ማንችስተር ሲቲ አዲሱ የማርከስ ፈላጊ ሆኗል !
በፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት ማንችስተር ሲቲዎች ከታላላቆቹ የአዉሮፓ ቡድኖች ባርሴሎና እና ዩቬንቱስ ጋር በመፎካከር የቦርሲያ ሞንቼግላድባዉን አጥቂ ማርከስ ቱራምን ለማስፈረም ተፋጧል።
የ23 ዓመቱ አጥቂ አባቱ ሊሊያም በ1998 የአለም ዋንጫ አሸናፊ ሲሆን ይህም የሱን ፈለግ በመከተል ወደ እግር ኩዋስ የገባ ሲሆን በ2019 ነበር የፈረንሳዩን ጌንጋምፕ በመልቀቅ ወደ ጀርመኑ ሞንቼግላድባ የተቀላቀለዉ።
ቱራም በ2019/20 የዉድድር ዓመት 39 ጨዋታዎች በማድረግ 14 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን በአዲሱ የዉድድር ዓመትም በአቋሙ ቀጥሏል።
አጥቂዉ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሁለት ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን በዚህም ትልቅ አድናቆትን ሲያገኝ ነበር።
ከዚህም ዉጭ ተጫዋቹ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ከፊላንድ ጋር የወዳጅነት እና ከፓርቱጋል እና ከሲዊዲን ጋር በኔሽንስ ሊግ ላለባት ጨዋታ ጥሪ ቀርቦለታል።
@live_score_football@live_score_football