~~የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓላት በዓመት 14 ናቸው
==> በመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
1ኛ ህዳር 12 የተሾመበት ዲያብሎስን ድል የነሳበት ህዝበ እስራኤል የመራበት እለት ነው።
2ኛ ህዳር 13 በዓለመ መላእክት ያሉ አእላፍ መላእክት በዓለ ሲመቱን ተሰብስበው ያከበሩበት ቀን ነው። ዕለቱ ምነአእላፍ መላእክት ይባላል።
3ኛ ታኅሣስ 12 ዱራታወስና ሚስቱ ቲወብስታን የረዳበት ዕለት ነው።
4ኛ ጥር 12 የደሃዋን ልጅ ተላፊኖስን የረዳበት ያዕቆብን ከወንድሙ ከኤሳው እጅ የጠበቀበት ዕለት ነው።
5ኛ የካቲት 12 የሚበላው የሚጠጣው የሚለብሰው ላጣ አንድ ሰው በሰው አምሳል ተገልጦ ከሀብታም ሲበደር ዋስ የሆነበት ሶምሶንን ረድቶ አህዛብን ያጠፋበት ዕለት ነው።
6ኛ መጋቢት 12 ማቴዎስ የተባለውን ሰው እና ሚስቱን ልጆቹን የረዳበት የበለአምን አህያ ያናገረበት ዕለት ነው
7ኛ ሚያዝያ 12 አዳምን ወደ ገነት ያስገባበት ኤርሚያስን ከእስር ቤት ያወጣበት ዕለት ነው።
8ኛ ግንቦት 12 ዳንኤል በአንበሳ ጉድጓድ ውስጥ ሳለ እንባቆምን ምግብ አስይዞ በአንዲት የእራስ ጠጉሩ አንጠልጥሎ ከኢየሩሳሌም ዳንኤል ወዳለበት ወደ ባቢሎን ወስዶ ዳንኤልን በጉድጓዱ ውስጥ የመገበበት ዕለት ነው።
9ኛ ሰኔ 12 ባህራንን ከባህር ያወጣበት አፎምያን ከሰይጣን ያዳነበት ዕለት ነው
10ኛ ሐምሌ 12 የደኀይቱን ልጅ ተለሀሶንን ከባህር አውጥቶ የጠበቀበት ንጉሥ ሰናክሬምን ከነሰራዊቱ ደምስሶ ጻድቁ ሕዝቅያስን ያዳነበት ዕለት ነው።
11ኛ ነሐሴ 12 ሶስናን ከእደ ረበናት ያዳነበት ንጉሥ ቆስጠንጢኖስን ረድቶ መክስምያኖስን ድል ያደረገበት ዕለት ነው።
12ኛ ጳጉሜን 3 ቅዱስ ሩፋኤል ያሳረገው የዕመቱን ጸሎት ዕጣን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብበት ዕለት ነው።
13ኛ መስከረም 12 ሰማዕቱ ፋሲለደስን የረዳበት ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ነቢዩ ሕዝቅያስ ሂዶ እንዲመክረው ያደረገበት ዕለት ነው።
14ኛ ጥቅምት 12 ነቢዩ ሳሙኤል ዳዊትን ቀብቶ እንዲያነግሰው የላከበትና ዳዊትን የረዳበት ዕለት ነው።
በዚህ በዓላት ወደ ፈጣሪው 14 ልመናዎችን ያቀርባል።
ቅዱስ ያሬድን የቅዱስ ሚካኤል ልመናዎች 14 እንደሆኑ ገልጿል።
ወአሰርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ በማለት ዘምሯል
14ቱ ልመናዎቹ በ 14ቱ በዓላቶቹ በጉልበቱ እየሰገደ ፈጣሪውን ለሰው ምህረት ይቅርታ እንዲደረግላቸው የሚለምናቸው ልመናዎች ናቸው።
እንግዲህ የቅዱስ ሚካኤል በዓላት በየወሩ የዓመት መሆኑን መርሳት የለብንም።
ወስበሐት ለእግዚአብሔር ይቆየን
https://t.me/Lordl