ኪነ ጥበብ ብቻ


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ የሚገኝበት ቻናል ነው፡፡
ግጥሞች
መነባነቦች
ከዚያም ከዚህ
እናስተዋውቃችሁ
፡ ጭውውት
ድራማ.... ወዘተ
ለሀሳብ @ty1921 ይጠቀሙ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


++ ኪነጥበብ - በልሃ ልበልሃ !!


ሁለት ሰዎች ከተለያየ ቦታ ሲመጡ መድረክ ላይ ይታያሉ የሁለቱም ሰዎች ማለፊያ መንገድ አንድ በመሆኑ መንገዱ አጠገብ ያለው ድልድይ ደግሞ የሚያሳልፈው አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ በዚያ አገር ባህል እና ወግ ደግሞ ሁለትሰዎች እዚያ ድልድይ ላይ ከተገናኙ በልሃ ልበልሃ ተባብለው ያሸነፈው ሰው በቅሚያ ያልፋል፡፡ ይሕም ነገር አሁን ተከሰተ፡፡


እንግዲህ ወንድሜ ባገሩ ወግና ባህል
በልሃ ልበልሃ እንባባል ቀዳሚው እንዲለይ

ምን ገዶኝ ወንድም ጃል
የቀየው ባህልና ወግ አይደል
ታዲያ ቀዳሚው እንዲለይ
በዕጣ መጣጣል ብንለያይ
እኔ ግን በእድሜም ከፍ ስለምትለኝ
አንተ ብትቀድም ነው የሚበጀኝ

ስላከበርከኝ ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው
እንግዲህ በልሃ ልበልሃ ልጀምረው
በልሃ ልበልሃ
ካልመለስክ ልቅጣሃ

በላሃ በለኛ
ካልመለስኩ ቅጣኛ

ከሲና በርሃ ተነስቶ
ሃመልማል ሳይቃጠል አይቶ
ምንም አፉ ጎልዳፋ ቢሆን
እግዚአብሔር ለክብሩ መገለጫ ያሳየን
በዘጠኝ ተአምራት በአስረኛ ሞተ በኩር
የአምላክን ሕዝብ ከፈርዖን አገዛዝ ያስጣለ በተአምር
የስራኤልን ሕዝብ የመራ
ማነው ስሙን ጥራ?

እሱንማ መች አጥቼው
እናቱ ሸሽጋ በሳጥን ያኖረችው
የፈርዖን ልጅ አግኝታ በፍቅር ያቀፈችው
ያ መልከ መልካም እንቦቀቅላ
ፍትፍቱን ትቶ እሳቱን የበላ
የአምስት መፅሐፍ ፀሐፊ የተባለው
ሊቁ ታላቁ አባት ሊቀ ነቢያት ሙሴ ነው፡፡

ትክክል ብልሃል መልሱንም አውቀሃል
በል ተራው ያንተ ነው ጥያቄህ የታል



በልሃ ልበልሃ
ካላወክ ልቅጣሃ

በልሃ በለኛ
ካላወኩ ቅጣኛ

አርጢሞስ አምላክ ሳትሆን ተቀራፂ ምስል
ባንዴ የምትፈርስ በእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል
ብሎ ባመሰስተማር ለእስር የበቃሁ
በፈላም ውሃ ውስጥ የተቀቀለም ነው
ይሔም አልበቃውም ንጉሱም ጨካኝ ነው
በፍጥሞ ደሴት ውስጥ በግዞት ያለ ነው
በዛ ውስጥ እያለ አንድ ነገር ሰርቷል
የሰራሁስ ስራ? ስሙስ ማን ይባላል?

ይህንን ካላወኩ ምኑን አወኩ ሊባል
ባጭሩ ልንገርህ ኤሊያስም አይደል

ፍፁም ስህተት ነው መልሱም ይህ አይደል
ቅጣትህን ተቀበል

ይሔው ለቅጣቴ ጎንበስ ቀና ብዬ
ባለማወቄማ ልቀጣ ጌታዬ

አቡነ ዘበሰማያት ይደገም ግዕዙ
እሱን ካላወቁ ሌላ ይታዘዙ

ይሔው ልጀምረው ያደኩበትን
ከየኔታ እግር ስር የተማርኩትን
አቡነ ሰበሰማያት …….

በትክክል ነው ግዕዙንም ያልከው
የጥያቄዬን መልስ ስማኝ ልናገር ነው
በፍጥሞ ደሴት ውስጥ በግዞት ተቀምጦ
ራዕዩንም ፃፈው ብራናውን ገልጦ
የዚህ ታላቅ አባት ስሙም ክብር ያለው
ቅዱስ ዮሐንስ ነው ደቀ መዝሙሩም ነው
እንግዲህ አሁንም ጠያቂው እኜ ነኝ
በልሃ ልበልሃ
ካላወክ ልቅጣሃ

በልሃ በለኛ
ካላወኩ ቅጣኛ

በጎጃም ሃገር በዳማ ሥላሴ
አንድ ፀሐይ ወጥታ ታዛዥ ለሥላሴ
በ7 አመቱ ብርሃኑን አጥቶ
ለአምስት አመት ቆየ በጸሎት በርትቶ
ጌታ አምላካችን በአካል ተገልፃል
አዳኝ በመሆንህ ዓይንህ ይስራ ተመልሶ
ይሔንንም ሰጠው 12 አክናፍ
ዓለምን ይዞራል በመፍጠን
ታዲያ ይህ አባት ስሙን በል ጥራልኝ
እውቀትህን ገልጸህ ለይተህ አሳየኝ

ማንም አይረሳቸው አባ ዘርዐብሩክ
ሐይን ያቆሙ ታላቅ አባት ናቸው
ለወንዝ መፅሐፍን ባደራ የሰጡ
በጸሎት በስግደት የኖሩ ሳይወጡ
የዞንዶ ጥርስ ሳይቀር አስታርቀው ሲቆጥሩ
እንዴት ይረሳሉ እኝህ ታላቅ አባት
ይደርብን ዘውትር የእሳቸው በረከት

በእውነት ልክ ነው ፍፁም የለው ስህተት
እንዴት ይረሳሉ እኝህ ታላቅ አባት

በል እንግዲህ ያሸነፍኩ እኔ ነኝ
ድልድዩን ልቀቅ በሰላም አሻግረኝ

ይሔው ለቀኩልህ በሰላም ተሸገር
ካሸነፍከኝማ ላንተ ይሁን ክብር
ወጉ ማዕረጉን አልጥስ
አንተ እኮ ነህ ንጉስ

ወጉን ማዕረጉን የሚቀድመው አለ
ማክበር መከባበር የኢትዮጵያውያን ወጋቸው አይደለ
አንተም እኮመ እኔን በእድሜዬ ሰትበልጠኝ
በጥያቄው ሳይሆን በእድሜዬ አሸነፍከኝ


ሁለቱም ሰዎች ተሳስመው ተመራርቀው በእድሜ የሚበልጠው ሰውዬ ቀድሞ ይሻገራል ቀጥሎ ተሸግሮ ወጥቶ ይሔዳል።
@kinexebebe


ከዘማዊቷ አንደበት
____________
በሰው እጅ ወድቄ በደካማው ጎኔ
ይገባታል ስባል ሞትና ኩነኔ
በፊትህ ለመቆም ሳይገባኝ ለኔ
ባንተ ፊት አቁመው አይሁድ እንዲህ ሲሉህ
መምህር ስለዚች ሴት አንተ ምን ትላለህ
ስትዘሙት አግኝተን ይዘናት መጥተናል
ሙሴ በኦሪቱ በደንጋይ ተወግራ እንድትሞት አዞናል
ብለው ሲጠይቁህ አይሁድ ሊፈትኑህ
አትወገር ብትል ህጋችን አፍርሷል
ትወገርም ብትል እንዴት ይጨክናል
ለሰው ሞት አያዝንም? የእግዜር ልጅ ነኝ ይላል
ለማለት አስበው ወዳንተ ሲመጡ
በዚህ ከባድ ሐሳብ አንተን መልስ ሊአሳጡ
ከናንተ መካከል ኀጢአት የሌለበት
መጀመሪያ አንስቶ ደንጋይ ይጣልባት
ብለህ ስትናገር ስትፈርድ ስለእውነት
ከአይሁድ መካከል ማን ነበር ካንተ ፊት
ቁሞ የተገኘ ኀጢአትን ያልሠራት
ባንቺ የሚፈርዱት ሰዎች ወዴት አሉ
ብለህ ስጠይቀኝ አወቅሁ እንደሌሉ
አይሁድ ሲዘጋጁ በኔ ላይ ሊፈርዱ
ዘማ ናት እያሉ እኔን ሊያዋርዱ
ቃላቸውን ሰምተህ መጻፍ ስትጀምር ያንዱን ኀጢአት ባንዱ
ትንሹም ትልቁም እየወጡ ሄዱ
አቤቱ ጌታየ እኔ ግን ከንቱ ነኝ
ኀጢአቴን ሰውረህ ከሞት አድነኸኝ
ኢየሱስ የት አለ? ብለው ሲጠይቁኝ
በጣቴ ጠቁሜ ለአይሁድ ያሳየሁኝ
መልካም ውለታህን መመለስ ያልቻልኩኝ
ወርቀ ደምህ ዋጅቶኝ በደምህ ስትገዛኝ
ስለመልካም ሥራህ ክፉ የመለስኩኝ
ከንቱ ነኝ ከንቱ ነኝ የከንቱ ከንቱ ነኝ
የአንተን ውለታ መመለስ ያልቻልኩኝ።
ዮሐ ፰ ፥ ፫

🔸ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!🔹


ጡት ነካሾችና : ውለታ ቢሶች ከመሆን አምላክ ይጠብቀን!
@kinexebebe


"ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል። አዎ አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው። በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበተ ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል። አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ስድበኸዋል። እንግዲህ ተመልከት ነቢዩ "እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ አግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፥3)።

እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውና ሌላ ስው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቆጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቸቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው፣ ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቆጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው?

አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነር ትጠነቀቃለህ። ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ። ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቦናህ ግን እዚህም እዚያም - በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል! ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው።

እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
@kinexebebe


✟ ስለ ጾም ብሂል ✝️
✍️ ጾም የትሩፍት ሥራ መጀመሪያ የጽሙዳን ክብራቸው ናት፡፡
/ ማረ ይሰሕቅ/

✍️ በትጋህ ሌሊት ጊዜ መቆም መስገድ ባይቻልህ በአልጋህ ላይ ተቀምጠህ ሳለህ ትጋህን ያዝ ተገኝተህም ቢሆን ሁለት ቀን ወይም ባይቻልህ እስከ ሠርከ ጹም ፡፡
እስከ ሠርክም ወጾም ባይቻልህ መጥነህ ተመገብ እስክትጠግብ እንዳትመገብ ተጠበቅ
/ አቡነ ሺኖዳ/

☞ ይህን ዓለም ማሰብ በመዓልት እንዲዋጋን እንዲሠለጥብን የታወቅ ስለሆነ ዘወትር ጾምን ጽኑ ጋሻ ልንይዝ ይገባል ፡፡
/ ዮሐንስ አፈወርቅ /

☞ የአንደበት ጾም ከአፍ የተሻለ ነው ፡፡ የልብ ከፍትወት መከልከል ደግሞ ከሀሉም የተሻለ ነው ፡፡
/ ቅዱስ ይሰሕቅ /

☞ ጾም መከታ ነው ማንኛውም ሰው የዲያብሎስ ኃያል መመከት አለበት ፡፡
/ ቅዱስ እንድርያስ /

☞ አንድ ንጉሥ የጠላቶቹን ከተማ ለመይዝ ከፈለገ በመጀመሪያ ማድረግ ይለበት የጠላቶቹን የውኃና የምግብ መስመር ሙሉ ለሙሉ ማቋረጥ ነው ፡፡ በሥጋም ቢሆን ልክ እንደዚሁ ነው ፡ አንድ ሰው ሲጾም በጣም ስለሚርበው የነፍሱን ጠላቶች ፈጥነው ይደክማሉ ፡፡
/ ዮሐንስ ሒጺር /
@kinexebebe




+ አባቶቻችን እንዲህ አሉ +

"እሳትና ውኃን ማዋሐድ እንደማይቻል በሌሎች ኃጢአት መፍረድም በራስ ኃጢአት ከመጸጸት ጋር አብሮ አይሔድም" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው" አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ

"እግዚአብሔር ለኃጢአተኛ ሰው ያለው ፍቅር
ጻድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል"
አባ አርሳኒ

"ሕፃን ልጅ እናቱ ስታጥበው ያለቅሳል:: ሕፃን እምነት (ትንሽ እምነት) ያላቸው ሰዎችም ነፍሳቸውን የሚያጥብ መከራ ሲመጣባቸው እግዚአብሔርን ያማርራሉ" አባ ስምዖን

"ዕለትን የሠጠህ እርሱ ለእለት የሚበቃህንም ይሠጥሃል" ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

"እጅግ ምርጡ ጸሎት "ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ" ማለት ነው"
ባሕታዊ ቴዎፋን

"ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንጹሕ ብትሆንም አትናቀው:: ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድም ብሏል" አባ ቴዎዶር

"አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ ብታይ እንኳን አትፍረድበት:: አንዳንዴ ዓይንህም ሊሳሳት ይችላል"
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"ለኃጢአተኛው ክንፍህን ዘርጋለት:: ኃጢአቱን ልትሸከምለት ባትችል እንኳን ሸፍንለት"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

ከአበው አንዱን ትሕትና ምንድርን ነው? ብለው ጠየቁት:: እርሱም "ትሕትና ማለት ወንድምህ በበደለህ ጊዜ እርሱ ይቅርታ ሳይጠይቅህ በፊት ቀድመህ ይቅር ማለት ነው" አለ::

"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ" አባ ኤፍሬም አረጋዊ
መልካም ቀን
@kinexebebe


# ዳግም ምን አሏቸው? #
/መነባንብ/

****✞**********

እናታለም ተዋህዶ
ባንችነትሽ የሚኮራ
በስምሽ ስም የሚጠራ
ዛሬ ጠፋ የሚያበራ
ስለፍቅርሽ ቀልጠው ነደው
ስለ አምላካቸው ተማግደው
በሃይማኖት ፍቅር እጅጉን ተነክተው
ካንቺ ጉያ በኖሩ
እግሮችሽ ስር በተማሩ
ለምን/2/ ተዋህዶ ጠላቸው መንደሩ
ምን አሏቸው ደግሞ ቅዱሳን አበውን
አንቺን እናት እምነት ከዚህ ያበቁትን
ምን አሏቸው ደግሞ አበው ሊቃውንትን
አንድምታውን ፈተው ባመሰጠሩልን
ሚስጢርን መሰጥርው ለኛ ባኖሩልን
ብራና ወጥረው አምድ በፃፉልን
ውለታቸው ታዲያ ይህ ነው?
ስላደረጉልን የምንከፍለው
ጭራሽማ አምላክ ባከበራቸው
አክሊሉን በደፋላቸው
በሀሴት በተቀበላቸው
ልባችን ለምን አመፀ ለምንድን ማይቀበል
ተፈትኖ ያለውን የተፃፈላቸውን የህይወት ገድል
ለምንድን! የማናምን በምልጃቸው
እሱ እግዚአብሔር በሰጣቸው
ደግሞስ ምን አሏቸው?

እሄ......./በለቅሶ/

ሁሌም እውነት ነው
መልከ መልካም ሙሽራዋ
የፀናች በድንግልናዋ
ማን አለ እንደዝች እንደ ቅድስት እናት
ያልተረታ በነገስታት
አንገቷን ለሰይፍ የሠጠች
ክርስቶስን ብላ የኖረች
እኮስ ምን አሏት ይህችን እናት
የስጋ ፋላጎት ያልሠበራት።
ተዋህዶ እናት አለም
እንደድሮ ፀንቶ የሚኖር ልጆችሽ ፈርተዋል የሉም
የምልጃ ታላቅ ስራ
ለህዝቦቿ እያበራ
እየለመኑ ምህረት
ሲያስተዳድሩ አናብርቱ አናብስቱን
ከባህር ውስጥ የፀለዩ
በስራቸው የተለዩ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ አባት
ምን አሏቸው ይሆን አንቺ ምስኪን እምነት
አይደል እንዴ ተዋሕዶ
ስጋቸውን የገበሩ
በእርኩሳን መናፍስት የተፈሩ
በእግዜር ጥበብ የከበሩ
ምን አሏቸው ቅዱሳንን ሰማዕታት ፃድቃናትን
የክርስቶስ ደቀመዝሙር ሃዋርያት
ትንቢት ፀሀፊ ነቢያት
ተዋህዶ ውዷ እናቴ ምን አሏቸው?
በዕቶን ውስጥ ማግደዋቸው
እንደ እንስሳ አረደዋቸው
በቁም ቆመው ቆዳቸውንገፈዋቸው
ላንቺ ቋሚ ልጆችሽን ምን አሏቸው
አይ ተዋህዶ....

በአንድ እግራቸው ሰባት ዓመት የፀለዩ
ባንቺ የፍቅር መግቦትሽ ከዓለም ላይ የተለዩ
የተክለሃይማኖት እናት አንቺ ቅድስት እምነት
አያማልዱም ሲላቸው ልጆችሽን
ዛሬ ምን ተሰማሽ ንገሪኝ በእውነት
የልጆችሽን ምልጃ ሊያስታርቅ ሊቃትት
መቻል ደጉ....
ስንቱን ቻልሽው እናታለም....
እሄ......

የእመብርሃን አስራት ኢትዮጵያ
የቅዱሳን የፃድቃን መፍለቂያ
አንቺስ ጋር ምን አሏቸው
መሠረቶችሽን ሲገፏቸው
ምን አልሻቸው ይሆን እንደው ዝም አልሻቸው
የመኖሬ ምስጢር
የመኖሬ ዘመን እምነቴ እሷናት ብለሽ ሳትነግሪያቸው
የቅዱሳንን ምልጃ የፃድቃንን ምልጃ ሳታሰተምሪያቸው
ለዚህ ይሆን አማላጅ አይደሉም ብለው የናቋቸው
ለነገሩ አይደለም
ስንቴ አስተማርሻቸው
በግልጽ አሳይተሽ አስቀምጠሽላቸው
ሰብከሻቸው ነበር ጊዜ ነጎደና በመናፍቅ እስር
የማማላዳቸው ያን ሁሉ ምስክር
ቀበሩት ከአፈር
እና ተዋህዶ ያንቺን ጓዳ የሚያውቁ
በፍቅርሽ ማነቆ የታነቁ
ቀስ በቀስ ወጡ እያለቁ
አሁንማ እናቴ
ባንቺ ጉያ እየኖሩ
አንቺንም እያሳፈሩ
ፈሉብሽ እንደ አሸን ቅዱሳንሽን እየካዱ
አያማልዱም ብለው ረግጠው እየሄዱ
ታዲያ ምን አሏቸው
ያንቺን ልጆች በቤታቸው
ዛሬስ ምን አሏቸው???


ውስብሐት ለእግዚአብሔር!
@kinexebebe
@kinexebebe
@kinexebebe


# ልጄ_ሆይ_አመስግን
📍📍📍📍📍📍📍

፨በአለም ላይ በሚሊዬን የሚቆጠሩ ሰዎች የዕለት ጉርሳቸውን አጥተው ተርበው ያቃስታሉ፤አንተን ግን እግዚአብሔር በቸርነቱ አጥግቦ እያኖረህ ነው እና አምላክህን አመስግነው
፨ብዙዎች በእዚህች ሰዓት እንደ መፃጉ በደዌ ተመተው በአልጋቸው ላይ ሆነው ምህረትን ከእግዚአብሔር ይለማመናሉ።አንተ ግን እንደ በደልህ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ፍቅር በጤንነት ትመላለሳለህ እና አምላክህን አመስግን
፨ብዙዎች ይህችን ጀንበር ላያዩ አንቀላፍተዋል፤አንተ ግን በምህረት ጥላ ውስጥ ሆነክ ይኼው አዲስ የቸርነት ቀናትን እየኖርካቸው ነው እና አምላክህን አመስግን
፨በደዌ አልጋ ላይ ተኝተህ ብትኖርም አመስግን ፤አልጋህን ተሸከምህ ተረማመድ የሚል አምላክ በቀኑ ወደ አንተ ይመጣልና።
፨ አለኝ የምትለውን አጥተህ ፤የምትመካባቸውን ተነፍገህ እግዚአብሔር እንደበደለህ በሚነግሩ ክፉዎች መሐል ሆነህ ሀዘን ቢሰማህም "እርሱ ሰጡ እርሱ ነሳ" ብለህ እንደ ትዕግስተኛው ኢዬብ ትዕግስትን ተላብሰህ አመስግን ።
፨እንደ ይሁዳ መጠራትህ ለክህደት ሳይሆን ለመፅናት ከሆኑ ሐዋርያቱ ጉባኤ ትሆን ዘንድ ከቤተክርስቲያን እናትነት ተወልድህ ቆመሐል እና እግዚአብሔርን አመስግን
፨ እንደ ዳዊት ማንም ቢታዘብህ አንተ ግን የምትማልከውን አምላክ አስበህ ስለተደረገልህ ነገር ሁሉ እንደ እንቦቅቅላ በኃይል አመስግን
**
ልጄ ሆይ እርሱ ምስጋና የባህሪው ነው፤ቅዱሳን መላእክት በሰማይ ፤ቅዱሳን ልጆችሁ በምድር ለስሙ ምስጋና አዘጋጅተው ዘውትር ያመሰግኑታል።አንተም በምስጋና ከእነርሱ ጋር ተባበር። አመስግነህ ክብር።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
✨✨✨✨✨✨✨✨
@kinexebebe


እሱ ማነው???
ሀይማኖቱን ከከሀዲ ዮዲት ጉዲት መሳይ
የሚከላከለው መንጋን ተመለስ ባይ
ማርያን- ጠንቋዩን ለአምላክ ያስገዛ
የወንጌል ገበሬ የኢትዮጵያ መዓዛ
እኮ እርሱ ማነው??
የትሩፋት መምህር የእግዚአርያ በረከት
የክርስቶስ ወታደር የብዙዎች አባት
ኢትዮጵያን ያበራት በወንጌል አዝመራ
ባለ ብዙ ሰብል በመኸር ጎተራ
በሰባኬ ክረምት በተዓምራት ፀደይ
የበረከት አባት በፍሬው የሚለይ
እኮ እርሱ ማነው??
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ
ለምስጋና ሚቆም ከመንበረ ስሉስ
እንደ መላእክቱ ክንፍ የተሸለመ
እርሱስ ባህታዊው ተክለ ሃይማኖት ነው፡
@kinexebebe


🙏ፍቀጂልኝ ላንብብ
🕯️🕯️🕯️⛪️🕯️🕯️🕯️


ውዳሴሽን ላነብ ቆርጬ ተነሳው

ሴጣን ዲያብሎስን አሣሩን ላበላው

እኔም እንድባረክ እንድሆን የበቃው

ከሃጢአት የነፃው ንስሀ የገባው

ግን እመቤቴ አልቻልኩም ላነበው

ቅዱስ መፅሃፍሽን ገና አይኔ እንዳየው

ሀጥያቴን አስቤ ሆኜ በደለኛ

የሰው ንብረት በግፍ የምወስድ ቀማኛ
ዝሙትን የምወድ የሆንኩኝ ሴሰኛ
የሰው ደም የማፈስ ገዳይ ነኝ ደመኛ
በውሸት መስካሪ ነበርኩ ሀሰተኛ
ይህን ሁሉ እያሰብኩ ማንበቡ ከበደኝ
እንደ ተራራ ራስ ትልቅ ሆኖ እየታየኝ

የሚጨምር እንጂ ፈፅሞ የማይቀንስ
የምሰራው ሀጥያት ቀን በቀን የሚብስ
ሀጥያቴ አሳፈረኝ ውዳሴሽን ከበደኝ ማንበቡ
እንኳንስ ማንበቡ አቃተኝ ስምሽን መጥራቱ
የጌታዬ ክርስቶስ የአምላኬ እናቱ

ፍቀጂልኝ ላንብብ ውዳሴ ማርያምን
ከሀጥያት ወጥቼ ከሲኦል እድድን
አዲስ ህይወት ስጪኝ አጥፎተሽ የድሮን

ከሀጥየት የነፃው ነጭ አርገሽ እንደርግብ
ውዳሴ #ማርያምን ፍቀጂልኝ ላንብብ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር
@kinexebebe


✅ ቅድስት ድንግል ማርያም ብቻ ‼️



1• አምላክን የወለደች-ማርያም ብቻ !

2• ከመውለዳ በፊትም ሆነ ኋላ ድንግል የሆነች - ማርያም ብቻ!

3• ከሰው ወገን ተለይታ መርገም ያልነካት - ማርያም ብቻ!

4•የእግዚአብሔር ሀገር ከተማ የተባለች - ማርያም ብቻ!

5• በድምጽዋ መንፈስ ቅዱስን የምትሞላ ንግስት- ማርያም ብቻ!

6• ጽንስ በማሕፀን የዘለለላት ብጽዕት - ማርያም ብቻ!

7• ያላፈውም የሚመጣውም ትውልድ የሚያመሰግናት - ማርያም ብቻ!

8• ጸሐይን ተጎናፅፋ ጨረቃን የተጫማች ልዩ እናት - ማርያም ብቻ!

9• በጌታ ሞት ያዘነውን ዓለም እንድታፅናና ጌታ የሰጠን ሥጦታችን - ማርያም ብቻ!

10• በስጋዋ፣ በነፍስዋና በሕሊናዋ በሶስት ወገን ድንግል የሆናች - ማርያም ብቻ!

11• ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነች - ማርያም ብቻ!

12• ከፍጥረት ሁሉ ተላይታ አምላኳን "ልጄ" የምትል - ማርያም ብቻ!

13• ፍቅርዋ በልቤ የሚቀጣጠል አማላጅነትዋን ነፍሴ የሚመሰክርላት እናቴ - ማርያም ብቻ!

14• ከሰው ወገን 'ቤዛዊተ ዓለም' የሚል የጸጋ ስም ያላት - ማርያም ብቻ!

15• በንጉሱ ቀኝ ቆማ የምትማልድ ንግስት - ማርያም ብቻ!

16• ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን የሚላት - ማርያም ብቻ!

17• አባ ኤፍሬም ያወደሳት፣ አባ ሕርያቆስ ያመሰገናት፣ ቅ.ያሬድ የተቀኘላት እመቤት - ማርያም ብቻ!

18• ከሰው ወገን በስጋ ከሞት ተነስታ ያረገች ንጽሕት እናት - ማርያም ብቻ!

19• የመላእክት እህታቸው፣ የሰማዕታት አክሊላቸው፣ የመነኮሳት መመኪያቸው - ማርያም ብቻ!

20• ዘንዶው በሰው ልብ እንዳትቀረፅ ሊውጣት የሚፈልግ፣ ዘርዋንም ሊዋጋ የሚሻቸው ባለ ሁለት ክንፍ እመቤት - ማርያም ብቻ!

21• ጌታ ከፍጥረት ሁሉ ለይቶ "እናቴ" የሚላት - ማርያም ብቻ ‼️
@kinexebebe


#የኔታ
ከበሮ _ለምን_ይጮሀል?
የኔታ ለተማሪዎቻቸው አንድ ጥያቄ አቀረቡ..... " ልጆች ከበሮ
ለምን ይጮሀል?" የኔታ ....የኔታ .... "በቆዳ ስለተወጠረ
ነው"......አለ አንድ ተማሪ የዳዊት መሀደሩን በእጁ
አንጠልጥሎ ለመመለስ እየቸኮለ። የኔታም "አይደለም አሉ"
ሌላኛው ተማሪም...."የኔታ ከእንጨት ስለ ተሰራ ነው" አለ
የለበሰውን ለምድ ከፍ ከፍ እያደረገ ........የኔታም ትንሽ ዝም
ካሉ በኋላ ..... "አይደለም አሉ"...ተማሪው ሁላ ማውጣት
ማውረድ ጀመረ በሀሳብ ተወጠረ። ሁሉም የመጣለትን እና
የገመተውን መናገር ቀጠለ ግን የሚመልስ ጠፋ።
አንድ የሁሉንም ምላሽ በእርጋታ ይሰማ የነበረ ተማሪ እጁን
አወጣ።...." እሽ ልጄ " አሉ የኔታ .....ድምፁን ከፍ አደረገና
....,የኔታ እድሉን ስለ ሰጡኝ አመሰግናለሁ ብሎ እጅ ከነሳ በኋላ
....የኔታ ከበሮ የሚጮኸው "ባዶ ስለሆነ ነው"! አለ። የኔታም
የልጁን ምላሽ በማድነቅ ከወንበራቸው በመነሳት ...ልጄ ተባረክ
አሉ። ተማሪዎቹም በጭብጨባ አጀቡት።
የኔታም ቀጠል አደረጉና ..... ልጆች "ባዶ" የሆነ ነገር ሁላ
ይጮሀል በውስጡ የሆነ ነገር ያለው እቃ ግን አይጮህም።
የተማረም ሰው እንዲሁ ነው። እውቀት ያለው አይጮህም፣
ጥበብ ያለው አይጮህም፣ ምንጊዜም ባዶ የሆነ ሰው ሲጮህ፣
ጥበብ የሌለው ሲፎክር እውቀት የሌለው ሲያቅራራ ይታያል።
እና ልጆቼ.... እናንተ "ባዶ" እንዳትሆኑ እውቀትን ጨምሩ፣
በእውቀት ላይ ጥበብን፣ በጥበብ ላይ እግዚአብሔርን መፍራት
ጨምሩ። ምድራችንን በማስተማር እና በመስበክ የሞሉ
ግን"ባዶ" የሆኑ። ምድሪቱን በዝማሬ የሞሉ በሐይማኖትእና
በምግባር ግን "ባዶ" የሆኑ። ጌታ ሆይ..... ጌታ ሆይ....የሚሉ
ግን ጌታ የማያውቃቸው እንደ ሰው ተፈጥረው እንደ እንሰሳ
በደመ ነፍስ የሚኖሩ ሰዎች ፣ በዝተዋልና ብለውቁጭ አሉ።
ተማሪዎቹም የኔታን አመስግነው ትምህርታቸውን ቀጠሉ።
@kinexebebe


በአንድ ወቅት መፀሐፍ አንብቦ የማያወቅ ሰውዬ ከጎደኞቹ ጋር ተቀምጦ ሳለ ስላነበቧቸው መፃሐፍት እየተነጋገሩ እሱ ብቻዝም ማለቱ በጣም ተሰማው በተለይደግሞ የመፀሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን እያነሱ የተጫወቷቸው ጨዋታቸው ባይገባውም ውስጡን ግን ደስደስ አሰኝቶታል ከዛ አንዱን ጓደኛውን መፀሐፍ ቅዱስ ማንበብ እፈልጋለሁ ይለው ና ይቀበለዋል ከዛም ቤቱገብቶ ይቀመጥና መፀሐፍ አንብቦ ስለማያውቅ ዝምብሎ ከመሀል ገፅ ይገልጥና ሲመለከት ይሁዳም ራሱን አጠፋ.....ይላል ደንግጦ ዘጋው ምን አይነት ነገርነው ብሎ ኸረጉዱን ልየው ብሎመልሶ ከመሀል ቢገለጠው ....እናንተም እንዲሁ አድርጉ....የሚልሀረግ ያገኛል ከመጀመሪያው ይበልጥ ደነገጠ ከመቀመጫው ብድግ ቁጭ አለ ይሄንንነው መፅሐፍ ቅዱስ የሚሉት ድንቄመ ቅዱስ እያለ ሊመልስለት ሄደ፡፡
✍የዚ ዘመንም ዋናው ችግር ብሉይን ሳያነቡ ሀዲስ መፃፈነብያትን ሳያነቡ ወንጌልን ወንጌልን ሳያነቡ መልዕክታቱን እያነበቡ ያንዱን ንባብ ከሌላኛው ጋር እየጨረሱ ይመስለኛል


Репост из: የያሬድ🕇🕆 ውብ💒💒ዜማ⛪⛪
🌿Maqaa Abbaa kan ilmaa kan Afuura Qulqulluu Waaqa tokko Ameen!

Caamsaa ⓱

🌷 Ayyaanota Waggaa

1,Qulqulluu Eephifaaniyoos
2, Qulqulluu Elaariyoon
3, Aabbaa Lukiyaanoos
4, Qulqulluu Filaataawoos

🌷Ayyaanota ji'aa

1,Hangafa Daaqonootaa Wareegamaa Qulqulluu Isxiifaanoos
2, Duuka bu'aa Qulqulluu Yaa'iqoob
3, Qulqulloota Maaksimoos fi Dumaatewoos

Waaqayyoof galanni haa ta'u!! Araarsummaan qulqullootaa nurraa adda hin bahin!! Ameen!!
-------------------------------------------

"Egaa beektota ta'aa! qabsaa'aa.! Diinni keessan seexanni akka leenca beela'ee waan liqumsu barbaaduutti jooraatii"
{1ffa Phex 5: 8}
Https/t.me/amantaakoo


"መንፈሣዊ የሕይወት ምክር"
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✟ የእግዚአብሄር ትእዛዝ የሕይወት ምንጭ ነዉና ትእዛዙን ጠብቅ።
✟ ኣመጽና የክፉዎች መስዋእት በእግዚኣብሄር ዘንድ የረከሰ ነዉና
በክፉ ስራ ኣትጓዝ።
✟ እግዚአብሄርን ባለመፍራት የሚገኝ ብዙ ባለጸግነት
እግዚኣብሄርን በመፍራት የሚገኝ ጥቂት ሃብት ይሻላልና በፈሪሃ
እግዚአብሄር ተመለስ።
✟ እግዚኣብሄር መልካሙን ዋጋ እንዲሰጥህ ጠላትህን ቢርበዉ
ኣብሰዉ ቢጠማዉ ኣጠጣዉ ቢታረዝ ኣልብሰዉ ቢቸገር እርዳዉ
ይህንን በማድረግ በምላሹ ላንተ ጉድጓድ ቢምስብህ ራሱ
ይወድቅባታል።
✟ ቀናተኛ ሰዉ የኣጥንት ነቀዝ ነዉና ከቀናተኛ ጋር ኣትዋል።
✟ ድሃን የሚንቅ ፈጣሪዉን ያስቆጣል የሚያከብር ግን ምሕረትን
ያገኛል ድሃን ኣትናቅ።
✟ እዉነተኛ ምስክር ነፍስን ከክፉ ያድናልና የሓሰት ኣቀጣጣይ
ኣትሁን።
✟ ኃላ እንዳትቀር ኣይንህን ያየዉን ተናገር።
✟ ከሃሰተኛ ባለጸጋ እዉነተኛ ደሃ ይሻላል።ሕግን ከመስማት
ጀሮዉን የሚመልስ ሰዉ ጸሎቱ የተናቀ ነዉ።
✟ መልካም ሞት የመልካም ኑሮ ዉጤት ነዉ።
✟ ላያልፍ የመጣ ክፉ ነገር የለምንና እስከያልፍ ታገስ።
✟ የሞተ ሰዉ ጠላት የለዉም ጠላት ካለህ መኖርህን እወቅ።
✟ በሰዎች ስትገፋ ለምን ኣትበል ቅቤም ተገፍታ ነዉ ከሰዉ ራስ
ላይ የምትወጣዉ።
✟ ኣንደበትህ ትልቅ ዉስጥህ ቀላል እንዳትሆን ተጠንቀቅ።
✟ በእግዚኣብሄር እንጂ በደጋፊዎች ኣትተማመን በደጋፊዎች
ከተማመንክ ከሰባራ ወንበር ላይ እንደተቀመጥክ ቁጠረዉ።
✟ ኣዝማሪና ዘዋሪ የሚሸለሙበት ጊዜ ደርሰሃልና በጸሎትትጋ።
✟ የሰይጣን ደህና ባይኖረዉም ብቻዉን ካለ ሰይጣን ይልቅ በሰዉ
ላይ ካለ ሰይጣን ተጠንቀቅ።ከሰዉ ለይ ያለዉ ሰይጣን በስመአብ
ስትለዉም ከሰዉየዉ ጋር ተጣብቆ ያስቸግራል።
✟ ሰዎች ባንተ ላይ ምንም እንዲያወሩ ስልጣን የለህምና
የሚሉህን እየሰማህ ስህተትህን ኣስተካክል ።
✟ ጊዜህን ከእዉነተኛ መምሃራን ጋር ኣሳልፍ ሓሰተኞች መምሃራን
ጋር የሚበላዉ ህዝብ በዝተዋልና።
ፍጣሪ ኩፉ ይጠብቀን የመንግስቱ ወራሽ ያድርገን ፡ኣሜን
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
@kinexebebe


​​✝ ቅዳሴ ለማስቀደስ ወደ ቤተክርስቲያን ስንመጣ ራሳችን

👉 1ኛ ቆመን ለማስቀደስ
👉 2ኛ የሚነበቡትን መጻሕፍቶች ከሕይወታችን ጋር እያዛመድን ለማዳመጥ ለመስራት
👉 3ኛ ቅዱስ ቁርባን ለመውሰድ የዘለዓለም ሕይወትንም ለማግኝት አምኖ መምጣት አለበት

-በቅዳሴው የመግቢያ ክፍል ይህንኑ በዜማ “እስመጨረሻው ቅዳሴውን ያላስቀደስ ቅዱሳን መጻሕፍትን ሲነበቡ ቆሞ ያላዳመጠ በመጨረሻም ቅዱስ ቁርባን ያልተቀበለ ከቤተክርስቲያን ኅብረት ልጅነት ይሰደድ” ይላል ስለዚህ ራሱን አዘጋጅቶ መምጣት ይገባል፡፡

-በተጨማሪም ሰው ለቅዳሴ ሲቆም 5ቱን የሥሜት ሕዋሳቶቹን ሰብስቦ ወደ ቅዳሴው ትኩረት ሰጥቶ በንቃት ለቅዳሴ መቆም አለበት ለዚህም ዲያቆኑ በመሃል በመሃል “ለፀሎት ተነሱ” እያለ ያውጃል ምዕመኑም ራሱን በእግዚአብሔር ፊት አዋርዶ ይቅርታን በመጠየቅ “አቤቱ ይቅር በለን” ይላል።

አምስቱ የስሜት ሕዋሳት የሚባሉት አይን፣ ጆሮ፣ አፍንጫ፣ እጅ እና ምላስ በአንድት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ ለምሳሌ፡-

#ዐይን፡- ካህኑ ቅዳሴን ሲቀድስ በመንበሩ አጠገብ ቆሞ ብቻ አይደለም የተለያዩ ዓይነት እንቅስቃሴዎች አሉ እነዛን እንቅስሴዎች ደግሞ ራሳቸውን የቻሉ መንፈሳዊ ምሥጢራዊ ትርጓሜዎች አሉዋቸው እነዚህን እንቅስቃሴዎች አይን ያያል ስለዚህ ዐይን ያስቀድሳል ማለት ነው፡፡

#ጆሮ፡- ካህኑም ዲያቆኑም ምእመኑም በአንድትም ሆነ በተናጠል የሚያዜሙትን ዜማ፣ የሚያነቡትን ንባብ ይሰማል በዚህ ጊዜ ጆሮአችን ያስቀድሳል ማለት ነው፡፡

#አፍንጫ፡- የዕጣኑን መዓዛ በማሽተት አፍንጫችን ያስቀድሳል

#ምላስ፡- ቅዱስ ቁርባን በመውሰድ፣ የቅዳሴውን ፀበል በመጠጣት በዚህ ጊዜ የመቅመስ ስሜታችን ያስቀድሳል፡፡

#የመዳሰስ፡- የመዳሰስ ስቀሜታችንም ስግዱ በተባለ ጊዜ፣ ወንጌል ከተነበበ በኋላ ወንጌሉን ሲስም በመጨረሻም ሰዓት የካህኑን እጅ ለመባረክ ስንስም የመዳሰስ ስሜታችን ያስቀድሳል ማለት ነው፡፡

ስለዚህ አምስቱም የስሜት ሕዋሶቻችን በተሟላ መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት መንገድ ምንድን ነው ቢባል ቅዳሴ ነው። በቅዳሴ ውስጥ የምናገኘው ትምህርት በአውደምህረት በኮርስ ከምናገኝው ትምህርት የተለየ ነው ይኽውም በዜማ የታሸ ብዙ ሊቃውንት የደከሙበት መንፈስ ቅዱስ እንደገለፀላቸው ለሰው በቀላሉ የሚገቡ ትምህርቶች ናቸው ሌላው ደግሞ ወንጌል ይነበባል መልዕክታት፣ የሐዋርያት ሥራ፣ ከዓለም አቀፍ ከሆኑ ሁሉ እና በዜማ ስለሆነ ነው እንጂ (ምስባክ) የምንለው ከመዝሙረ ዳዊትም ውስጥ ይነበባል።

- ስለዚህ 1 ሰው ቅዳሴን ሲያስቀድስ ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን ከብሉይ እስከ ሐዲስ ድረስ ይማራል ማለት ነው። ረጅም ዘመን ያስቀደሰ በሕይወቱ ውስጥ ምሁር ማለት እርሱ ነው ማለት ነው። ምክንያቱም ከላይ እንዳልነው ነው። የመላእክትን ህይወት በምድር ላይ መኖር ማለት ነው፡፡

በቤተክርስቲያናችን ትልቁ ሱታፊ ቅዳሴን ማስቀደስ ነው ይህንንም ከራስ አልፎ ወገኖቻችን ይህን ምሥጢር እንዲሳተፉ ማድረግ ይገባል ልጆቻችን ከቅዳሴው እንዲሳተፉ ተሰጥዖ እንዲመልሱ፣ መባን ይዘው እንዲመጡ፣ ቅዳሴ ለማስቀደስ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ፣ ቅዱስ ቁርባን እንዲቀበሉ ማድረግ ተገቢ ነው ያለበለዚያ የምሰጠውን የምናጣበት ደረጃ ላይ እንዳንደርስ የቀደመውን ሥርዓተ አምልኮ የሚፈፀምበት ሥርዓት እንዳይጠፋ የሚረከበን እንዳናጣ የቀደመው ለተተኪው ትውልድ ማስረከብ መቻል አለበት ሰማያዊ ምሥጢር በምድረ ከተሰራባት ከመላእክት ጋር አንድ ሆነን ፈጣሪን ከምናመሰግንባት ከቅድስት ቤተክርስቲያን ሳያናውጥ ያኑረን አሜን።

ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች ዕመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን።


ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር

♥አሜን
@kinexebebe


( አንቺ እናት ባትሆኝኝ )

የመኖሬ ትርጉም ቅኔዉ ሲጠፋብኝ፣
የህይወቴ መፅሐፍ ገፁ ሲምታታብኝ፣
የእኔነቴ ዋጋ ባዶ ሲሆንብኝ፣
የሀጢያት ሐረግ ሲነጠላጠልብኝ፣
ሙቸ መራመዴ ለእኔ ሲታዉቀኝ፣
ምን ይዉጠኝ ነበር አንቺ ባትኖሪልኝ?

አልቅሸ ሰነገርሺ አለዉህ ባትይኝ፣
የመዳንን መድህን ልዑል ባትዉልጂልኝ፣
በምልጃሺ ፀሎትሺ ቤቴ ባይሞላልኝ፣
በይቅር ባይነት ንሮ ባይቀናልኝ፣
ማን ያሰበኝ ነበር አንች ባታሰቢኝ።

ሀጥያት ተፀይፈሺ ፊት ያላዞርሽብኝ፣
ብርሀን ዉልደሺ ፀሀይ የሆንሺልኝ፣
ለዉለታሺ ገላጭ ምንም ቃላት የለኝ፣
አማላጇ እናቴ ሁሌም ክበሪልኝ፣
ድንግል እመቤቴ ከፍ ከፍ በይልኝ።

የችግሬ ደራሽ እመ እግዚአብሔር፣
ቃል ኪዳንሽ ይርዳኝ ካንቺ ጋራ ልኑር።
የአዳም ተስፋው ነሽ የሴት ቸርነቱ፣
ኪዳነ ምህረት ነሽ የኖህ ምልክቱ።
አዳም ደጅ የጠናሽ ሲገባ ንስሃ፣
ኖህም ድኖብሻል ከጥፋቱ ውሀ።
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ፣
ማርያም አንቺ ነሽ የፈጣሪ እናቱ።
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ፣
እመብርሃን ስሚኝ ልመናዬን ሁሉ።

የሰለሞን አክሊል የዳዊት ዝማሬ፣
ድንግል መሆንሽን ትመስክር ከንፈሬ።
ለተጠማ ውሻ የሚራራው ልብሽ፣
ለኔም ራርቶልኝ አስታርቂኝ ከልጅሽ።
የተራበ ጠግቦ የተጠማ ረክቶ፣
በስምሽ ይኖራል ሁሉም ተደስቶ።
በህይወት ጠብቂኝ ከመሞት ሰውረሽ
መከራን እንዳላይ በክንፎችሽ ጋርደሽ።

የምህረት ቃልኪዳን አምላክ የሰጠሽ፣
የአማኑኤል እናት መጽናኛዬ ነሽ።
ምንም ተስፋ የለኝ ባንቺ ነው እምነቴ፣
አማልጅኝ ከልጅሽ ክብረት እመቤቴ።
ሕይወቴ ጎስቁሎ በነፍሴ ብዝልም፣
በምልጃሽ ታምኜ በኪዳንሽ ልቁም።
ስምሽን እየጠራሁ እጽናናለሁኝ፣
ስሞት እንዳልጠፋ ድንግል ጠቢቂኝ።

ደሃ ምስኪን ሆኜ ለሰዎች ብታይም፣
ሞልቶ የተረፈ ጥሪት ባይኖረኝም፣
ስምሽን ብጠራው ምንም አይጨንቀኝም።
አንቺ ካለሽልኝ ኑሮዬ ሙሉ ነው፣
አፍሮ አያውቅምና የተማጽነሽ ሰው።
እኔን የሚረዳኝ በአገሩ ስቸገር፣
ዘመድ ጠያቂ የለኝ ፍጽም ካንቺ በቀር።
ከውጭም ስገባ ከቤትም ብወጣ፣
ነፍሴ እንድትቀደስ ከርኩስነት አምልጣ፣
ጠብቂኝ እመቤቴ ከዘመኑ ቁጣ።

ከአፌ አለይሽም አንቺን እጠራለሁ፣
ከአፌ አለይሽም ማርያም እልሻለሁ፣
አንቺ የወለድሽው ኢየሱስ አምላክ ነው፣
አንቺ የወለድሽው ክርስቶስ ንጉስ ነው።
የዳዊት ዘር ድንግል ንጉሱ ወዶሻል፣
ገነትን ስናጣ ተስፋችን ሆነሻል።
ክብርሽን የሚረሳ ልብ የለንም ከቶ፣
ልጅሽ አድኖናል ሞታችንን ሞቶ፣።

አሳረፈው ልቤን የእጆችሽ በረከት፣
የአማኑኤል እናት የታተምሽው ገነት።
በሰማይ በምድር ያንቺ ክብር ልዩ ነው፣
ለሰው ዘር መዳኛ ምክንያት የሆንሽው።
ክብርሽን ያወቀው ከመቅደስሽ ገብቶ፣
ተፈሲህ ይልሻል ለክብርሽ ተቀኝቶ።
ከሴቶች ለይቶ ማደሪያው ሲያረገሽ፣
የአዳም ዘር በሙሉ ቆሙ ለምስጋናሽ።
እናቱ ነሽና ዘመሩ ለስምሽ።

ፀጋን የተሞላሽ ደስተኛይቱ ሆይ ደስ ይበልሽ !

አዛኝቷ እመቤት አደለም ለሰው ልጆች ለውሻ የራራችው ኪዳነ ምህረት እናታችን የመረረውን ሕይወታችሁን ጣፋጭ ታድርግላችሁ ሲጨንቃቹ ሲጠባቹ ከልጇ ከወዳጇ ታማልዳችሁ!!!
@kinexebebe


".....ልቡ ግን ከእኔ ርቋል..."


አንድ ባሕታዊ ብዙ ሰዎች ሰብስበው እየሰበኩ ሳለ ጭራቅ ከጫካ ወደ ጉባኤው ይመጣል። ወደ ባሕታዊው ቀረብ ይልና "አባቴ እንግዲህ እንደምታውቁት የእኔ ሕልውና በሰው ሥጋና ደም ላይ የተመረኮዘ ስለሆነ እነኝህን ሰዎች ልበላቸው ነው" አላቸው።

ባሕታዊውም የሰው ሥጋ መብላትህን አውቃለሁ ግና እነዚህ ልጆቼን አትበላሸቸውም የክርስቶስ ናቸውና አትችልም ብለው ገዘቱት።

አቶዬም ግድ የሎትም አባቴ እኔ የክርስቶስ የሆኑትን አልበላም ንክችም አላረግም ሲል ቃል ገባላቸውና ተለያዩ።

ከሄዱበትም ሲመለሱ ጭራቁ ባሕታዊው ያስተማሩትን ሰው ሁሉ በልቶ ከንፈሮቻቸውንና ምላሳቸውን አስቀርቶ ጠበቃቸው ። በጉዳዩም በጣም የተቆጡት ባሕታዊ ምነው የክርስቶስ ናቸው እንዳትበላ አላልኩህም አሉት።

ጭራቁም በሰው ደም የለሰለሰውን ከንፈሮቹን በምላሱ እያበሰ "የክርስቶስ የሆኑትን አሁንም አልበላሁም" ብሎ በኩራት መለስላቸው።

ምን ማለትህ ነው ያስቀረኸው የለም እኮ ቢሉት "አባቴአባቴ የክርስቶስ የሆነው ምላሳቸው ነው። ክርስቶስ ያለው ከንፈሮቻቸውና ምላሳቸው ላይ ብቻ ስለሆነ ሌላውን አካላቸውን በላሁት" አላቸው።
ዛሬም በክስርቶስ ስም ተጠርተን አካላቱ ሆነን ልንመላለስ በሚያስፈልግበት ጊዜ እኛ በእርግጥ ሆነናል ወይስ እንደሰዎቹ ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣኦት ነን።

ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ ርቋል ማቴ ፲፭፣፯ ቃሉን ሰምቶ የማያድርገው ፊቱን በመስታወት እንደሚያይ ሰው ይመስላል። ፊቱን ካየው በኋላ ዞር ሲል ፊቱን ይረሳዋልና።
@kinexebebe


ከቴሌ-ብር አገልግሎት ጀርባ
-----------------------------------------



ሁል ጊዜ አዲስ ነገር ሲመጣ
ፍርሀት ይኖራል ፍርሀት ጥሩ ባይሆንም ከነገሮች ጀርባ ማጥናት
እና መመርመር መልካም ነው (ሁሉን መርምሩ የተሻለውንም
ያዙ ይላል ቅዱሱ መፅሀፍ )
...ባንክ ያንን ሁሉ ሰራተኛ ቀጥሮ ሲስተም ዘርግቶ ለገንዘባችን
ዋስትና ሰጥቶ ከአገልግሎቱ ተጠቀሙ ሲለን ያለ መክነያት
አልነበረም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያገኘውን
20%ኮሚሽን በማሰብ እንጂ ....
at this time everything give and take ሰጥቶ መቀበል
ነው የነፃ የሚባል ነገር የለም የሆነ ሰው የሆነ ነገር ያለ
ምክንያት ሲያደርግላችሁ ከናንተ የሚፈልገው የሆነ ነገር አለ
ማለት ነው ....
#ቴሌ_ብር 15 ብር ካርድ ...70MB....15%የአየር ሰአት ግዢ
ቅናሽ ሲስተም ዘርግቶ የነፃ የስልክ ጥሪ መስመር (127) ክፍት
አድርጎ በዚህ ሁሉ ማባበያ ስልካችን እስኪሞላ ቴክስት እየላከ
የተመቻቸ አገልግሎት ልስጣችሁ የሚለን ከምን አንፃር ነው
የሚለው ጥያቄ ነው ወሳኙ ነገር....
ባለፈው አመት በዘመነ ኮኖራ መጋቢት 26 ላይ ነበር
የሚኒስተሮች ምክር ቤት የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽን ረቂቅ አዋጅ
ያወጣው እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያፀድቅ
ያቀረበው።......ይኸው ዛሬ አንደኛ
አመቱን እንደያዘ አዋጁ አገልግሎቱን ጀመረ በኢትዮ ቴሌኮም
በኩል # ቴሌ_ብር የተሰኘ መተግበሪያ በስማርት ስልኮች እና
በቴሌኮም ኔትወርክ ሲሰተም አማካኝነት ጥሬ ገንዘብን ወደ
ኤሌክትሮኒክ ገንዘብ የመቀየር ሂደቱ አሀዱ አለ .....
ይህ አገልግሎት 3.5 ትሪሊዮን ብር ወደ ኤሌክሮኒክ ገንዘብ
በመቀየር 33 ሚሊዮን ሰወችን የዲጅታል ከረንሲ ተጠቃሚ
ያደርጋል ተብሎ ይታሰባል !
ይህ ዲጂታል ከረንሲ አጠቃቀሙ እና ጉዳቱ ምንድነው ?
ዲጂታል ከረንሲ ማለት በቁጥሮች የተመሳጠረ በኮምፒውተር
ሲስተም እና ኔትወርክ የሚንቀሳቀስ የወረቀት ብር ኖቶችን
የሚያስቀር የመገበያያ ገንዘብ ማለት ነው .....ከዚህ በፊት
የምንጠቀምባቸው በኤሌክሮኒክ ትራንዛክሽን አዋጅ የሚጠቃለሉ
...ሞባይል ባንኪንግ ....ሲቢኢ ብር....ATM የመሳሰሉ
ዲጂታላይዝድ የሆኑ የምንጠቀማቸው አገልግሎቶች ገንዘባችንን
በአንድም በሌላ መንገድ በጥሬው ማለትም በወረቀት የብር
ኖቶች ማውጣት እና ማንቀሳቀስ እንችላለን
ይህ ግን ዋነኛ አላማው ይህን ነገር ማስቀረት የወረቀት ብር
ኖቶች ወደ ኤሌክትሮኒክ ገንዘብ በመቀየር ህብረተሰቡን
የዲጂታል ከረንሲ ሙሉ በሙሉ የዲጅታል ከረንሲ ተጠቃሚ
ማድረግ እና የወረቀት ኖቶችን ማስቀረት ነው ...
ታዲያ ይህ የወረቀት ገንዘብ መቅረት እኛን ምን ይጎዳናል ነው
ያላችሁት .....
ትገርማላችሁ.......ይህ ነገር ዋና አላማው ህብረተሰቡን ሙሉ በሙሉ
የዲጂታል ከረንሲ ተጠቃሚ በማድረግ ወደ Micro Chip [ RIFD ] በሰውነት ላይ ማስቀበር ማሸጋገር ነው ያኔ የራዲዮ ፊሪኮየንሲ አደንቲ
ፊኬሽን ሲስተም ጉዳት ሲገባህ መልሰህ ወደ ወረቀት ብር ኖት
እንዳትመለስ እና RFID የመጨረሻ አማራጭህ አድርገህ
እንድትጠቀም ማድረግ እና በመጨረሻም ሰወችን ወደ ሮቦት
Artificial intelligence የመቀየር ሂደቱን ያለ ምንም እንቅፉት
ማሳካት ማስቻል ነው።
@kinexebebe


ይህን ያውቁ ኖሯል?
📝ለሰባኪያን መቆሚያ ከፍ ያለ ቦታና አትሮንስ በቤተክርስቲያን መጠቀም የተጀመረው ከ386 ዓ.ም አከባቢ ባለው ዩሐንስ አፈወርቅ ነው። ቅዱስ ዩሐንስ አፍወርቅ ቀሚያስተምርበት ጊዜ ሕዝቡ በብዛት ይሰበሰብ ነበር። ነገር ግን የዩሐንስ ቁመት አጭር ነቀረና ከፍ ብሎ ለሕዝብ እንዲታይና ድምፁም እንዲሰማ መቆሚያ ስፍራና ያጽሐፍት ማንበቢያ አትሮንስ ተሰራች። ቤተክርስቲያንም ከዚያ ዘመን ጀምሮ አትሮንስን ትጠቀምበት ጀመር።
📝ኑዛዜ በቤተክርስቲያን የተጀመረው ሕጋዊና ድንግል ከሆነው የእስክንድርያ 12እኛ ፓትራያርክ ከአባታችን ከቅዱስ ድሜጥሮስ ወዲህ ነው።አባታችን በከንቱ አምተውት የነበሩ ምእመናን በእግዚአብሔር ፋቃድ ክብሩ ቀተገለጠላቸው ጊዜ አባታችን ይቅርበለን ብለው ንስሐ ሲገቡ ይፍትሕ ይኅድግ ብለው ናዝዘዋል። ኑዛዜም ያን ጊዜ ተጀምሯል።
📝አንገት ላይ ማተብ ማሰር የተጀመረው ቀን5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሶርያ ያስተምር በነበረው በአባታችን በያዕቆብ ዘእልበረዲ ነው። አባታችን እያስተማረ በሚያጠምቅበት ጊዜ ለተጠመቁትና ያልተጠመቁት እየተቀላቀሉ ቢያስቸግሩት ለማየት ይቻል ዘንድ ለተጠመቁት ምዕመናን ማተብ ያስርላቸው ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ማተብ ለተጠመቁ ክርስቲያኖች መለያ ምልክት ሆነ።
ከመ/ር ቴዎድሮስ በየነ
@kinexebebe

Показано 20 последних публикаций.

820

подписчиков
Статистика канала