አምደ ሀይማኖት


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


በዚህ ቻናል ለአህዛብ እና መናፍቃን መልስ እንሰጣለን
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


.
#የፓስተሩና_የቄሱ_ወግ

ፓስተር... ኦርቶዶክሶች ማርያም አረገች የሚሉትን ተረት ሰምተሃል? አለው ለቄሴ

ቄሴ... "አዎ"
ፓስተር...."ይገርማል ግን እኮ ማርያም አላረገችም"

ቄሴ.... አለማረጓን እንደት አወቅህ?
.
ፓስተር....."መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማርያም አርጋለች" ስለማይል ነዋ።

ቄሴ...ትክክል ነህ ኦርቶዶክሶቹ ተሳስተዋል። ምክንያቱም ማርያም እንኳን ወደ ሰማይ ልታርግ ጭራሹንም እኮ አልሞተችም።

ፓስተር እንዴ...ያምሃል እንዴ?እንደት አልሞተችም ትላለህ? መሞትማ ሙታለች።

ቄሴ... እሺ ከሞተች ከመጽሐፍ ቅዱስ "ማርያም ሙታለች" የሚል አሳየኝ?

ፓስተር.... መጽሐፍ ቅዱስ ላይስ የለም።

ቄሴ እና መሞቷን በምን አረጋገጥክ?

ፓስተር "ሞታለችማ እሚለን ተአምረ ማርያም ነው" ብሎ እርፍ 😂😂😂

ቄሴ..ክክክ😂 አይ ፓስተር መሞቷን ከተአምረ ማርያም አንብበህ ስታምን ስለ እርገቷ የሚናገረውን ግን ማመን ለምን አቃተህ?

ፓስተር----ዝምምምምምምምምምምምምምምም
===============================
ቆይ ግን እነዚህ ሰዎች አዋልድ መጻሕፍትን እኛ ስንጠቅስ ተረት ተረት..... እነርሱ ሲጠቅሱ ደግሞ እውነት የሚሆነው በየትኛው ሕግ ነው???

ገጠመኜን ነው የጻፍኩላችሁ።።

እና ተሐድሶ ፕሮቴስታንቶች ሁሉ ጌታን እንዲቀበሉ እጸልያለሁ።

ክፍል 2 ይቀጥላ


@manetkelfares
@manetkelfares


🙏🙏🙏
#share ይደረግ




#ኑ_በእግዚአብሔር

ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን(፪)
ለታላቁ ክብር ለዚህ ላበቃን
ከሞት ወደ ሕይወት ላሸጋገረን
ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ደበለን

የሰማዩን መንግሥት እርስቱን ለሰጠን
ከጨለማ አውጥቶ ብርሃንን ላሳየን
ለዚህ ድንቅ ውለታው ምስጋና ያንሰዋል
በእርሱ ደስ ይበለን ክብር ይገባዋል
#አዝ
ከአለት የፈለቀ ውሃ ጠጥተናል
ሰማያዊ መና አምላክ መግቦናል
ፍቅርህ የበዛልህ ምን ልክፈልህ ጌታ
ስምህን ላመስግነው ከጠዋት እስከ ማታ
#አዝ
በቃዴስ በረሀ ምንም በሌለበት
በኤርትራ ባሕር ወጀብ በበዛበት
ለእርሱ መንገድ አለው ከቶ ምን ተስኖት
ልባችሁ አይፍራ በፍፁም እመኑት
#አዝ
በባርነት ሳለን በድቅድቅ ዓለም
ብርሃንን አገኘን በድንግል ማርያም
ያጣነውን ሰላም ዛሬ አገኘን
እጅግ ደስ ይበለን በእመቤታችን
#አዝ
የሐና የኢያቄም የእምነታቸው ፍሬ
በእግዚአብሔር ፈቃድ ተወለደችዛሬ
የኢያቄም ስዕለቱ የሐና እምነት
ለምኝልን ለኛ ኪዳነ ምሕረት


✞ላመስግንህ የእኔ ጌታ✞

ላመስግንህ የእኔ ጌታ ላመስግንህ
ልቀኝልህ የእኔ ጌታ ልቀኝልህ
ሕይወቴ ነው ዝማሬዬ ትሩፋቴ
የሰጠኸኝ እንዳከብርህ አንተ አባቴ(፪)

ከኔ የሆነ የምሰጥህ ባይኖረኝም
ከሰጠኸኝ የአንተን መስጠት አይከብደኝም
ጥበቤ ነህ የምስጋና መሠረቴ
ዝማሬዬን ያፈሰከው በህይወቴ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና
ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና(፪)
አዝ= = = = =
ባዶ እኮ ነኝ የእኔ ጌታ ምን ልቅዳልህ
በእጄ ላይ አንዳች የለኝ የምሰጥህ
ላንተ ክብር የሚመጥን ህይወት የለኝ
ዝማሬዬን በቸርነት ተቀበለኝ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና
ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና(፪)
አዝ= = = = =
ከምድር ላይ ከአፈር ስትፈጥረኝ
ከምስጋና የተለየ ምን ሥራ አለኝ
ቀን እና ሌት በመቅደስህ እቆማለሁ
አምላኬ ሆይ ሳወድስህ እኖራለሁ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና
ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና(፪)
አዝ= = = = =
ዕዝራ ስጠኝ የከበረ መሰንቆህን
ዳዊት ስጠኝ የሚፈውስ በገናህን
መዝሙር ቅኔ ተምርያለሁ ከአባቶቼ
ዘምራለሁ ባንተ ፍቅር ተነክቼ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና
ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና(፪)
መዝሙር
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

"እግዚአብሔርን አመስግኑ"
፩ ዜና ፲፮፥፷


ወእመአኮ

ወእመአኮ ከመወሬዛ ሀየል
ውስጠ አድባር ቤቴል
አዝ.........
ሀሌሉያ አበባ ነሽ ድንግል
" " " ግዜው ያላለፈ
" " " አብቦ ጠውልጎ
" " " ደርቆ ያልረገፈ
አዛኝ የለኝም ድንግል ሳለው በህይወቴ
ጡቶን ሳልጠግበው ድሮ ጥላኝ እናቴ
አንቻን የሰጠኝ ጌታ ይመስገንልኝ
ከንግዲ ወዲያ ካንቺ ማንም አይለየኝ
አዝ.......
ሀሌሉያ እኔም እንደ ኤፍሬም
" " " እንዳመሰግንሽ
" " " አመስግነኝ የሚል
" " " አሰሚኝ ከቃልሽ
አዛኝ የለኝም ድንግል-------

አዝ
ሀሌሉያ ማእበሉ ገፍቶ
" " " ቢታወክ ህይወቴ
" " " ሐመረ ኖህ ድንግል
" " " ሆንሺኝ መሰረቴ
አዛኝ የለኝም ድንግል-----

አዝ
ሀሌሉያ ሠባራውን ልቤን
" " " ደገፍሽው እንዲቆም
" " " ውለታሽ አያልቅም
" " " ብጮህ ለዘላለም
አዛኝ የለኝም ድንግል- - - - -




ሰባቱ መንጦላይት ወዴት ተጋረዱ
ሰባቱ መብራቶች ወዴት ተሰናዱ
ታናሽ ሙሽራ ነሽ የአሥራ አምስት ዓመት
በአንቺ ላይ ሲፈጸም እንግዳ ሥርዓት

አንዴ እየታጠቀ አንዴም እየፈታ
ገብርኤል ሲያበስርሽ በፍጹም ሰላምታ
ይኩነኒ ብለሽ ስትቀበይው
መለኮት እንዴት ነው የተዋሐደው
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል

አዝ = = = = =

ሁሉን የሚወስን ባንቺ ተወሰነ
ከሦስቱ አካል አንዱ ቃልም ሥጋ ሆነ
ስፋት እና ጥበት ሰማይ እና ምድር
ባንቺ ተገናኙ ገባሪና ግብር
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል

አዝ = = = = =

እንዴት ቢመርጥሽ ነው እንዴት ቢያከብርሽ
ትናንት እና ዛሬን ያገናኘብሽ
ምልዐትና ወሰን ግዝፈትና ርቀት
ባንቺ ተዋሐዱ ፈጣሪና ፍጥረት
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል

አዝ = = = = =

ምስጢር ሊመረምር ይወጣል ኀሊና
ያልፋል ይሻገራል ከሰማይ ደመና
ነገር ግን አይችልም ምንም ቢገሠግሥ
በመሰወሪያው ቀኝ ከልጅሽም ሊደርስ
ስለዚህ አቅቶት ደክሞት ይመለሳል
መልክዐ ውዳሴሽን በአድናቆት ያደርሳል

#ዘማሪ- ቀሲስ ምንዳዬ ብርሀኑ


እቴ ሙሽራዬ

እቴ ሙሽራዬ ሰለሞን ያለሽ
እኔም ልበልሽ እናቴ
እማምላክ ግቢ ከቤቴ
እኔም ልበልሽ እናቴ
ማርያም ግቢ ከቤቴ

ሁሉም ሰው ለራሱ ወንበር ሲዘረጋ
የክብርን ሽልማት ለራሱ ሲያስጠጋ
ድንግል እንደ ባሪያ ውሃ ተሸክመሽ
ጌታን በትህትና ታገለግያለሽ

ነይ በደመና (3)
እመቤታችን ርህርይተ ህሊና

ወርቀዘቦ ለብሰው በቤቱ ከሞሉት
በሀር እና በእንቁ ከተንቆጠቆጡት
በሠው ፊት ያማሩ ብዙ ሆነው ሳለ
ጌታ ግን ወደደሽ እናቴ ነሽ አለ

ነይ በደመና (3)
እመቤታችን ርህርይተ ህሊና

አሳድጎሽ ሳለ መልአኩ መግቦ
ተሸልመሽ ሳለ በዝቶልሽ ተውቦ
እጅግበትህትና ስላገለገልሽው
እንደ ኪሩብ መላክ ጌታን ተቀበልሽው

ነይ በደመና (3)
እመቤታችን ርህርይተ ህሊና

የባሪያውን ውርደት ተመልክቶልእና
የወለድሽው ንጉስ ይድረሰው ምስጋና
ከልብ የወጣ እንጂ ከንቱ ሆኖ አይደለም
ንፅይት እንላለን እኛም ለዘላለም






አይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ (2)
ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ (2)




ጎሳ ልብየ
ጎሳ ልብየ ቃለ ሠናየ/2/
ወአነ አይድ ቅዳሴሀ ለማርያም /2/
አዝ
እኔስ የማርያምን ውዳሴዋን እናገራለው
እንዳባቴ ዳዊት በበገና እዘምራለው
ቀን ከለሊት ሳልል በምስጋና እተጋለሁ
የሀጥያቴ ቁስል እንዲፈወስ እጮሀለሁ
ምርኩዜ ነሽና እመቤቴ ባንቺ እመካለሁ
አዝ
ኦ እመቤቴ በእውነት እንወድሻለን
የእዉነተኛ መብልን ክርስቶስን ወለድሽልን
ምክንያተ ድሂን ሆይ ድንግል ማርያም የአምላክ መገኛ
በአማላጅነትሽ በመታመን እንጮሀለን እኛ
ምህረትን አሰጭን ኪዳነምህረት የአለም መዳኛ
አዝ
ስለ ቸርነትሽ እመቤቴ ለኔ እናቴ ነሽ
ስለ ንግስትነትሽም እመቤቴ ነሽ
ዝናብ ሳያጠጡት አየራትም ሳያሳድጉት
ሰማያዊ እንጀራ የሰጠሽን ቤቴልሄማዊት
ቅድስተ ቅዱሳን የኖህ መርከብ የአምላክ እናት
አዝ
ቃና ዘገሊላ በሰርጉ ቤት በዚያ ተገኝተሽ ሳለሽ
ውሀውን ወደ ወይን ባንቺ ምልጃ እንዳስለወጥሽ
ዛሬም የኔ ህይወት ወይኑ አልቆ ባዶ ሆኗልና
አንቺ የአምላክ እናት ንፅህት ንግስት ርህርተ ህሊና
ህይወቴን አንፅተሽ ቀድሰሽ ሙይው በምስጋና

ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ










በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን🙏🙏🙏

ሰላም የልዑል እግዚያብሄር ቤተሰቦች የእመቤታችን የድንግል ማርያም የአስራት በኩራት የአደራ ልጆች እንደምን ቆያችሁ 👋👋

ይህ ቻናል ከዛሬ ጀምሮ የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ፣የመዝሙር ግጥሞች፣ትረካዎች፣ግጥሞች፣ እንዲሁም በዋነኝነት ለመናፍቃን እና አህዛብ ምላሽ የምንሰጥበት ይሆናል

ስለዚህ ሁላችሁም ቢያንስ ለ5 ሰዎች share በማድረግ ይህ ቻናል ላልደረሳቸው ሰዎች በማዳረስ ይተባበሩን ዘንድ በእግዚያብሄር ስም እንጠቃለን



Показано 20 последних публикаций.

212

подписчиков
Статистика канала