🌺#ሂወት_ይቀጥላል
አንዳንዴ ሂወት ውስጥ እንዲህ ያጋጥማል
እንዳሰብከው ሳይሆን አንተ እንደጠበከው
ፍፁም ተቃራኒ ሁኖ ነው ሚገኛው
ጎንህ ላለው በርቶ ላንተ ይጨልማል
ሌትተቀን እየጣርክ ትርፍህ ድካም ሁኗል
ያቀድከው ያለምከው አልሳካ ብሎህ
መጣ ያልከው ቀርቶ፣ ደግ ያልከው ከፍቶብህ
የኔ ያልከው ወዳጅ ፣ የሩቅ ሰው ሁኖብህ
ውስጥህ ብቸኝነት ፣ ተሞልቶ ባዶነት
ድንግርግር ብሎህ ትርጉሙ የሂወት
በቃ ሁሉም ነገር ስልችት ብሎሀል
ከተስፋ መቁረጥ ስር ካፍፉ ቁመሀል …
,
,
ልብ በል ወዳጀ #ሂወት_ይቀጥላል
#ጨለማን ባናቅ ኑሮ እኮ #የብርሀንን ዋጋ ባልተገነዘብን ነበር ፣ #ማጣትን ባናይ ኑሮም
#የማግኛት ትርጉም በቅጡ ባልገባን ነበር ፣ #የደግ_ሰዎችን ግምት አንድታቅ
የሚያደርጉህም #የክፉወች መኖር ነውኮ።
ሁሉም የሚሆንበት የራሱ ምክንያት አለው
አየህ የሂዎት ገፆች ብዙና የተለያዩ ናቸው ሁሉም ገፆች #መልካምና_ጥሩ እንዲሆኑ ግን
መጠበቅ የለብህም። የንጋቱዋን ፀሀይ ለመሞቅ የለሊቱን ጨለማ በትግስት ማሳለፍ ግድ
ነው ።
#ልብ_በል ባንተ መቆም የሚቆም ባንተ መኖር የሚኖር ቢያንስ አንድ ሰው አለ ስለዚህ
የፈለገውን ያክል ነገሮች አሰልቺ ቢሆኑብህ እንኳ #ተስፋ_መቁረጥን የመጨረሻ ምርጫህ
እንኳ አታድርገው ። ከፈጣሪህ አትራቅ ፣ ዛሬ ላይ ማድረግ ያለብህን ካንተ የሚጠበቀውን
እያደረክ ነገን መልካም እንደሚሆን #ተስፋ አድርግ ።ማን ያቃል ባልጠበከውና ባላሰብከው
መንገድ ሂወት በራሷ የተቃናች ትሆን ይሆናል ምክንያቱም #ሂወት_ይቀጥላል ።