Репост из: Bahiru Teka
👉 የመርከዙ ሰዎች የተምዪዕ ማረጋገጫ
ክፍል አራት
የማግራራት አካሄድ ( منهج التساهل )
የኢብኑ መስዑድ ሰዎች ከነበሩበት ዐቂዳ ለመንሸራተታቸውና የሰለፍያ ዳዕዋ ባለበት ማስኬድ ሙተሸዲድነት ነው ብለው ወደ ማግራራት አካሄድ ለመሄዳቸው የተወሰኑ ነጥቦችን እናያለን ። እንደ ሚታወቀው የተውሒድ ዳዕዋ ሲጀመር ከዳር እስከ ዳር ወጣቱ ወደ ተውሒድ አስተምሮ እየተመመ ሰላሰቱል ኡሱል ፣ ኪታቡ ተውሒድ ፣ አል ኢረሻድና የመሳሰሉ ኪታቦች በየገጠሩ ጭምር እየተቀሩ ሽርክ ወደ መቃብር ሊወርድ ሲቃረብ ኢኽዋኖች እንባ ጠባቂ ሆነው ነው ያተረፉት ። ኪታቡ ተውሒድ ውስጥ ከተካተቱ ባቦች አንዱ :–
ባቡ ማ ጃአ ፊል ሙሰዊሪን ( ምስል ቀራጮችን አስመልክቶ የመጡ ዛቻዎች ) የሚለው ይገኝበታል ።
ይህ ባብ ሁሉም ዳዒ ወይም ኡስታዝ አይኑ ቀልቶ ጡንቻው ተገታትሮ ፎቶ ሐራም ነው ። የኑሕ ህዝቦች ሽርክ ውስጥ የገቡት በምስል አማካይነት ነው እያለ ወጣቱ ዓእምሮ ውስጥ የፎቶ ሐራምነት በማስረፅ በጣም አስፈላጊ ለሆነ ጉዳይ ብቻ ያውም እየቀፈፈው ፎቶ እንዲነሳ አድርገው ነበር ። ከእነዚህ ኡስታዞች አብዛኞቹ የኢብኑ መስዑድ መርከዝ ኡስታዞች ነበሩ ።
ቴሌቪዥን ሐራም ነው አላህን ፍሩ ቤታችሁ እንዳታስገቡ ።
ቪዲዮ ሐራም ነው ። እየተባለ ነበር ዳዕዋ ሲደረግ የነበረው ። እንኳን ዳዒዎች ሊቀረፁ ኢኽዋኖች በቴሌቪዥን ቻናል ሲመጡ ረድ ይደረግ ነበር ። ያኔ !!!!
🔹 ከተወሰኑ አመታት ጀምሮ የመርከዙ ሰዎች ፋሽኑ ያለፈበትና ኢኽዋኖች የሰለቹትን የማግራራት አካሄድ በመጠቀም የቴሌቪዥን ጣቤያ በመክፈት በሱና ላይ ሆነው ቤታቸው ከቴሌቪዥን እርቆ አላህን በመፍራት ላይ የነበሩትን እነእገሌ በቴሌቪዥን ሊቀርቡ ነው ። በማለት የሱና ቤቶች በዲሽና በቴሌቪዥን እንዲጨናነቁ አደረጉ !!!!! ።
🔹 በዚህ አላበቃም የማግራራት አካሄዱ ወደ አሶሳ የነበረውን የዳዕዋ ጉዞ ከኤርፖርት ጀምሮ በክላክስና በፉጨት ታጅቦ እየተቀረፁ ከተማ አቋርጠው ሲሄዱ ቀርፀው ለህዝብ አስተዋወቁ ። በዚህም ኢኽዋንን አስናቁ ።
🔹 ቀጠለ በዚህ አላበቃም በየክፍለ ሀገሩ ወንድና ሴት መሀል ሆነው ዳዕዋ ሲያደርጉ እየተቀረፁ በሚዲያ ላይ ለቀቁ !!!! በዚህም ወደ ኢኽዋን የቀረቡ መሆናቸውን አስመሰከሩ ።
🔹 ጉዱ በዚህ አላበቃም ኢኽዋንን ኮቴ በኮቴ እየተከተሉ የማስናቁን ስራ ቀጥለውበት ረመዳን ላይ የጎዳና ኢፍጣር ብለው አምስት ገዳናዎችን በመዝጋት ሰዎችን መተላለፊያ በማሳጣት ሸሪዓውን በጣሰ ኢኽዋንን ባስናቀ መልኩ ወንድና ሴት በተቀላቀለበት ድሀው ከሀብታሙ በማይታወቅበት የፖለቲካ ፉክክር አሸናፊ መሆናቸውን ቀርፀው ለህዝቡ ዒባዳ ነው ብለው አስተዋወቁ ።
በዚህ መልኩ ከነበሩበት ጠንካራ የሰለፍያ አቋም ወጥተው በስሙ በመነገድ በየጊዜው ከሰለፍያ አካሄድ እየራቁ ወደ ኢኽዋን እየተጠጉ አልፈው ሊሄዱ ጫፍ ላይ ደርሰው ነው ያሉት ። አላህ ካለ በሚቀጥለው ክፍል ወሳኙና ከሰለፍያ በፍቃደኝነት የወጡበትን ዋናውን መሰረታዊ ነጥብ ይዤ እመለሳለሁ ።
አላህ ሐቅን አውቀው ከሚቀበሉትና ባጢልን አውቀው ከሚርቁት ያድርገን ።
https://t.me/bahruteka