ኤልሳ[FB]™ _____________________Elsa[FB]


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


የስራዎy for followers !
የ ኤልሳ[FB] ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል እነሆ
♥♥♥
በዚህ ቻናል የ ኤልሳ[FB]ን የስነ- ፅሁፍ ስራዎች በብቸኝነት እንዲሁም ሌሎች ውብ ፕሮግራሞችን ታገኛላችሁ
AMAZING QUOTES
MIND QUESTIONS AND OTHERS!
ግጥም
ድርሰት
አጫጭር አባባሎች ፍልስፍናዎች እና ሌሎችም!
@fkerofficial
ELSA[FB] OFFICIAL CHANNEL !

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Watch "ተለቀቀ ተለቀቀ !........አንተ እኮ አታውቅም! የኤልሳ[FB] አዲስ ግጥም fOLLOW AND SHARE..." on YouTube
https://youtu.be/v4fXILEPpks


እንዳትከተለኝ!

አልክድም...
ሳታውቀኝ አውቄህ ብዙ ለፍቻለሁ
ሳትለምደኝ ለምጄህ አቅሌን ስቻለሁ
አይወድሽም ስባል በፍፁም ብያለሁ
ስለ አብሮነታችን ስለት ተስያለሁ...
አልዋሽም...
እየቀለድክብኝ እኔም እያወኩት
መሄድን ጀምሬ ስንቴ ነው የዞርኩት?
የጠራኸኝ መስሎኝ የተደናበርኩት..

ግን...
ከእለታት ግማሽ ቀን መታገሴ አብቅቶ
ወደኋላ ማየት ማመንታቴ ቀርቶ
ልቤ ቆርጦ ጥሎህ በልቡ ሲገልህ
የበደልህ ፅዋ ከኔ ሲነጥልህ
በድግምግም ስህተት ተገፍቼ ስርቅ
ላላስታውስ ትቼህ ከራሴ ስታረቅ
አለመወደድን በልብህ ላይ ስፈርድ
ላልወድህ ስጠላህ ላልመለስ ስሄድ
ልክ እንዳላወቀ  ምነው እንዳትለኝ
ከመንገዴ እንዳትቆም እንዳትከተለኝ!


✍ኤልሳ[FB]
@Fkerofficial








አንተኮ አታውቅም!


አንተ እኮ አታውቅም...
አይኔ ሲፈልግህ ከሰው መሀል
ከእይታዎቼ ገለል ብለህ ስትጎል..
ከእልፍ ወላጅ መሀል እናቱን እንዳጣ
ጥፋትን አጥፍቶ ልክ እንደተቆጣ
እንደጨቅላ ህፃን ዳዴ እንደሚቆጥር
ፈልጎ ሲያጣህም እምባ እንደሚቋጥር...

አንተኮ አትሰማም
በቀትር በውድቅት በየቀን በመአልቱ 
ስምክን እያነሳው እንደዋልኩ ለስንቱ
ካፌ ቃል ሳይወጣ እንደሚታገለኝ
ልቤ ስንቴ አምጭው ናፈቀኝ እንዳለኝ!

አንተኮ አታይም...
ባካል ሳንራራቅ ገና ሳንለያይ
ከጎኔ ተቀምጠህ ልቤ እንደሚሰቃይ
አይኖችህ ሳያዩኝ ስንቴ እንዳማተርኩህ
በልቤ ዙፋን ላይ ሾሜ እንዳነገስኩህ
ሳላወራህ ስውል ፍቅሬን እንደሚያመኝ
ድምፅህን ስሰማ ሳቅ እንደሚቀድመኝ
ሳላገኝህ ስቀር ነፍሴ እንደምትቆዝም
በድምፅህ መለከፍ እድሜ እንደሚያረዝም
ኩሩው ማንነቴን እንደገደልኩልህ
ከራሴ እያኮረፍኩ ስንቴ እንደሞትኩልህ
ከአንደበትህ ዘር ላይ ፍቅር እንደምለቅም
አንተኮ አታውቅም!...


                                                        ኤልሳ[FB]

👉👉@fkerofficial






አይታይም?



እኔ እወድሀለሁ ውዴ ቅባርጥሴ
በፍቅርህ ረሀብ ልትወጣ ነው ነፍሴ
በየሰአታቱ በየደቂቃቱ
ውዴ የኔ ፍቅር ብዬ አለማለቱ
አትወደኝም ብለህ እንዳታስብ ፍፁም
ቃላት እንደ አርምሞ ስሜትን አይገልፁም!

አይታይም እንዴ?
አይታይም እንዴ የአይኖቼ መርገብገብ
አይኖችህን መራብ በናፍቆት መንገብገብ
አይነበብም እንዴ ከዝምታዬ ላይ
የታወረ ፍቅር የታፈነ ስቃይ
የተሸነፈ ልብ እኔነቱን ያጣ
ፍቅሩን ባለመግለፅ ራሱን የቀጣ
አጠገቡ እያለህ  በሀሳብ የሚነጉድ
አይታይም ፍቅር? አይነበብም መውደድ??

ኤልሳ[FB]
👉👉@Fkerofficial




ዛሬም...


ጉሮ ወሸባዬ ሙሽሪት ልመጂ
ከናትሽ ካባትሽ ባልሽን ውደጂ
ሙሽራው ማማሩ ሙሽራው ማማሩ
ቃላት አጣጣሉ ውብ አነጋገሩ...
እንዳልተባለልን እየተጨፈረ
ያ ሁሉ ምርቃት ተረት ሆኖ ቀረ
ውሎዬ ካይንህ ነው አይኔም ካንተ ከንፈር
ቀድሞ ለመታረቅ ማን ያውራ ማን ይድፈር?
የኔነት አንተነት ዛሬ ሁሉም ቀርቶ
የመኖሬ ትርጉም ስነጠልህ ጠፍቶ
ያ ሁሉ አልፎ እንኳን ሁሌ አስብሀለሁ
ይግረምህ የኔ ውድ ዛሬም ወድሀለሁ


ኤልሳ[FB]

👉👉@Fkerofficial




ወንድ ነህ!


ምናልባት ..
ትወደኝ ይሆናል ልብህ እስኪጠፋ
ትውልም ይሆናል ለሳቄ ስትለፋ
ግን ደሞ ወንድ ነህ...
ግን ደግሞ ወንድ ነህ ኢ- ታማኝ ፍጥረት
የሀሰታት ንጉስ የክህደት ተምሳሌት
አትሆንም ይሆናል...
የተሰበረ እምነት ግን በምን ይቃናል.?
አንዴ የተከዳ ልብ ደግሞ እንዴት ሰው ያምናል?
በፍፁም አያምንም!
ቢያምንም.... እንደፊቱ አይሆንም
እንዴት ነው ከሌሎች ለይቼ የማምንህ?
ባለመታመን ጥግ ልቤ የወሰነህ
አንተ እኮ ወንድ ነህ

ኤልሳ[FB]
@fkerofficial




ሰላም ሰላም...
ኤልሳ[FB] ነኝ...
ሁላችሁም በተለይ ሴቶች ስለምን እንዲገጠምላችሁ ትፈልጋላችሁ?
ማለትም ለምሳሌ ስለ ፍቅር ከሆነ ምን አይነት ሁኔታ ላይ ስላለ ፍቅር?... ስለሰው ከሆነ ስለምን አይነት ሰው?
COMMENT ላይ ፃፉልኝ

👉👉@fkerofficial










ነፍስ ያፈቀረ ሰው

ከሳ ጠቋቆረ ፀለመልሽ ፊቱ
ልብሱ ተራገበ ተቆጠረ አጥንቱ
ሰውነቱ ዛለ ገላው ገላ ሸሸው
መኖሩ ተጠላ ፊቱን አጠለሸው
ተጎሰቋቆለ ቅሪት መስሎ መጣ
መሸብሸብ ጀመረ ገፁ እየገረጣ
ዱሮ ነበር እንጂ እንዲ ሳይሳጣ
አሁንማ ቀፍፎ ሰውነቱን አጣ
አይገባሽም ላንቺ ተይው አትበሉ
ነፍስ ያፈቀረ ሰው አይታየውም ሁሉ...

✍ኤልሳ[FB]
@Fkerofficial

Показано 20 последних публикаций.

796

подписчиков
Статистика канала