..........🌺ፍቅር ወይስ ውለታ🌺.......
🌹እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌹
💐ክፍል..3
አብሪሽ ነው ንዴቴ አንድ ጢስ በኖ ጠፋ ግራ እስኪገባኝ ፈገግ አልኩና አልሄድክም እንዴ አልኩት አዋ ሰው አየጠበኩ ነበር ጓደኛዬ ጥሎኝ ሲሄድ እኔም መጠበቁ አስጠላኝ ተሸኚኝ አለ እእ
አልኩት አዋ ምነው አለ ምናልባት ወንድ ልጅ ሸኚኝ ሲል የመጀመርያዬ ሰለ ሆነ ይሆን አልኩት በቃእኔ የመጀመርያሽ እሆናለኋ ብሎ እየተሳሳቅን ግማሽ መንገድ ድረስ አብረን ሄድን በቃ ከዚ በኋላ በታክሲ እሄዳለሁ አለኝ እሺ ቻው ሲለኝ አንተ በቃ የምርህን ነው እንዴ አትሸኘኝም እንዴ አልኩት ሸኚኝ እንጂ ለሽኝሽ አላልኩም ደግሞ ሚስቱካዬን ለውሽማዋ ጥለሽልኝ መጣሻ አለኝ እ አልኩ በመሃል ታክሲ ሲቆምለት ደውይልኝ ብሎኝ ሄደ እኔም ግራ እየተጋባሁ ወደ ቤት ሄድኩኝ ፍቅርተ ጋር ሳምንቱን ሙሉ አልተገናኘንም አብሪሽ ልክ በተገናኘን በሳምንቱ ሚሴጅ ላከለኝ ሰለ ፃፈለኝ ደስ አለኝ ቡና አትጋብዢኝም እንዴ አለ በልቤ ይሄ ልጅ አርጉልኝ እንጂ ላድርግላቹ አያውቅም እንዴ አልኩኝ እሺ ግብዣ በእኔ ሂሳብ በአንተ አልኩት በይ እሺ አስር ሰአት ላይ እንገናኝ ደግሞ እንደ ሚታነቅ ሰው በዶ ኪስሽን አትምጪ አለኝ ስቄ እሺ አልኩት እስካየው ሰለ ቸኮልኩ ነው መሰለ ሰአቱ አልሄድልኝ አለ ጓደኞቼ ደውለው ጠፋሽብን ብለው ጨሁብኝ በኋላ እንገናኛለን ብዬ ወደ ፀጉር ቤት ሄድኩኝ ብዙም ወራፍ ሰላልነበረው ቶሎ ጨረስኩ ሚገርመው ስንት ስራ ስስራ ቆይቼ ሰአቱ ግን አልሄደም የትኛውንም ወንድ ለማግኘት እንዲህ አጣድፎኝ አያውቅም ብቻ ሰአቱ አይደርስ የለ ደርሶ ተገናኘን በትኩረት አየኝና።እኔን ለማግኘት ወደ ሶስት መቶ ብር አውጠሻል አለኝ ሳቄ አመለጠኝ ያውም የታክሲ ሳይጨምር ነው አለኝ ምነው የቢዝነስ አማካሪ ነኝ አልክሳ አልኩት እሱም ሳቀና ፍቅርተ ደህና ናት አለ ከአንድ መቶ ስልሳ ስምንት ሰአታት በፊት ደህና ነበረች አልኩት ሳቁን እዛኔ አየሁለት በጣም ደስ ይላል ከልቡ
ሚስቀው ነገር ውስጥን ደስ ያሰኛል ተጫዋች ነሽ አለ ምነው አልተገናኛቹም አልኩት አፍራ ነው መሰለኝ አንዴ ደውዬላት አታነሳም አለኝ እንዴት ምን ያሳፍራታል ስለው የዛሬ ሳምንት እኮ ጓደኛዋ ነው ብላ ያስተዋወቀች ለእኔ እኮ ምርጥ ጓደኛዬ ነው እንዳትደናበሩ ሰለ ፈለገ ነው ዝም ያለው አለኝ እኔ ራሱ እንደዚህ ሲለኝ ተሸማቀኩ
ለማነኛው ያለፈው አልፏል እርሺው አለኝ ከዛን ቀን ጀምሮ አብሪሽ ጋር እንገናኝ ጀመር ግንኙነታችን በጣም ጠበቀ ፍቅርተ ጋር ሙሉ በሙሉ አቆመ እሷም ሌላ ጓደኛ ያዘች አንድ ቀን ኤሚ ምንላት
ጓደኛችን ልታገባ ቀን እንደ ቆረጠች ነገረችን በጣም ደስ ብሎን እያለ አንዷ ሚዜ እኔ አንደ ሆንኩ ነገረችኝ ምን ልበላት በጣም ጨነቀኝ ኤሚ ማለት በጣም ብዙ ሚቀርቧት ጓደኞች አሏት ግን እኔን መርጣ ሚዜዋ ስላ ደረገችኝ ምን ብዬ እንቢ ልበላት ለመጀመርያ ጊዜ ነው ለሚዜ ነት ስመረጥ
ሳምንቱን ሙሉ ለእሷ የተለያየ ነገር ስናዘጋጅ ቆየን ቤተሰቦቿ ባህር ዳር ናቸው በዚህ መሃል ለአብሪሽ ሚዜ እንደ ተመረጥኩ ነግሬው ነበር ደውዬ አልልሽም በሎ ሳቅ አለና ስትደርሺ ደውይልኝ አለ እሺ ብዬው ስልኩን ከመዝጋቴ ነይ ውጪ መኪና መጧል ብለው አዋከቡኝ እና በግዜ ወጣን ባህር ዳር እንደደረስኩ የወንዶችና የሴት ሚዜዎች ጊዜ አለ ተብሎ ለባብሰን ከምን አይነት ሰው ጋር እንደሚገጥመን እያሰብን ወደ ሆቴል ጉዞ ጀመርን ሆቴል ስንደርስ ወንዶቹ ሚዜዎች ቀድመውን ደርሰዋል ሞቅ አርገው ተቀበሉን ማን ከማን ጋር
እንደሆነም ተወሰነ የኔም ሚዜ መጥቶ አጠገቤ ቁጭ ብሎ ማውራት ጀመርን የኔ ሚዜ እንደ አጋጣሚ ሆኖ የተሻለ መልክና ቁመና ያለው ነበር
ሌሎቹ ሴት ሚዜዎች ረዱ አፈስሽ አሉኝ ኧረ እኔ ለኔ የተመዘነውን ካፈስኩ ቆይቻለሁ አልኳቸው በዚህ መሀል ለአብሪሽ ስልክ እንዳልደወልኩ ትዝ ሲለኝ ስልኬን ሳየው 12 ሚስኮል አገኘሁ አብሪሽ ደውሎ አላየሁትም ነበር ዘወር ብዬ ደወልኩለት አንዴ እንደጠራ አነሳውና "አንቺ እብድ ቢያንስ ገባሁ አይባልም አለኝ" በጣም ይቅርታ ተዋከብኩና ረሳውት አልኩት። አሁን ያለንበትን
ሁሉንም ነገርኩትና ሩም ስገባ እደውልልሀለው አልኩት ስመለስ የኔ ሚዜ ዞር ብሎ ስልክ ማውራት እኮ ባለትዳር ነኝ ማለት ነው አለኝ አልተሳሳትክም አልኩት ይቺ እጅሽ ጨክና ፈረመች አለኝ አይ እጄስ ገና አልፈረመችም ልቤ ነው የፈረመው አልኩት እሺ ለኔ የእጁን ፈርሚልኝ አለኝ ልብ የሌለበት የእጅ ፊርማ ምን ያደርግልሀል አልኩት ኧረረ አልቻልኩሽም አለኝና ተነስተን ወደ
ሌሎቹ ሚዜዎች ተቀላቀልን እየተጫወትን ድንገት ሚዜዬን ሳየው እያየኝ ነው ፈራሁት ሌሎቹ ሚዜዎች በጣም ተግባብተዋል ተጫወትን እንደጨረስን ለሊት ወደ ፀጉር ቤት ስለምንሄድ እንግባ ተብሎ ወደ ሩም ለመሄድ ተነሳን ሁላችንም በተለያየ ሰአት ስለደረስን የተለያየ ቦታ ነበር አልጋ የያዝነው የኔ ሚዜና አንድ ሌላ ሚዜ መኪና ይዘው ስለነበር ሊሽኙን ተነሱ እኔንና ሌላ ሶስት ሚዜዎች የኔ ሚዜ ሸኝን ሌሎቹን መጀመሪያ ሸኝናቸው መጨረሻ ላይ እኔን አደረሰኝና አመሰግናለሁ የነገ ሰው ይበለን ብዬው ወረድኩኝ ግባ አትይኝም አለኝ ወዴት አልኩት ወደ ልብሽ አለኝ ውይ ትርፍ አንጭንም አልኩትና ወደ ሩም ገባሁ እንደ ገባሁ ለአብሪሽ ስልክ ደወልኩ በፍቅር ጋደም ብዬ እያወራሁት እያለ ናፍቀሺኛል አለኝ እኔ ደሞ ርበህኛል አልኩት በዚህ መሀል የክፍሌ በር ተከፈተ በጣም ደነገጥኩ ስዞር ይበልጥ የሚያስፈራ ነገር አየሁ "ሚዜው ቆሟል
ምን ታደርጋለህ እዚህ አልኩት ስልኬን አልጋው ላይ ወርውሬ ተነሳሁ ልብሽ ባይፈቀድልኝ ክፍልሽ ልግባ ብዬ እኮ ነው አለኝ በጣም ተናደድኩ...ውይ በጣም ትቀልዳለህ አልኩት ቀና ብዬ ሳየው ወደኔ እየመጣ ነው በዛ ላይ በጣም ሞቅ ብሎታል
በጣም ፈራሁና በዚህ ሰአት ጉልበት ሳይሆን ብልጠት አንደሚያስፈልገኝ አሰብኩኝ ወዲያው አንተ ምን ሆነህ ነው በአንድ ቀን ታመረዋለህ
እንዴ ነገም እኮ የኔና ያንተ ነው ቢያንስ እንድግደረደር እንኳን ዛሬን ስጠኝ ነገ ብትን ብለን አብረን እናድራለን አልኩት እስቲ ሙት በይኝ አለኝ እኔ ልሙት ብዬ ማልኩለት እሺ ብሎኝ ከክፍሌ ወጣ እኔም ኡፈይ አልኩኝና በሬን ቆልፌ አልጋ ላይ የወረወርኩትን ስልኬን አነሳሁት አልተዘጋም ነበር ሄሎ አብሪሽ ስለው… ይቀጥላል
🌹💐ዝገት ከከሌጋ💐🌺🙃
◉◌◍JOIN
👇👇👇👇👇👇
💝
@hammerawi💔
💗
@hammerawi ♥️
💞
@hammerawi💘
💖
@hammerawi💖