#ExitExam
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ፈተናውን 250 ሺህ ለሚደርሱ ተማሪዎች ለመስጠት ዝግጅት መደረጉንም ገልጿል፡፡
በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ ሚጀና እንዳሉት፥ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ሲወጡ ሊኖራቸው የሚገባውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ለመለካት የሚሰጥ ነው፡፡
የሚወጡ ጥያቄዎችም የየትምህርት ክፍሎች ምሩቃን እንዲኖራቸው የሚጠበቀውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት መሠረት አድርገው የሚዘጋጁ ናቸው ብለዋል።
ሚኒስቴሩ ፈተናውን ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ጠቅሰው፤ፈተናው ተዘጋጅቶ እንዲገመገም ተደርጓል ነው ያሉት።ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች ዝርዝር በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ተረጋግጦ ነው ወደ ሚኒስቴሩ የሚላከው ብለዋል፡፡
በፈተናው ሞባይል ይዞ የሚመጣና መታወቂያ ሳይዝ የሚመጣ ተማሪ ፈተናውን መውሰድ እንደማይችል ጠቅሰው፥ ተማሪዎች ይህን አውቀው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል
Join for more 👇
https://t.me/GraduationInfo