+ 14 ሠዓሊያንን ያሳተፈ የሥዕል ዐውደ ርእይ ተካሔደ +
/አዲስ አበባ : ጥር 02 2014 ዓ.ም./
ጃንደረባው ሚዲያ
የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ከጥር 1-2 2014 ዓ.ም. ያዘጋጀው የሥዕል ዐውደ ርእይ በርካታ ጎብኚዎችን በማስተናገድ በድምቀት ተካሔደ::
ዐሥራ አራት ሠዓሊያንን ባሳተፈው በዚህ ዐውደ ርእይ ላይ የሸራ ሥዕላት : የቆዳ ሥዕላት : የብራና ሥዕላት : የዲጂታል አርት እና የስትሪንግ አርት ሥዕላት : የወረቀት የእርሳስ ሥዕላት : የእንጨት ላይ ሥዕላት ለእይታ ቀርበዋል::
በዐውደ ርእዩ ላይ በክብር ሠዓሊነት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የለንደን ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጥልቅ አባታዊ መልዕክቶችን የያዙ ውብ ሥራዎቻቸው ለጉብኝት ቀርበዋል::
#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው?