"ከቀን ወደ ቀን በትዳር ላይ እየተከሰቱ ያሉ ስብራቶች የትዳር ብቻ ሳይሆኑ የሀገር ስብራቶችም ናቸው" - የጋብቻ አማካሪው ሀበንዮ ሲሳይ
****ኢትዮጵያ ለትዳር ትልቅ ስፍራ ከሚሰጡ አገራት መካከል አንዷ መሆኗ ይታወቃል፤ በሐይማኖትም ሆነ በባህል በኢትዮጵያ ትዳር ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ነው።
ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፍቺ በተለይ በከተሞች አካባቢ እየጨመረ መምጣቱን የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ለአብነትም የካቲት 7/2016 ዓ.ም የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ያወጣውን መረጃ መጥቀስ ይቻላል።
ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር መረጃው ላለፉት ስድስት ወራት ብቻ በአዲስ አበባ ፍቺ በ106.7 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ያመላክታል።
ኢቢሲ ሳይበር ይሄንን አስመለክቶ የጋብቻ አማካሪ የሆኑትን ሀበንዮም ሲሳይን አነጋግሯል።
እንደ አማካሪው ገለጻ ከሆነ ጋብቻ እና ትዳር የሚሉት ቃላት በተለዋዋጭነት የምንጠቀማቸው ቃላቶች ናቸው።
ጋብቻ ከአንድ ሰው ጋር ብቻ የሚል ትርጉም እንዳለው ገልጸው፤ ትዳር የሚለው ቃል ደግሞ ሰፋ ያለ ትርጉም እንዳለው ያብራራሉ።
በማብራሪያቸውም፤ ትዳር የሚለው ቃል "ሀደረ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ እና ማስተዳደርን የሚያመለክት ነው ይላሉ፤ በዚህም ትዳር ማለት ትንሽ ሀገር መሆኑን ይገልጻሉ።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0ohchxtCLyAkjkNQRBaqd8F1ZMuuxKsFzPmneJaJ9wbnjeCW151QC1r5qkSXejwZ8l