Mayor Office of Addis Ababa


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ይህ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የቴሌግራም ገፅ ነው፡፡
ከተማችን አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ፣ ውብና ለነዋሪዎቿ የተመቸች እንድትሆን እንሰራለን፡፡

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций










በፈተና ውስጥ ሆነንም በርካታ አንፀባራቂ ድሎችን እያስመዘገብን ተጉዘናል!
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
በዛሬው እለት እየተከናወነ ባለው የጋራ መኖርያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ስነስርዓት ላይ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች
👉 ባለፉት ጊዜያት ከውስጥም ከውጪም የነበሩብን ችግሮች ገሚሱም አድምቶን፤ ገሚሱም አበርትቶንና አስተምሮን አልፏል።

👉 ሆኖም በፈተና ውስጥ ሆነንም በርካታ አንፀባራቂ ድሎችን እያስመዘገብን ተጉዘናል፤

👉 እነኚህ ዛሬ እጣ የምናወጣባቸው ቤቶች በበርካታ ችግሮች ማለትም የፋይናንስ እጥረት ፤ የመሰረተ ልማት አቅርቦት ፤ የግንባታ እቃዎች ዋጋ መናርና እጥረቶች ፤የተቋራጭ መጥፋትና ሌሎችም ችግሮች የተወሳሰበ ቸግሮችን አልፏል፡፡

👉 ይህንን ችግር ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ከንግድ ባንክ በብድር በመውሰድ ለእጣ ብቁ እንዲሆኑ የተደረገበት ነው፡፡

👉 በሌላ በኩል ደግሞ በእነኚሁ ቤቶች የእጣ አወጣጥ ስነስርዓት ሂደት ባጋጠመን የሌብነትና የማጭበርበር ድርጊት ምክንያት እጣው እንዲሰረዝና እንዲጓተት መደረጉ ነው፡፡

👉 በተለይ ለረጅም ዘመናት በትዕግስት ሲቆጥብና ሲጠባበቅ ለነበረው ህዝባችን አሳዛኝ ዜና ነበር፡፡ በሂደቱም መንግስትና ህዝብን በማቃቃርና አለመተማመን የሚፈጥርና ፖለቲካዊ አንድምታ የነበረው ድርጊት ነበር፡፡

👉 የከተማ አስተዳደሩ ችግሩን ለመፍታት በታማኝነት በግልፀኝነትን ተጠያቂነት ለማስፈንም ተገደናል፡፡ በዚህ ድርጊ የተሳተፉ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ የህዝብ ሃብት ከዝርፊያ ማዳን ተችሏል፡፡

👉 ከሁሉም በላይ ግን ትልቁ ስራ የነበረው ህዝባችን ውስጥ የተፈጠረውን አለመተማመንና ጥርጣሬ ለመቅረፍ እና የማያዳግም ስራ በመስራት የህዝባችንን እምነት ለመመለስ የሄድንበት መንገድ ነው፡፡

👉 ይህንን ኢ-ፍትሃዊነት ድርጊት ለመከላከል የቤት ዕጣ ማውጫ ሲስተሙን በአዲስ መልክ ከፍተኛ ልምድ ባለዉና ሪፎርም ባደረገው በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) እንዲለማና የሴኪዩሪቲ ደህንነቱ እንዲረጋገጥ ተደርጓል፡፡

👉 አዲስ የበለፀገውንም የዕጣ ማውጫ ሲስተም ፍተሻ ለማድረግ (አርተፊሻል ኢንተለጀንስ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ፣ ከከተማና መሰረተ ልማት ሚንስቴር) የተውጣጡ አምስት ሙያቸው የተመሰከረላቸው ባለሙያዎች ቴክኒካል ኮሚቴ በማቋቋም የለማውን ሶፍትዌር የማረጋገጥና ተችሏል፡፡

👉 ለእጣ ከመቅረቡ በፊት የቅድመ ኦዲት ስራ በመስራት የከተማ አስተዳደራችን አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ በማድረግ በፍትሃዊነት ለህዝባችን እጣ መውጣት እንዲችልና ለዛሬ ቀን እንዲበቃ ማድረግ ችለናል፡፡

👉 ይህ አይነት የዝርፊያና የህዝብን ሃብት ለግል ጥቅም የማዋል ዝንባሌና ተግባር በቤቶች ስራ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም መስኮች ዋነኛ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡

👉 ሌብነትና ብልሹ አሰራር የብልፅግና ጉዟችን ዋነኛ ፀርና የምንመኘውን የህዝብ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዳናረጋግጥ ትልቁ ጋሬጣ ነው፡፡

👉 የከተማችንም አስተዳደር ይህንን ከግምት በማስገባት የፀረ ሌብነት ትግሉ የቀጣይ ዋነኛ የርብርብ ማእከል በማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

👉 ህዝቡን እያሳተፍን ለሌብነት የማይመች ነባራዊ ሁኔታን በመፍጠር አስተማሪ እርምጃን እየወሰድንና ህዝባችንን በስፋት እያሳተፍን መሄዳችንን እንቀጥላለን፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ተጀምሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለባለ ዕድሎች መልካም እድል ይመኛል


ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ እየተገነባ ያለውን የተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን የመኖርያ ቤት ችግር ለመፍታት የተለያዩ አማራጭ እቅዶችን በመንደፍ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል፡፡

ከነዚህም መሃከል በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የ10ሺህ ተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ ሞዳሊቲ አንዱ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት በቦታው ላይ አጋጥሞ በነበረ የፍርድ ቤት እግድ ምክንያት ተቋርጦ የነበረና አሁን ግን በከፍተኛ ፍጥነት ግንባታው እየቀጠለ ያለ ፕሮጀክት ነው፡፡

ከንቲባዋም በቦታው ተገኝተው ግንባታው ስላለበት ሁኔታ የመስክ ምልከታ በማድረግ ግንባታው ስለሚፋጠንበት ሁኔታ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘውም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዮናስ አያሌውም በበኩላቸው የተጀመሩትን ግንባታዎች ድርጅታቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ ገልፀው አዳዲስ ብሎኮችንም በቅርቡ ውስጥ እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በዚሁ ወቅት የቤት ልማት ስራ መንግስት የተለያዩ አማራጮችን ማስቀመጡን አውስተው የቤት ፈላጊዎችና የግል ባለሃብቶች በነዚህ አማራጮች በመጠቀም በቤት ልማት ላይ ተሳትፎ ያደርጉ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 14ኛ ዙር እና የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት እጣ በነገው እለት ህዳር 6/2015 ዓ/ም በይፋ ስነስርዓት ያወጣል፡፡

በዛሬው እለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ የ20/80 14ኛ ዙር እና የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት እጣ የማውጣት ስነስርዓት በነገው እለት ከሰዓት በኋላ ከ8 ሰዓት ጀምሮ እንደሚያካሂድ ተገልጿል፡፡

በመግለጫው ወ/ት ያስሚን ዋሃቢረቢ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ እንደገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1/2014 ዓ.ም. የ20/80 14ኛ ዙር እና የ40/60 3ኛ ዙር የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በይፋ ማካሔዱ አስታውሰዋል ሆኖም ባጋጠመ የወንጀል ጥቆማ መሰረት በተደረገ ኦዲት እጣው ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዝ ተደርጎ በጉዳዩ የተጠረጠሩ አካላትም በህግ አግባብ እንዲጠየቁ መደረጉን አንስተዋል፡፡

በዚህም መሰረት በሁለቱም የጋራ መኖሪያ ቤት ፕሮግራም ማለትም በ20/80 18,930 ቤት እና በ40/60 6,843 ቤቶች በድምሩ 25,791 ቤቶች እጣ የሚወጣባቸው ሲሆን ቀደም ብሎ ከፍተኛ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረውን የባለ 3 ሶስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎችን ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ 300 መቶ ቤቶችን ቀሪ ስራ በማከናወን ለነባርና አዲሰ ተመዝጋበዎች በእጣ ለማስተላለፍ ዝግጁ መደረጉን ወ/ት ያስሚን ገልፀዋል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሄዱ።

የመወያያ ሰነዱም በዋናነት በሰላም የተገኘውን ድል በላብ ማፅናት ፣በምግብ ዋስትና ራስን ለመቻል የከተማ ግብርናን ከሌማት ትሩፋት ተልዕኮ ጋር በማስተሳሰር ለስኬት መረባረብ በሚያችሉ አጀንዳዎች ሲሆኑ ፣ የሀገራችን ፈተና የሆነውን የዋጋ ግሽበትን መከላከል ፣ ለሠላም ስምምነቱ ተፈፃሚነት መረባረብ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ዙሪያ ከነዋሪው ጋር ውይይት ተደርጓል።

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማጠቃለያው እንደተናገሩት ሠላም ሲኖር ነው ያሰብነውን የምናሳካው፣ሠላም ሲኖር ነው ሀገራችንን የምናበለፅገው በሠላም ያስመዘገብነውን ድል በኢኮኖሚው ዘርፍ በማፅናት ሀገር መገንባት ያስፈልጋል ሲሉ በኩታ ገጠም የተዘሩ አዝዕርቶችን ይበልጥ በማስቀጠል በምግብ ራስ የመቻል ስነልቦናን ማዳበር፣ከምንግዜውም በላይ ደግሞ ከሌማት ቱርፋት ስራዎች አንጻር ልዩ ትኩረት ሠጥቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን አክለውም በክፍለ ከተማው እየተከናወኑ ያሉ የሌማት ትሩፋት የሆነው የሠብል ምርቶችን ለማስፋት አርሶአደሩን ማገዝ እንዲሁም በ90 ቀን የሚተገበሩ ተግባራትን ልዩ ክትትል በማድረግ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

Показано 9 последних публикаций.

2 505

подписчиков
Статистика канала