በአሜሪካ ሴነት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባላተ የሆኑት ሰናተር ኮሪ ቡከር እና ክሪስ ኩን ለሀገራቸው የገንዘብ ሚኒስቴር በጻፉት ደብዳቤ በግድቡ ድርድር ላይ ሀገራቸው ወገንተኝነትን ማሳያት እንደሌለባት አሳስበዋል። ሁለቱም ሴናተሮች ከፈተኛ ጫና ማሳደር የሚችሉ ናቸው። ቡከር በቅርቡ ለዲሞክራት ፓርቲ የፕረዚደንት እጩነት ሲወዳደር የነበረ ሲሆን በሚዲያዎች ላይ በመናገር ጫና በመፍጠር የሚታወቅ ወጣት ትቁር እንደራሴ ነው። ክሪስ ኩን ደግሞ በሴኔት ውስጥ ወሳኝ በሚባሉ እንደ በጀት፣ ውጭ ጉዳይ እና ፍትት ንኡስ ኮሚቴዎች ውስጥ አባል ነው።