የእሳት አደጋ መድረሱን ተከትሎ የድረሱልን ጥሪ ሲያሰሙ የነበሩ እናት ህይወት አለፈ❗
በአርባ ምንጭ ከተማ ዛሬ ረፋድ 4 ሠዓት አከባቢ በተለምዶ ' ቡቡ ሜዳ ' ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በሚገኘዉ አዲሱ ገበያ የእሳት አደጋ ተከስቶ በንብረት ላይ ዉድመት ማድረሱን የከተማው አስተዳደር ፖሊስ አስታውቋል።
በእሳት አደጋዉም የሰዉ ሕይወት መጥፋቱን የሚገልፁ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን ማብራሪያ ስቷል ።
የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር ጋፋሮ ቶማስ ፤ በአከባቢው በሚገኝ አንድ የኤሌክትሮንክስ ሱቅ ዉስጥ በኤሌክትሪክ ኮንታክት ምክንያት በተነሳ የእሳት አደጋ 12 ሱቆች መዉደማቸዉን ገልጸዋል።
በአደጋው ወቅት በገበያው ዉስጥ በተለምዶ መንገድ በጩኸት ይድረሱልን ጥሪ ሲያደርጉ ከነበሩ ሴቶች መካከል አንዲት እናት ባለባቸው የጤና እክል ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።
እኚህ እናት የልብ ሕመም እንደነበራቸው የገለጹት ም/ኢንስፔክተር ጋፋሮ ፤ በጩኸት የድረሱልን ጥሪ ሲያሰሙ ሳለ በመድከማቸው ወደ ነጭ ሳር ሆስፒታል ቢወሰዱም ሕይወታቸው ማርተፍ አልተቻለም ነው ያሉት።
ሆኖም በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሕይወቷ ያለፈዉ በእሳት አደጋዉ በደረሰ ጉዳት ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነዉ ብለዋል።
በገበያዉ ዉስጥ ያለዉ የሱቆች አሰራር እና አጠቃቀም ለእሳት አደጋ አጋላጭ ነዉ ያሉት አዛዡ ፤ ሕይወቷ ያለፈዉ ግለሰብ በገበያው ዉስጥ ሱቅ እንደነበራቸውና ሱቃቸዉም እሳት አደጋዉ እንዳልደረሰበት ገልፀዋል።
" ሞች ወ/ሮ አበባየሁ መንገሻ እንደ እናት ያሳደጉኝ እናቴ ናቸዉ፤ የሞቱት በእሳት አደጋዉ አይደለም " ያሉት አቶ አማኑኤል ሰይፉ የተባሉ ነጋዴ አስቀድመው የልብ ሕመምና የሕክምና ክትትል እንደነበራቸው አስረድተዋል።
አክለው በእሳት አደጋዉ ወቅት መደንገጣቸዉና ከሌሎችም ሴቶች ጋር ሆነዉ ለይድረሱልን ብዙ መጮኻቸዉን ተከትሎ መዳከማቸዉንና ወደ ነጭ ሳር ሆስፒታል ቢወሰዱም ሕይወታቸው ማለፉን ነው የገለጹት።
https://t.me/fanos_newsshttps://t.me/fanos_newss