ማቲያስ ዴሊት በጥሩ ሁኔታ እያገገመ ይገኛል !
ኔዘርላንዳዊው ተከላካይ ማቲያስ ዴሊት ከገጠመው የረዥም ጊዜ ጉዳት በጥሩ ሁኔታ እያገገመ መሆኑ ተገልጿል።
ዴሊት ቀዶ ጥገና ካደረገ በኃላ በታቀደለት መልኩ በኤቢዛ ከተማ የሚገኝ ሲሆን የማገገሚያ ሂደቶቹን ተከትሎ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደገለፁት የተጫዋቹ የማገገሚያ ሂደት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ሲሆን ተጫዋቹ በሚቀጥለው ሲዝን መጀመሪያ ላይ ወደ ጨዋታ ለመመለስ ግብ አስቀምጦ እየሰራ መሆኑ ተነግሯል።
ዘገባው የሳሙኤል ሉክኸርስት ነው።
@Manutdethionews