قناة السنة سفينة نوح


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


የተለያዩ ኢስላማዊ ዳዓዋዎች እና የትላልቅ መሻይኮች ፈትዋ በማስራጨት ላይ ትኩረት ያደረገ ቻናል ነው #Join እና ሸር ሽር ያርጉት ሌሎች ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ!!
Wasapp?
https://chat.whatsapp.com/APqfHCy23fgH1EhS7dioRr
Telegram?
https://t.me/Menhaj_Salafiya

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከጭፍን ተከታይነት መጠንቀቅ

ከሱንና ሰዎች አበይት መገለጫዎች ውስጥ አንዱ የፈለገ ቢገንኑ ለዑለማዎች ጭፍን ወገንተኛ አለመሆን ነው፡፡ የፈለገ ብንወደው ማንም ቢሆን የተናገረው ሁሉ ልክ አይሆንም፡፡ ስለሆነም ለማንም ጭፍን ወገንተኛ ልንሆን አይገባም፡፡ ዑለማዎቻችንን ስለወደድናቸው ብቻ ንግግራቸውን እንደወረደ አንወስድም፡፡ ይህንን በተግባር ያስተማሩን እራሳቸው ዑለማዎቹ ናቸው፡፡ ለአብነት ያክል የአራቱን አኢማዎች ንግግሮች እዚህ ላይ ላስፍር፡-

[ሀ] አቡ ሐኒፋ ረሒመሁላህ፡-

1. “አንድ ሐዲሥ ትክክለኛ ከሆነ መዝሀቤ እሱ ነው፡፡”
2. “ከየት እንደወሰድነው ካላወቀ ለማንም አቋማችንን ሊወስድ አይፈቀድለትም፡፡”
3. “ማስረጃዬን ያላወቀ ሰው በኔ ንግግር ፈትዋ ሊሰጥ ሐራም ነው፡፡”
4. “እኛ ሰዎች ነን፡፡ አንድ ንግግር ዛሬ እንናገርና ነገ ከሱ እንመለሳለን፡፡”
5. “የላቀውን አላህ መፅሐፍና የመልእክተኛውንﷺ ንግግር የሚፃረር ንግግር ከተናገርኩኝ የኔን ንግግር ተውት፡፡”

[ለ] ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁላህ፡-

1. “እኔ ሰው ነኝ፡፡ እስታለሁ፣ አገኛለሁ፡፡ ስለዚህ እይታየን ተመልከቱ፡፡ ቁርኣንና ሱንና ጋር የገጠመውን በሙሉ ያዙት፡፡ ቁርኣንና ሱንና ጋር ያልገጠመውን ተውት፡፡”
2. “ከነብዩ ﷺ በስተቀር ንግግሩ የሚያዝለት ወይም የሚመለስበት ያልሆነ አንድም የለም፡፡”
3. “ከነብዩ ﷺ በኋላ ከንግግሩ የሚያዝና የሚተው ያልሆነ አንድም የለም፡፡ ነብዩ ﷺ ሲቀሩ፡፡

[ሐ] ኢማሙ አሽሻፊዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-

1. “አንድ የነብዩﷺ ሱንና የተገለፀለት ሰው ለማንም ንግግር ሲል እሷን (ሱንናዋን) መተው እንደማይፈቀድለት ሙስሊሞች በሙሉ ኢጅማዕ አድርገዋል፡፡”
2. “በኪታቤ ውስጥ ከአላህ መልእክተኛﷺ ሱንና የሚፃረር ነገር ካገኛችሁ የአላህ መልእክተኛንﷺ ሱንና ተከተሉ፡፡ የኔን ንግግር ተውት፡፡”
3. “ሐዲሥ ትክክለኛ (ሶሒሕ) ከሆነ መዝሀቤ እሱ ነው፡፡”
4. “እኔ ከተናገርኩት በተቃራኒ በዘርፉ ምሁራን ዘንድ ከአላህ መልእክተኛﷺ ትክክለኛ ዘገባ የመጣበት ርእስ ሁሉ እኔ በህይወት ሳለሁም ሆነ ሞቼ ከሱ ተመልሻለሁ፡፡”

[መ] ኢማሙ አሕመድ ረሒመሁላህ፡-

1. “የአውዛዒይ አስተያየት (ረእይ)፣ የማሊክም አስተያየት፣ የአቡ ሐኒፋም አስተያየት ሁሉም አስተያየት ነው፣ እኔ ዘንድ፡፡ መረጃ ያለው ከነብዩ ﷺ እና ከሶሐቦቹ ቅሪት ዘንድ ነው፡፡”
2. “ማሊክንም፣ ሻፍዕይንም፣ አውዛይን፣ ሠውርይን በጭፍን አትከተል፡፡ እነሱ ከያዙበት ያዝ፡፡”
እነዚህንና መሰል ወርቃማ ንግግሮችን ከሸይኹል አልባኒ ረሒመሁላህ “ሲፈቱ ሶላት አንነቢይ” ኪታብ መግቢያ አካባቢ ማግኘት ይቻላል፡፡

ወንድሜ ሆይ! እህቴ ሆይ! እኛ ከዚህ ምን እንማራለን? ከማስረጃ ጋር አገናዝበን ሳይሆን የምንወደው ሸይኽ ስለተናገረ ብቻ የምንነፍስበት ጊዜ የለንም? አሁንስ ተመሳሳይ ስህተት ላለመድገም ዝግጁ ነን? ለራሳችን እውነተኛ እንሁን፡፡
ከላይ ያለፉትን ንግግሮች በአንክሮ እናስተውል፡፡ የህይወታችን ቋሚ መመሪያም እናድርጋቸው፡፡ “ማሊክንም፣ ሻፍዕይንም፣ አውዛይን፣ ሠውርይን በጭፍን አትከተል” የሚለውን የኢማሙ አሕመድ ንግግር አስተውለነዋል? እነዚህን የኡማው ከዋክብት በጭፍን መከተል ካልተፈቀደ ከነሱ በእጅጉ የሚያንሱትንስ በጭፍን መከተል ይፈቀዳልን? ጤነኛ ከሆንክ መልሱ አይጠፋህም፡፡ እናም በተመሳሳይ እንበል፡፡
- ኢብኑ ተይሚያንም፣ ኢብኑል ቀይምንም፣ ኢብኑ ኪሠርንም፣ ዘሀቢንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወህሃብንም፣ ዐብዱርረሕማን ኢብኑ ሐሰንንም፣ ዐብዱልለጢፍ ኣሊ ሸይኽን፣ ሰዕዲንም፣ ሙሐመድ ኢብኑ ኢብራሂንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- ኢብኑ ባዝንም፣ አልባኒንም፣ ኢብኑ ዑሠይሚንንም፣ ሙቅቢልንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- ፈውዛንንም፣ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድንም፣ ጃሚንም፣ መድኸሊንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- በሰፈርህ፣ በአካባቢህ፣ በሃገርህ ያሉ መሻይኾችንም፣ ተማሪዎችንም የፈለገ ብትወዳቸው በጭፍን አትከተል፡፡ የሐቅ መለኪያ ሚዛንም አታድርጋቸው፡፡ ማንም ይሁን ማን፡፡
እዚህ ላይ ይህ ፅሑፍ ዑለማን ከማክበርና ትንታኔያቸውን ከመጠቀም ጋር የሚፃረር የሚመስለው ካለ የፅሑፉን መልእክት ፈፅሞ አልተረዳም፡፡ የዚህ ፅሑፍ አላማ ግለሰቦችን የሐቅ መለኪያ በማድረግ ሊከሰት ከሚችል ፈተና መጠንቀቅ እንደሚገባ ማሳሰብ ብቻ ነው፡፡ እንጂ የቁርኣንና የሐዲሥን ማብራሪያ የምንወስደው ከዑለማዎች እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ ሆኖም ግን የአንዱ ዐሊም ትንታኔ ከሌላው የሚፃረርበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም በጭፍን ልንከተል እንደማይገባ የሚያሳይ ነው፡፡ ዛሬ ግን ታላላቅ መሻይኾችን ቀርቶ በአካባቢያቸው የሚገኙ ዝቅ ያሉ አስተማሪዎችን ጭምር በጭፍን በመከተል የወደዱትን የሚወዱ፣ የጠሉትን የሚጠሉ፣ የነኩትን የሚነኩ፣ የፈቀዱትን የሚፈቅዱ፣ የከለከሉትን የሚከለክሉ፣ ያስጠነቀቁትን የሚያስጠነቅቁ ብዙ ናቸው፡፡ የሚከተሏቸው ሰዎች በሆነ ምክንያት አቋም ሲቀይሩም ያለምንም ማገናዘብ ሰልፋቸውን በመቀየር ዥዋዥዌ ይጫወታሉ፡፡ ይሄ ፈፅሞ ሊሆን አይገባም፡፡ አላህ ማስተዋሉን ያድለን፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 07/2010)


#ለልጆችዎ_መስተካከል_ወሳኝ_ምክር_እንዳያመልጥዎት

ልጆችዎ መልካም ይሆኑ ዘንድ አስፈላጊ እርምጃዎችን ሊያጠኑና ሊተገብሩ ይገባል። ለልጆች ሂዳያና መስተካከል መጨነቅ የነብያትና የሷሊሆች ፈለግ ነው።

የነብዩ ኢብራሂምን ዱዓ ያስተውሉ፤
رَبِّ اجْعَلْنِي مُقِيمَ الصَّلَاةِ وَمِنْ ذُرِّيَّتِي ۚ رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَاءِ

«ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ዘሮቼንም (እንዲሁ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ

የኢልም አርበኛ የሱና ታጋይ የነበሩት ሸይኽ ሀሙድ አቱወይጅሪይ (ረሂመሁላህ) ብዙ ልጆች ሲኖሯቸው ሁሉም በዲናቸው ጠንካሮች አላህን ፈሪ ሷሊሆች ናቸው። አንድ ተማሪያቸው የግል ጥያቄ ልጠይቆትና የዚህ ምክኒያቱ ምንድነው ብሎ ሲጠይቃቸው፦ ፈገግ አሉና "ለይል ሰግጄ አላህ መልካም ልጆች ያደርግልኝ ዘንድ ዱዓ አደርጋለሁ" በማለት መለሱ።

እባክዎን ለልጆችዎ ዱአ ከመድረግ አይቦዝኑ። ለልጆች መላካም አስተዳደግ ተርቢያ ትኩረት ሰጥቶ ዱአ ማድረግ የትኛውንም አይነት ምድራዊ ምቾት ከሟሟላት በበለጠ ለልጆችዎ የሚውሉት መልካም ውለታ መሆኑን ይገንዘቡ።

http://t.me/Menhaj_Salafiya


አንተ ኢኽዋነል ሙፍሲዲን ሆይ?!
ባለህበት ሂድ በሰለፎች ለይ ጣትህን አትቀስር!!
http://t.me/Menhaj_Salafiya






Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
حكم دفع الرشوة لأجل الحصول على وظيفة الشيخ/ سليمان الرحيلي وفقه الله

📌قناة سفينة نوح الدعوية
t.me/Menhaj_Salafiya


Репост из: MuhammedSirage M.Nur.
የአማኞች ፣ የከሃዲያን እና የእንስሶች ደስታ

መልካሙን የተለመደውን በመጠጣትና በመመገብ ፣ በማግባትና ጠቃሚ የሆኑ የዱንያ ቁሶችን እጅ ውስጥ በማስገባት በተለያየ ግዜ ደስታን እንገበያለን።
እነዚህን ወቅታዊና ጎዶሎ ደስታዎች ደግሞ ከሃዲያን እና እንስሶች ይጋሩናል! !
በኢማን ፣ አላህን በመፍራትና ሸሪዐዊ አውቀትን በመፈለግ የሚገኙትን እውቀቶች ግን የኢማንና የተቅዋው ባለቤት ብቻ ይቋደሳቸዋል ! ! ከሃዲያን አያወቁትም!! ወንጀል ውስጥ የሚዘውትሩ አመፀኞችም በሰፊው ተነፍገውታል ። ወደር የሌለውና እውነተኛ ደስታም ነው ይሄኛው ደስታ ። አማኞች የተለየን ነንና ከሃዲያን እና እንስሶች የማይጋሩንን፣ ልዩ የሆነውን ደስታ እንፈልግ! ! አላህ ይወፍቀን! !


👆🏻🌹👆🏻
🌹تلاوة طيبة للقارئ #رعد_الكردي🌹
﴿طس ۚ تِلْكَ آيَاتُ الْقُرْآنِ وَكِتَابٍ مُّبِينٍ ۝ هُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ ۝﴾ النمل




Репост из: بذرة خير


ከሰውነታችን ላይ ማስወገድ የሚፈቀደውና የሚከለከለው ፀጉር የቱ ነው?
ሰውነት ላይ የሚወጣ ፀጉርን በተመለከተ ዐሊሞች ለ 3 ይከፍሉታል።

① ይወገዱ ዘንድ ሸሪዐዊ ትእዛዝ የመጣባቸው የፀጉር አይነቶች።:– ለምሳሌ
– የብብት ፀጉር፣
– የብልት አካባቢ ፀጉር፣
– የቀድሞ ቀመስ ፀጉር (ማሳጠር)፣
– በሐጅ/ በዑምራ የእራስን ፀጉር መላጨት ወይም ማሳጠር

② መወገዳቸው የተከለከሉ የፀጉር አይነቶች። ለምሳሌ:–
– የቅንድብን ፀጉር ማስወገድ (ከከባባድ ወንጀሎች ነው)፣
– ፂምን መላጨት (በኢጅማዕ የተወገዘ ነው)

③ ክልከላም ይሁን ትእዛዝ ያልመጣባቸው የፀጉር አይነቶች። ለምሳሌ:–
– የክንድ ላይ ፀጉር፣
– የእግር / የጭን ላይ ፀጉር፣
– የደረት ፀጉር፣
– የአፍንጫ ፀጉር፣ ወዘተ
በነዚህ ላይ ዐሊሞች ተወዛግበዋል። ከፊሎቹ ተፈጥሮን ከመቀየር ጋር በማያያዝ ሲከለክሉ፣ ሌሎች ግን ሸሪዐው ዝም ስላለው መሰረቱ ፍቁድነት ነው ብለዋል። ይህም በፍቃድም ይሁን በክለከላ መልክ ሸሪዐው ያልገለፀው ነገር ባለበት የመተውም ይሁን የማስወገድ ምርጫ አለው ማለት ነው። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–
★ "ሐላል ማለት አላህ በመፅሐፉ የፈቀደው ነው።
★ ሐራም ማለት አላህ በመፅሐፉ የከለከለው ነው።
★ ከሱ ዝም ያለው የተተወ (ያልተከለከለ) ነው።" [ሶሒሕ አትቲርሚዚ]
ስለዚህ በማስወገድም ይሁን በመተው ቁርኣንና ሐዲሥ ላይ ያልተገለፁት አይነቶች ከሶስተኛ ምድብ ላይ ያርፋሉ ማለት ነው። እናም ባለበት የመተውም ይሁን የማስወገዱ ምርጫ ለባለቤቱ የተተወ ነው።
ይህንን አቋም በርካታ ዐሊሞች መርጠውታል። ለምሳሌ ያክል የሳዑዲ ዑለማዎች ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ (ለጅነተ አድዳኢማህ) "ለሴት የሰውነቷን ፀጉር ማስወገድ ብይኑ ምንድን ነው?" ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ ብለው መልሰዋል:–
"ከቅንድብና ከእራስ ፀጉር ውጭ ያለውን ማስወገድ ይፈቀድላታል። እነዚህን ግን ልታስወግዳቸው አይፈቀድላትም። …" [ፈታዋ ለጅነት አድዳኢማህ: 5/194]
በተለይ ደግሞ ፀጉሩ ባልተለመደ መልኩ የወጣ ከሆነ ለምሳሌ የሴት ፂም ወይም ቀድሞ ቀመስ ገፅታዋን ስለሚያበላሽ ማስወገድ ትችላለች።

ከተለያዩ ምንጮች የተሰበሰበ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 02/2010)
http://t.me/Menhaj_Salafiya






የኒካሕ መስፈርቶች /ሸርጦች/
1. የተጋቢዎቹን ስም ለይቶ መግለፅ፡- ከአንድ በላይ ልጆች ባሉበት ሁኔታ “ልጄን አጋብቼሃለሁ” ወይም ለልጅህ አጋብቼያለሁ” ቢል በቂ አይሆንም፡፡ ስለዚህ ስም ተጠቅሶ ለምሳሌ “ልጄን ፋጢማን ለዐብደላህ አጋብቼያለሁ” ሊል ነው፡፡
2. የሁለቱ ተጋቢዎች ስምምነት፡- የግዴታ ጋብቻ ተቀባይነት የለውም፡፡ [ቡኻሪ፡ 5136፣ ሙስሊም፡ 1419]
3. ለሴቷ ወልይ መኖር፡፡ ነብዩ ﷺ “ያለ ወልይ ኒካሕ የለም” ብለዋልና፡፡ [ሶሒሕ ኢብን ማጃህ፡ 1537]
4. ኒካሑ ሲታሰር ሁለት ብቁ ምስክሮች መኖራቸው፡፡ [ሶሒሕ ኢብን ሒባን፡ 4075]
5. ተጋቢዎቹን እንዳይጋቡ የሚከለክል ነገር (ቅርብ ዝምድና፣ አማችቻ፣ ጥቢ፣ የእምነት ልዩነት፣ …) አለመኖር፡፡
የኒካሕ ማእዘናት፡-
1. ጋብቻን ከሚከለክሉ ነገሮች ነፃ የሆኑ ተጋቢዎች
2. ከሴቷ ወልይ በኩል “አጋብቻለሁ” ወይም መሰል የይሁንታ ቃል
3. የአግቢው ወይም ወኪሉ “ተቀብያለሁ” ወይም መሰል የመስማማት ቃል

(ከአልፊቅሁል ሙየስሰር ኪታብ የተወሰደ ገፅ፡404-406)
http://t.me/Menhaj_Salafiya






Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሽብር፣ ፍንዳታ፣ ተክፊርና ወደ አመፅ መጣራት ከኢኽዋነል ሙስሊሚን አበይት መገለጫዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው። ሰይድ ቁጥብ፣ አዝዘዋሂሪ፣ ቢን ላደን፣… በዚህ ረገድ የሚጠቀሱ ምሳሌዎች ናቸው።
ሰው የሚዘነጋው ሌላኛው የቡድኑ አብይ መገለጫ ተለዋዋጭነት ነው። ልክ እንደ እስስት ገፅታቸውን መቀያየር። ቡድናዊ ትርፍ እስካስገኘ ድረስ ትላንት ሲያስተጋቡት ከነበረው አቋም 180 ዲግሪ ዞረው በተቃራኒ ለመሰለፍ ምንም ሐያእ አይዛቸውም። አሕባሽን ባለበት ብቻ ሳይሆን በሌለበትም ጭምር ያብጠለጠሉ ሰዎች ዛሬ ከአሕባሽ ጋር ለመደመር አይናቸውን አያሹም። እስካሁን ካሳለፉት አካሄድ ይህን ያላስተዋለ ከፊታችን ያሉ ክስተቶችን በአንክሮ ይከታተል።
ይህ የተለዋዋጭነት ባህሪያቸው ጎልቶ ከሚታይባቸው ቦታዎች አንዱ ከሰለፍያ አንፃር የሚያሳዩት መንታ ገፅታ ነው። ከሰለፍያ ዑለማዎች ጋር ሲገናኙ የሰለፍያ መስመር ተከታዮች እንደሆኑ መስለው ይቀርባሉ። ሺዐንና ሱፍያን ያወግዛሉ። ከሰለፍያ ጠላቶች ዘንድ ወይም ሰለፍያን ከማያውቁ ክፍሎች ዘንድ ሲቀርቡ ደግሞ ሰለፍያን በጠርዘኝነት፣ በተክፊርነት፣ በአሸባሪነት ይከሳሉ። ከአላዋቂዎች ወይም ከከሃዲዎች ዘንድ በሀሰት ለመወደድ። የዘመናችን የሽብርና የተክፊር አስተሳሰብ ከኢኽዋን የወጣ መሆኑን በመደበቅ። ድብብቆሹ ውሎ አድሮ ብዙ እያስከፈላቸው ቢሆንም የቡድኑ ትልቁ ችግር ግን ካለፈው መማር አለመቻል ነው።


⤴️ *[ويــــن رايــــح أنـــــت ؟]*

مقطع مؤثر:
الـشيخ /
*عبد الرزاق بن عبد المحسن البدر*
حفظـه الله تعالـى -




የተለያዩ ኢስላማዊ ዳዓዋዎች እና የትላልቅ መሻይኮች ፈትዋ በማስራጨት ላይ ትኩረት ያደረገ ቻናል #Join እና ሸር ሽር ያርጉት ሌሎች ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ !! Wasapp👇

https://chat.whatsapp.com/APqfHCy23fgH1EhS7dioRr

Telegram👇

https://t.me/Menhaj_Salafiya

Показано 20 последних публикаций.

2 886

подписчиков
Статистика канала