Репост из: Bahiru Teka
🔷 ወደ አላህ ሽሹ !!!!
በተለያየ የሀገራችን ክፍል በተለይ በሰሜንና ምእራቡ ያላችሁ ወንድምና እህቶች አባቶችና እናቶች ስቃዩና መከራው በየቀኑ እየጨመረ ይነጋል ሲባል እየጨለመ በሚመስል ሁኔታ ትክክለኛው ያላችሁበት ስሜት እናንተና አላህ ብቻ የምታውቁት ሲሆን ምድር ከመስፋትዋ ጋር የጠበበች ብትመስላችሁም የአላህ ፈረጀት ይመጣል ። አብሽሩ !!!!
በጭንቀት መሪነት እግራችሁ ወዳቀናበት ብትሸሹም በዋነኝነት በልባችሁ ወደ አላህ ሽሹ !! የፀፀት እንባ አንቡ !! ከሱ በስተቀር መጠጊያም መመኪያም ያለ መኖሩ እወቁ !! ከመከራ በኋላ ፈረጀት ፣ ከጥበት በኋላ የእዝነት ስፋት ከፅልመት በኋላ ንጋት መኖሩን አስታውሱ ።
በምድር ላይ የሚከሰት ማንኛውም በላእ በየብስም ይሁን በባህር ምክንይቱ የሰው ልጆች ሀጢያት ቢሆንም ከአላህ ነው ። ይህን አስመልክቶ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል : –
" وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ الْقُرَىٰ آمَنُوا وَاتَّقَوْا لَفَتَحْنَا عَلَيْهِم بَرَكَاتٍ مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ وَلَٰكِن كَذَّبُوا فَأَخَذْنَاهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ
الأعراف" ( 96 )
" የከተማዋም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር ፡፡ ግን አስተባበሉ ፡፡ ይሠሩት በነበሩትም ኃጢኣት ያዝናቸው ፡፡"
አሁንም በሌላ የቁርኣን አንቀፅ እንዲህ ይለናል : –
" ظَهَرَ الْفَسَادُ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِي النَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ الَّذِي عَمِلُوا لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ
الروم " ( 41 )
" የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተገለጠ ፤ (ተሰራጨ) ፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና ፡፡"
አላህ ይህን መከራና ጭንቀት ያመጣበትን ምክንያት ሲነግረን የሰዎች እጆች በሰሩት ሀጢያት ነው ይለናል ። በዚህ መከራ የተፈለገው ደግሞ የእነርሱ ከወንጀል መመለስ ነው ። ተመልከቱ የአላህ እዝነቱ ባሮቹ ባሉበት ወንጀል ትቷቸው የእሳት ቅጣት እንዳያገኛቸው በዱንያ ላይ መከራ አቅምሷቸው ተመልሰው የሱ ትክክለኛ ባሮች እንዲሆኑና ዘላለማዊው የተድላ ሀገር እንዲወርሱ ነው ። ሱብሃናላህ !!!!!!
ለዚህ ነው አላህ የኑህ ሕዝቦችን በመልእክተኛቸው አማካኝነት በሱ ላይ ከማጋራት ወጥተው ወደርሱ እንዲሸሹ ያዘዛቸው ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይለናል : –
" فَفِرُّوا إِلَى اللَّهِ ۖ إِنِّي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ مُّبِينٌ "
الذاريات ( 50 )
« ወደ አላህም ሽሹ፤ እኔ ለእናንተ ከርሱ" ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝና» (በላቸው) ፡፡
" وَلَا تَجْعَلُوا مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ ۖ إِنِّي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ مُّبِين ٌ"
الذاريات ( 51 )
" ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አታድርጉ ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ (የተላክሁ) ግልጽ አስፈራሪ ነኝና ፡፡"
ከዓባስና ዐልይ – ረዲየላሁ ዐንሁማ – በተያዘ አሰር እንዲህ የሚል መጥቷል : –
" ما نزل بلاء إلا بذنب ولا رفع إلا بتوبة "
በላእ አልተከሰትም በሀጢያት ቢሆን እንጂ አልተነሳምም በተውበት ( በፀፀት )
እንጂ
ስለዚህ የዚህ በላእ መፍትሄ ወደ አላህ መሸሽ ፀፀት አድረጎ መመለስ ወደርሱ ማልቀስ ነው ።
የበላእ ምክንያቱ ሀጢያት ነው ሲባል የግድ ሁሉም ሀጢያተኛ ነው ማለት አይደለም ። በህዝቦች መካከል ወንጀል ሲንሰራፋ ፣ ግፍ ሲበዛ ፣ በደል ሲስፋፋ ተዉ የሚል ከሌለ የሚመጣው በላእ ሁሉንም ይነካል ። ይህንንም አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ በማለት ይነግረናል : –
" وَاتَّقُوا فِتْنَةً لَّا تُصِيبَنَّ الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنكُمْ خَاصَّةً ۖ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَاب ِ"
الأنفال ( 25 )
" ከናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ ፡፡ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን እወቁ ፡፡"
በመሆኑም አሁንም ወደ አላህ የመመለሻው ጊዜ አለ በስደት ላይ ሆነን ወንጀል መስራት ሳይሆን ተውበት አድርገን መመለስና አላህን መገዛት አለብን ። የመጣውን በላእ አንሱልን ብሎ ለቆሌ ፣ ለአድባር ፣ ለሙታን ፣ መለመንም ሆነ መማፀን በላኡ አንዲብስ የሚያደርግ ተግባር ስለሆነ መራቅ ይኖርብናል ። ሌሎቻችን ደግሞ ወገኖቻችንን በቁሳዊ ነገር መርዳት የማንችል በዱዓእ ስስታም አንሁን ። አላህ ሀገራችንን ሰላም እንዲያደርግልን ህዝቦቿንም ከመከራ እንዲያወጣልን ልንለምነውና ሁሌም ልንማፀነው ይገባል ።
https://t.me/bahruteka