Фильтр публикаций


ሶላት አለን-ነብይ የማውረድ ትሩፋት

قال صلى الله عليه وسلم « مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلاَةً صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا »

❥ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
❥ እንዳሉት‘መን ሶላ ዓለየ ሶላተን ሶለልሏሁ ዐለይሂ ቢሃ ዐሸራ’ ‹‹በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ አስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል››

وقال صلى الله عليه وسلم : « لاَ تَجْعَلُوْا قَبْرِي عِيْدًا وَصَلُّوْا عَلَيَّ؛ فَإِنَّ صَلاَتَكَ تَبْلُغُنِي حَيْثُ كُنْتُمْ »

ሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዳሉት: ‘‹‹መቃብሬን የባዕል ማዕከል አታድርጉት ፡፡በኔ ላይም ሶለዋት አውርዱ፡፡ የትም ሆናቸሁ ሶለዋት ብታወርዱ ይደርሰኛል፡፡›› ’

وقال صلى الله عليه وسلم : « الْبَخِيْلُ مَنْ ذُكِرْتُ عِنْدَهُ فَلَمْ يُصَلِّ عَلَيَّ »

እንዲህ ሲሉም ተናግረዋል፡-‹‹ስስታም ማለት ከርሱ ዘንድ እኔ እየተወሳሁ በኔ ላይ ሶለዋት ያላወረደ ነው፡፡››’

وقال صلى الله عليه وسلم : « إِنَّ لِلَّهِ مَلاَئِكَةً سَيَّاحِيْنَ فِي اْلأَرْضِ يُبَلِّغُوْنِي مِنْ أُمَّتِي السَّلاَمَ »

እንዲህ ሲሉም ተናግረዋል: “ለአላህ ተጓዥ መላኢኮች አሉት፡፡ ምድር ላይ ከኡመቴ የሚላክልኝን ሰላምታ ለኔ ያደርሳሉ፡፡”

وقال صلى الله عليه وسلم : « مَا مِنْ أَحَدٍ يُسَلِّمُ عَلَيَّ إِلاَّ رَدَّ اللهُ عَلَيَّ رُوْحِيَ حَتَّى أَرُدَّ عَلَيْهِ السَّلاَمَ »

صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፡: “አንድ ሰው ሰላምታ ሲልክልኝ አላህ ነፍስ ይዝራብኝና ምላሽ እሰጠዋለሁ፡፡.”
#ቴሌግራም_ቻናላችንን_join_ብለው ይግቡ
https://t.me/joinchat/AAAAAEgolEJ2Rl3gT_bmuA

Facebook peg link
https://www.facebook.com/323366755034719?referrer=whatsapp


قال صلى الله عليه وسلم-:
"من صام رمضان ثم أتبعه بست من شوال كان كصيام الدهر"
رواه مسلم في كتاب الصيام بشرح النووي

🛑 የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ይላሉ

📌 «ረመዷንን ፆሞ ከሸዋል ስድስት ቀናትን አስከትሎ የፆመ አመቱን እንደፆመ ይቆጠርለታል»

ሙስሊም ዘግበውታል


#ሸዋል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ሚሽነሪዎች የማያውቁትን ከመጠየቅ ይልቅ፦ “ዘካህ ከመቶ 2.5% ስጡ የሚል መረጃ የለም፣ ሪባ ማለት አራጣ ማለት እንጂ ወለድ ማለት አይደለም፥ የቁርኣን አወራረድ ሁለት አይነት ነው የሚል መረጃ ከቁርኣንም ከሐዲስም መረጃ የለም” እያሉ ዲስኩራቸውን ሲደሶክሩ ነበር። ለእናንዳንዱ አርስት ከቁርኣና ከሐዲስ ከዚህ ቀደም ምላሽ ሰተናል። ዛሬ ደግሞ፦ “ሸዋልን ጹሙ! የሚል ቁርኣን ላይ የለም” እያሉ ይደሶክራሉ። ሚሽነሪዎች ሆይ! ጮቤ ረግጣችሁ አንባጒሮ አትፍጠሩ። ተረጋጉ! የጅብ ችኩል አትሁኑ! በሰላና በሰከነ መንፈስ ጠይቁ መልስ ይሰጣችኃል። ከሆያ ሆዬ ወደ አንቺ ሆዬ ትንሽ እንኳን እደጉ።
የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ዐሥራ ሁለት ወር ነው፥ እነዚህም፦
1ኛ ወር ሙሐረም
2ኛ ወር ሰፈር
3ኛ ወር ረቢዑል-አወል
4ኛ ወር ረቢዑ-ሣኒ
5ኛ ወር ጀማዱል-አወል
6ኛ ወር ጀማዱ-ሣኒ
7ኛ ወር ረጀብ
8ኛ ወር ሻዕባን
9ኛ ወር ረመዷን
10ኛ ወር ሸዋል
11ኛ ወር ዙል-ቀዒዳህ
12ኛ ወር ዙል-ሒጃህ ናቸው፦
9፥36 *የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነርሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው*፡፡ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ

ከእነዚህ አስራ ሁለት ወራት አንዱ 10ኛ ወር “ሸዋል” ነው፥ “ሸዋል” شَوَّال ማለት “ማንሳት” ወይም “መሸከም” ማለት ሲሆን የወር ስም ነው። ነቢያችን”ﷺ” እንድናደርገው ሙስተሐብ አድርገው ከሰጡት ሱና መካከል ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን መጾም ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 78
አቢ አዩብ እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *ማንም ረመዷንን የጾመ ከዚያም ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ ዋጋው ዓመቱን ሙሉ እንደጾመ ነው”*። عَنْ أَبِي أَيُّوبَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ فَذَلِكَ صِيَامُ الدَّهْرِ ‏

የረመዷን ሰላሳ ቀን እና የሸዋል ስድስት ቀን ጾም ጾመን ዓመት እንደጾምን የሚያስቆጥርበትን ስሌት ማወቅ ይቻላል። አምላካችን አላህ አንድ መልካም ሥራ ምንዳው አሥር እጥፍ እንደሆነ በቅዱስ ቃሉ ነግሮናል፦
6፥160 *”በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት”*፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

ስለዚህ አንድ መልካም ሥራ አሥር ብጤዎች ካሉት የረመዷን አንድ ወር መጾም የአሥር ወር ምንዳ አለው። 1×10=10 ወር ይሆናል። እንዲሁ የሸዋል ስድስት ቀን መጾም የስድሳ ቀን ምንዳ አለው፥ ስድስት ቀናት በአሥር እጥፍ ስድሳ ቀን ነውና፥ 6×10=60 ቀን ወይም 2 ወር ይሆናል። ሲጠቀለል የረመዷን የአሥር ወር ምንዳ እና የሸዋል ሁለት ወር ምንዳ 12 ወር ይሆናል፥ 10+2=12 ወር ይሆናል። አንድ ዓመት ደግሞ 12 ወር መሆኑ እሙን ነው። አሊያም ሠላሳ የረመዳን ቀን እና ስድስት የሸዋል ቀን በአስር ምንዳ ሲባዛ 360 ቀናት ይሆናሉ፥ 36×10= 360 ይሆናል። አንድ ዓመት ደግሞ በጸሐይ አቆጣጠር 360 ቀናት መሆኑ ቅቡል ነው።
አምላካችን አላህ በተከበረ ቃሉ፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት” ይለናል፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ስለዚህ ኢሥላም ሰው ሰራሽ ሕግና ሥርዓት ሳይሆን ዐቂደቱ አር-ረባንያህ ነው። ይህንን ስንል አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ የሆነ ስሑትና መሪር የቡና ወሬ ይዘን ሳይሆን ቁርኣንና ሐዲስን ያማከለ ስሙርና ጥዑም ማስረጃ ይዘን ነው።

✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
@islamic_knowledg


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


‏الله أكبر الله أكبر الله أكبر
‏لا إله إلا الله
‏الله أكبر الله أكبر
‏ولله الحمد

‏الله أكبر الله أكبر الله أكبر
‏لا إله إلا الله
‏الله أكبر الله أكبر
‏ولله الحمد

‏الله أكبر الله أكبر الله أكبر
‏لا إله إلا الله
‏الله أكبر الله أكبر
‏ولله الحمــد...


🌺ተክቢራ እናብዛ🌺
@islamic_knowledg
@islamic_knowledg
@islamic_knowledg




🛑 «በዒድ አልፊጥር ግዜ ወደ ሰላት ከመውጣቱ በፊት ተምር ዊትር ዊትር (3,5,7…) እያደረጉ በልቶ መውጣቱ ሱና ነው።»

📌 ሸይኽ ዑሰይሚን – መጅሙዑል ፈታዋ (16/ 234)


ዒድ ሙባረክ!
እንኳን ለ1442ኛው ለዒድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
ተቀበለላሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊኻል አዕማል!


اللهم تقبل صيامنا وصلاتنا
اللهم تقبل منا ختم قرآنك الكريم
اللهم تقبل أعمالنا الصالحة
اللهم إستجب دعائنا
اللهم إغفر ذنوبنا وإعفو عنا
آمين 🖤

#رمضان_٣٠

የመጨረሻዋ ቀን 🥰

┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄


http://chng.it/BYRjJwTJQL


ይህን ፒቲሺን በመሙላት የእስራዔልን ወረራ በመቃወም ከፍልስጤም ወንድሞቻችን ጎን እንቁም‼

አሁን 406, 800 ደርሷል። የሚያስፈልገው 500,000 ፊርማ ነው።
ለሌሎችም ሼር እናድርገው!
👇👇👇
http://chng.it/RpmK5yWXDd


#Eid
=====
✍ዒድ ብሎ ማለት በየአመቱ አዲስ ደስታን ይዞ የሚመለስ ከመሆኑ አንፃር እና እንዲሁም «ዓደ» ተመለሰ ከሚለው ቃል የአረበኛ ቃል የተወሰደ መሆኑን ፉቃሀዎች ያስቀምጣሉ።
||
✔️ ይሁን እንጅ ልብ ልንልን የሚገባው ነገር ዒድ ቂያማ እስቂቆም ተመላልሶ የሚመጣ ቢሆንም እኛ ግን የሚቀጥለውን ለመድረስ ምንም ዎስትና እንደሌለንና ያለንን ጊዜ ኸይር ላይ እንድናውለው አስታዉሳለሁ።


✔️የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) መዲና ከተማ ሲመጡ የመዲና ሰዎች በመሀይምነት ዘመን ደስታቸውን የሚገልፁባቸው፣ የሚጫወቱባቸው ሁለት በዓላት ነበሩዋቸው፣ ረሱልም ይህንን ባዩ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ:-
« እነዚህ ቀኖች ምንድን ናቸው አሉ………

በእነዚህ በሁለቱ ምትክ ከእነርሱ በተሸሉ ሁለት በዓላትን ቀይየረላችሁ፤ እነሱም የኢደል ፈጥር እና የኢደል አድሀ በዓላት ናቸው»፡፡
📒አቡዳውድ እና አህመድ ዘግበውታል
||
عَنْ أَنَسٍ-رضي الله عنه- قَالَ: قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ -صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ- الْمَدِينَةَ، وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ:(مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ؟) قَالُوا: كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ، فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ -صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ-: (إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الْأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ)

📒رواه أبو داود. واحمد


ዒድ‼️
===
✔️የዒደልል ፊጥር ቀን ጧት ላይ ወደ መስገጃው ሜዳ ስንወጣ ቴምርን በልቶ መውጣት ሱና ነው።

✔️የዒደል አድሐ ቀን ግን እርድ ሚያርድ ሰው ከሆነ ሳይበላ እንድወጣ ነው የታዘዘው።


وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَٰنِ إِلَّا مَا سَعَىٰ

ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም፡፡
وَأَنَّ سَعْيَهُۥ سَوْفَ يُرَىٰ

ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል፡፡

ثُمَّ يُجْزَىٰهُ ٱلْجَزَآءَ ٱلْأَوْفَىٰ

ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል፡፡
وَأَنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلْمُنتَهَىٰ

መጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡


●وقت إخراج زكاة الفطر●

#የዘካ አልፍጥር መስጫ ጊዜ🌿

ﺍﻟﻮﺍﺟﺐ ﺇﺧﺮﺍﺝ ﺯﻛﺎﺓ ﺍﻟﻔِﻄﺮ ﻗﺒﻞ ﺻﻼﺓ ﺍﻟﻌﻴﺪ، ﻭﻻ ﻳَﺠﻮﺯ ﺗﺄﺧﻴﺮﻫﺎ ﺇﻟﻰ ﻣﺎ ﺑﻌﺪ ﺍﻟﺼﻼﺓ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﺼﺤﻴﺢ ﻣﻦ ﻗﻮﻟﻲ ﺍﻟﻌﻠﻤﺎﺀ؛ ﻟﺤﺪﻳﺚ ﺍﺑﻦ ﻋﻤﺮ - ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﻤﺎ - ﺃﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ - ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ :- "ﺃﻣﺮ ﺑﺰﻛﺎﺓ ﺍﻟﻔِﻄﺮ
ﺃﻥ ﺗﺆﺩَّﻯ ﻗﺒﻞ ﺧﺮﻭﺝ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﺼﻼﺓ "؛ ﻣﺘﻔﻖ ﻋﻠﻴﻪ‏

ﻭﻳﺠﻮﺯ ﺇﺧﺮﺍﺟﻬﺎ ﻗﺒﻞ ﺍﻟﻌﻴﺪ ﺑﻴﻮﻡ ﺃﻭ ﻳﻮﻣﻴﻦ؛ ﻟﻤﺎ ﺭﻭﻯ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ﻋﻦ ﻧﺎﻓﻊ ﻣﻮﻟﻰ ﺍﺑﻦ ﻋﻤﺮ - ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﻤﺎ - ﻗﺎﻝ: ﻛﺎﻥ ﺍﺑﻦ ﻋﻤﺮ ﻳُﻌﻄﻲ ﻋﻦ ﺍﻟﺼﻐﻴﺮ ﻭﺍﻟﻜﺒﻴﺮ، ﺣﺘﻰ ﻭﺇﻥ ﻛﺎﻥ ﻳﻌﻄﻲ ﻋﻦ ﺑَﻨِﻲَّ، ﻭﻛﺎﻥ ﻳُﻌﻄﻴﻬﺎ ﺍﻟﺬﻳﻦ ﻳﻘﺒﻠﻮﻧﻬﺎ، ﻭﻛﺎﻧﻮﺍ ﻳﻌﻄﻮﻥ ﻗﺒﻞ ﺍﻟﻔﻄﺮ ﺑﻴﻮﻡ ﺃﻭ ﻳﻮﻣﻴﻦ ‏

ﻗﺎﻝ ﺷﻴﺨﻨﺎ ﺍﻟﻌﻼﻣﺔ ﺍﺑﻦ ﺑﺎﺯ - ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ :-
ﻻ ﻣﺎﻧﻊ ﻣﻦ ﺇﺧﺮﺍﺟِﻬﺎ ﻓﻲ ﺍﻟﻴﻮﻡ ﺍﻟﺜﺎﻣﻦ ﻭﺍﻟﻌﺸﺮﻳﻦ ﻭﺍﻟﺘﺎﺳﻊ ﻭﺍﻟﻌﺸﺮﻳﻦ
ﻭﺍﻟﺜﻼﺛﻴﻦ ﻭﻟﻴﻠﺔ ﺍﻟﻌﻴﺪ، ﻭﺻﺒﺎﺡ ﺍﻟﻌﻴﺪ ﻗﺒﻞ ﺍﻟﺼﻼﺓ؛ ﻷﻥ ﺍﻟﺸﻬﺮ ﻳﻜﻮﻥ ﺛﻼﺛﻴﻦ،
ﻭﻳﻜﻮﻥ ﺗﺴﻌﺔ ﻭﻋﺸﺮﻳﻦ، ﻛﻤﺎ ﺻﺤَّﺖ ﺑﺬﻟﻚ ﺍﻷﺣﺎﺩﻳﺚ ﻋﻦ ﺍﻟﻨﺒﻲ - ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ
ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ؛ ﺍﻫـ‏

➞▪ትክክለኛውና በላጩ የዘካ አልፊጥር መስጫ ወቅት የኢድ አልፊጥር እለት ከሶላት በፊት ነው!!

➞▪ኢማሙ ቡኻሪይ በዘገቡት ሀዲስ አብደላ ኢብኑ ኡመር ነብዩ ﷺ ዘካ አልፊጥርን የኢድ እለት ሰዎች ወደ ኢድ ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድንሰጥ አዘዙን!!

➞▪ይሁን እንጂ ከኢድ አልፊጥር እለት አንድ ቀንና ሁለት ቀን አስቀድሞ የሚቻል ሲሆን የመጨረሻው ማብቂያው ግን ከዒድ ሰላት በፊት መሆን አለበት!!

➞▪ኢማሙ ቡኻሪይ በዘገቡት ሀዲስ የአብደላ ኢብኑ ኡመር የቀድሞ ባሪያቸው የነበሩ ናፊዕ ኢብኑ ኡመር ዘካት አልፊጥር ከኢዱልፊጥር አንድና ሁለት ቀን አስቀድመው ይሰጡ ነበር!!

➞▪አልሼይኽ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ ዘካተልፊጥርን በረመዳን ሀያስምተኛው እለት ሀያዘጠነኛው እለት ረመዳን ሙሉ ከሆነ ሰላሳኛው!!

➞▪ነገ ዒድ ሊሆን ማታውን እና የዒዱን ቀን እስከ ሶላት በፊት ድረስ ከመስጠት የሚከለክል ማስረጃ ስለሌለ አዳዴ ወሩ ሙሉ እሚሆንበት አለ አንዳዴ ደግም በሀያዘጠነኛው ይጠናቀቃል ከለይ በተጠቀሱት ግዜ ውስጥ ዘካተል ፊጥርን መስጠት ይቻላል!!

✍🏻https://t.me/knawoledg


የ አላህ ፍልስጤም በቃሽ በላት ያ ኢላሒ
መስጂደል አቅሳን አንተው ጠብቃት🤲🤲🤲🤲🤲




አላህ እንዲህ ብሎናል፦

(إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا)

«ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡»
[አሽ-ሸርሕ: 6]


#ጨረቃ_ባለመታየቷ_ዒዱ_ሀሙስ_ነው።


🔸የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"በረመዳን የመጨረሻዋ ለሊት ለይለተልቀድርን ተጠባበቁ።"
📚ሰሒሁል ጃሚዕ (1234)


በሰው ልጅ ላይ ሶስት አስቸጋሪ ቀኖች

➲ሱፍያን ኢብኑ ዑየይና ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላል :-

➲የሰው ልጅ ሶስት ቦታ ላይ በጣም ይቦዝናል

① የተወለደ ቀን ወደ ማያውቀው ሀገር ሲወጣ

② የሞተ ቀን አምሳያቸውን አይቶ ከማያውቃቸው ሰዎች ጋር ጎረቤት ሆኖ ሲያድር

③ በሚቀሰቀስበት ቀን አይቶ የማያውቀው አይነት ክስተት ሲመለከት

➲አላህ ለነብይላሂ የህያ እነዚህን ሶስት ቀኖች አስመልክቶ እንዲህ አላቸው :-

[ وَسَلَامٌ عَلَيْهِ يَوْمَ وُلِدَ وَيَوْمَ يَمُوتُ وَيَوْمَ يُبْعَثُ حَيًّا ]

➲"በሚወለድበት ቀን በሚሞትበት ቀን ህያው ሆኖ በሚቀሰቀስበት ቀን ሰላም በርሱ ላይ ይሁን "

ሱረቱል መርየም : 15

አልጃሚዕ ሊአህካሚል ቁርአን ( 13/27 )
https://t.me/joinchat/AAAAAEgolEJ2Rl3gT_bmuA

Facebook peg link
https://www.facebook.com/323366755034719?referrer=whatsapp

Показано 20 последних публикаций.

2 042

подписчиков
Статистика канала