➖➖➖➖➖➖➖➖
ልብ ብለው ያንብቡ!!
➖➖➖➖➖➖➖➖
❀━┅┉┈ ┈┉┅━❀
ልጁ ነገውን ሚስት ሊያገባ ሽር ጉድ ላይ ሳለ እናት
ድንገት ከዚህ አለም በሞት ትለየውና የሰርጉን ፕሮግራም
ወደ አመት አዘዋወረው ። የማይደርስ የለምና ያ የቀጠሮ
ቀን አመቱን አክብሮ ብቅ አለ ። ልጁም የሚፈልጋትን ሴት
አገባ ። ያን ግዜ አባት በባዶ ቤት ብቻቸውን ሊቀሩ
ተገደዱ ።
፣
ምክንያቱም ባለቤታቸው ከሞተች በኋላ ከዚህ አንድ
ልጃቸው ሌላ ማንም አልነበራቸውም ። ልጅም ከአዲሷ
ሚስቱ ኑሮ ጀመረ ። ልጁ አንዳንዴ ሚስቱን ይዟት አባቱን
ሊጠይቅ ይመጣል ። አንዳንዴ ደሞ እሱ አባቱን ጠይቆ
እስኪመለስ እሷ ቤተሰቦቿ ዘንድ ትጠብቀዋለች ። ብዙ
ግዜ የሷን ቤተሰቦች ብቻ እንዲጠይቅ ታስገድደው ነበር ።
፣
በዚህ መልኩ አምስት አመታት ተቆጠሩ ። በዚህ መሀከል
እኚህን ምስኪን አባት በእርጅና ላይ በሽታው አዳከማቸው
። የአባቱ ሁኔታ ያሳሰበውም ልጅ አባቱን ቤት ሊወስዳቸው
እና ሙሉ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ሲጠይቃቸው ።
የልጁ ሚስቱ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው እንግዳ እንዳይሆኑ
ስለስጉ ጥያቄውን አልተቀበሉትም ። ከዚያም የረጅም
ግዜ የልጃቸው ውትወታ ለጥያቄው እጅ እንዲሰጡ
አደረጋቸውና ልጃቸው ቤት ቀሪ ዘመናቸውን ሊያጠናቅቁ
ብቅ አሉ ።
፣
ያን ግዜ የልጃቸው ሚስት ደስታ ራቃት ። ሁለት አይነት
ምግብ ማብሰል ጀመረች ለሽማግሌው በግዴለሽነት
ትሰራና ታቀርብላቸው ነበር ። አባት ምግብ ብቻቸውን
መብላት ቢከብዳቸው እንኳን ከልጃቸውና ከልጅ ልጆቻቸው
አብረው መብላት አትፈቅድላቸውም ነበር ። የሚስቱ እና
ያባቱ ሁኔታ ትንግርት የሆነበትም ልጅ በሁለት መዕበላት
ውስጥ ሆኖ ይናወጥ ጀመር ከአባቴ ልሁን ወይስ
ከሚስቴ !!!
፣
ያን ግዜ ሚስት እንድ ሀሳብ ሰነዘረች ፦"ለምን ሚስት
አናመጣላቸውም እነሱንም ትንከባከባለች እኛም
እንገላገላለን" አለች ። ልጅም በዚህ እድሜያቸው
አግብተው መኖር እንደማይችሉ ስላመነ አንድ አማራጭ
ፊቱ ላይ ድቅን አለለት ። አረጋውያን ማቆያ/ሰው
የሌላቸው ሽማግሌዎች የሚኖሩበት ድርጅት ውስጥ
ሊወስዷቸው ወሰኑ እና ይዘዋቸው ሄዱ ። ልጁም
ለዘመናት አብሮት የኖረውን የገዛ አባቱን በገዛ እጁ ገብቶ
ማያውቅበት ግቢ ውስጥ አስገብቶት እንባውን እያፈሰሰ
ተመለሰ ።
፣
አባቱን እዛ ግቢ ውስጥ ካስገባቸው በኋላ በሳምንቱ
ሊጠይቃቸው ወደ ግቢው ሲገባ አባት በብጣሽ ወረቀት
መልዕክት አስቀምጠውለት ከዚህ አለም በሞት
ተለይተዋል ። መልዕክቱ እንዲህ ይል ነበር ፦
፣
"ልጄ !!! ካሳለፍኳቸው ምርጥ ግዜያት ሁሉ ደስ የሚለኝ
ድሮ ከስራ ስገባ አንተ ያለህበት ክፍል ገብቼ ላንተ
መጫወቻዎችን ጣፋጭ ነገሮችን ስሰጥህ ነበር ።
፣
ልጄ !!! ካሳለፍኳቸው ምርጥ ግዜያት ሁሉ ደስ የሚለኝ
ዋና ላስለምድህ ገንዳ ውስጥ አንተን ተሸክሜ ምዋኝበት
ግዜ ነበር።
፣
ልጄ !!! ካሳለፍኳቸው ምርጥ ግዜያት ሁሉ ደስ የሚለኝ
አንተ ህፃን እያለህ ቢሮ ይዤህ ስሄድ አንተም ቢሮ ውስጥ
የሚጠቅሙኝን ወረቀቶች ስትቀዳድድብኝ በፍቅር ፈገግ
እያልኩ የምመለከትህ ግዜ ነበር ።
፣
ልጄ !!! በህይወቴ ካሳለፍኳቸው ምርጥ ግዜያት ሁሉ ደስ
የሚለኝ ላንተ የምትፈልገውን ሁሉ ልብስ ልገዛ በኪሴ
ያለውን ብር ባጠቃላይ ሳወጣ እና አንተ አምሮብህ እኔ
ደሞ የተቀደደ ልብስ ስለብስ ነበር ።
፣
ልጄ አሁን እኔ አንተን አልወቅስህም ። ነገር ግን በእንባ
ተሞልቼ ይሄን ምፅፍልህ የኔ መጨረሻ እንዲህ ይሆናል
ብዬ አስቤ ስለማላውቅ ነው ። የህይወቴ መጨረሻ ባንተ
እቅፍ እንዲሆን ነበር ምኞቴ ። ውድ አባትህ" እንብቦ
እንደጨረሰ እንባውን እያፈሰሰ ፀፀቱን ተሸክሞ ወጣ ።
_______________በህይወት እስካላችሁ ድረስ አባታችሁን እናታችሁን
እያገለገላችሁ ኑሩ ። ""ቆም ብለክ አስብ አስቢ ።
፣
፣
Social mediaን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ
እንጠቀም ፡፡ ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ
ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ፡፡ በምድር ላይ የምናደርጋቸው
ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው
ይከፈሉናል ፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን
ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና ፡፡
፣
ስለዚህ አንተም ይህ አሁን ያነበብከው
መጣጥፍ ትምህርት ሰጪ ሆኖ ካገኘኅው አንተም
ዘመዶችህ እንዲያነቡትና ትምህርት እንዲወስዱ ዘንድ
ሼር ያድርጉላቸው።
👇Share Share Share👇
@fikir_yishalegnal ከ
@yefikir_tarik ጋር በመተባበር የቀረበ