግድ የዱሓ ሶላትን አታሳልፍ።
የዱሓ ሶላት ፀሀይ ከወጣች ከ15 ደቂቃ በሇላ ጀምሮ የዙሁር ሶላት ሊደርስ 15 ደቂቃ እስኪቀረው የሚሰገድ ሲሆን 2ረከዓ ወይም 4 ከዚያም በላይ መስገድ ይቻላል።


"አርባ ዓመት ያክል ሶላት በጀመዓ አልፎኝ አያውቅም።" ሰዒድ ቢን አልሙሰየብ
السير 5/126.


"ለጌታው ብቻ ብሎ የሚሰራ ሰው በአሸዋ ላይ እንደሚጓዝ ነው ኮቲው አይሰማም የሄደበትን ግን ይታያል።" ዐብዱሏሂ ቢን መስዑድ
جامع العلوم والحكم



Показано 20 последних публикаций.

81

подписчиков
Статистика канала