እነዚህ የግብጽ ጋዜጦች ወሸት ዘግበው መሆን አለበት። ካላበዱ በቀር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምንም ምክንያት የግድቡን ሙሌት ማስጀመር እንዲዘገይ የሚስማሙ አይመስለኝም።በአሁኑ ሰዓት የግብፅ ብቸኛ ዓላማ ፍትሃዊ ስምምነት ላይ መድረስ ሳይሆን እስከ ነሃሴ ድረስ የግድቡ ሙሌት እንዳይጀምር ማዘግየት ነው። ያው ከነሃሴ በኋላ የዝናብ ወቅት ስለማይሆን እንሙላ ብንልም ይህን ማድረግ እንደማንችል በደንብ ያውቃሉ። ቀጣይ ዓመት ሌላ የዝናብ ወቅት እስኪመጣ ደግሞ እነሱ ሌላ ዘድ ቀይሰው ይጠብቁናል። ስለዚህ የተሻለውና ብቸኛው አማራጭ የግድቡን በቶሎ ሙሌት መጀመር ነው። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረት በኩልም ሆነ በሌላ አደራዳሪ አካል ይካሄድ የውሃ ሙሌቱን ማዘግየት እንደቅደመ ሁኔታ የሚያስቀምጥ ከሆነ የምንጎዳው እኛ እንጂ ግብፅ የምትፈልገውን አገኘች ማለት ነው። በዚህ ላይ የግብፅ ሚዲያዎች እያወጡ ያሉትን ነገር ላይ አስቸኳይ ማስተባበያ ከኛ ማንግስት መሰጠት አለበት።