አንድ ማለዳ ላይ፥
እንደወትሮው ሆና፥
ፀሀይ ስትወጣ፥
ወጋገን ቀስቅሶት፥
ከእንቅልፉ ሲነቃ፥
የነገረው ይመስል፥
የለሊቱ መልአክ፥
የህልሙ አለቃ፥
እንደሰማ ነገር፥
አንድ ትልቅ ሚስጥር፥
ፊቱ እያበራ፥
"ለካ"፥ብሎ ጮኋል
አላያቸውም ኖሯል
ሲጮህ ሰምተው ድምፁን፥
እናቱ ቆመዋል
"ለካ ሰው ነበረች፥
ከእኛ ያልተለየች፥
ታዲያ ምን ጋርዶኝ ነበረ፥
ስክብ ስቆልላት የነበረ፥
ተገርሞ እጁን ከአፉ ጫነ"፥
"እልል" አሉ እናቱ
አቀለጡት ቤቱን ፥
"ልጄ ተመለሰ" እያሉ፥
ወደላይ አንጋጠው፥
"ምን ይሳንሀል" እያሉ፥
✍ናኒ
https://t.me/justhoughtsss
እንደወትሮው ሆና፥
ፀሀይ ስትወጣ፥
ወጋገን ቀስቅሶት፥
ከእንቅልፉ ሲነቃ፥
የነገረው ይመስል፥
የለሊቱ መልአክ፥
የህልሙ አለቃ፥
እንደሰማ ነገር፥
አንድ ትልቅ ሚስጥር፥
ፊቱ እያበራ፥
"ለካ"፥ብሎ ጮኋል
አላያቸውም ኖሯል
ሲጮህ ሰምተው ድምፁን፥
እናቱ ቆመዋል
"ለካ ሰው ነበረች፥
ከእኛ ያልተለየች፥
ታዲያ ምን ጋርዶኝ ነበረ፥
ስክብ ስቆልላት የነበረ፥
ተገርሞ እጁን ከአፉ ጫነ"፥
"እልል" አሉ እናቱ
አቀለጡት ቤቱን ፥
"ልጄ ተመለሰ" እያሉ፥
ወደላይ አንጋጠው፥
"ምን ይሳንሀል" እያሉ፥
✍ናኒ
https://t.me/justhoughtsss