💙 ምኞት
እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመንታ ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ
🌹❀ ክፍል44 ❀🌹
.
.
.
ከደቂቃዎች ቡሀላ ብሩኬ በምኛት ስምና ፎቶ ወደ ከፈተው የፌስ
ቡክ አካውንት መልክት ደረሰ።
ብሩኬ ከፍቶ ሲመለከተው ሚኪ ነው ።
ለመሳቅ ባኮበኮበ ፊቱ የሚኪን መልክት ማንበብ ጀመረ•••
"ምኛትዬ በመጀመሪያ ነብሴ በጭንቀት በተወጠረችበትና
በዋተተችበት ሰአት በመልክትም ቢሆን ካንቺ ያገናኘኝን ፈጣሪዬን
አመሰግነዋለሁ።
አየሽ ምኞቴ ፈጣሪ በአንደበታችን ሳይሆን በልባችን የምንናገረውን
ነው የሚያደምጠው በስሜት የምንተገብረውን ስተት ሳይሆን
የልባችንን ክፋት እና ቅንነት ያስተውላልና ነው ባንቺ ላይ
የፈፀምኩትን በደል በስሜታዊነት እንጂ በትክክለኛው ማንነቴ
ከሀዲ እና ጨካኝ ሆኜ እንዳልበደልኩሽ ተረድተሽ በደሌን ቆጥረሽ
በኔ ላይ እንዳትጨክኚ ልብሽን ያራራልኝ።
በድጋሚ ከላይ የለበስነውን ፣ያከማቸነውን ሀብት አልያም ስምና
ዝናችንን ሳይሆን ልብን የሚመለከተውን ፈጣሪ አመሰግነዋለሁ።
" የኔ ስስት እሄን መስማት እንደሚያሳምምሽ ብረዳም ሁሌም
አፈቅርሻለሁ። በአሁኑ ሰአት በሰራሁት ስራ ተፀፅቼ አንቺን ፍለጋ
ሀገርሽ ድሬ ዳዋ ነው ያለሁት ። ይቅር በይኝ ምኛትዬ ብዘገይም
ምን ያህል እንደማፈቅርሽና ውስጤን ማንበብ የማልችል ስሜት
የሚነዳኝ ችኩል ሰው እንደነበርኩ የተረዳሁት ደብዳቤሽ የደረሰኝ
ቀን ነው።
እንኳን ጎንደር በአለማችን ላይ የትኛውም አህጉር ብትሆኚ አንቺን
መፈለግ አይደክመኝም።
ግን እባክሽ ጎንደር መጥቼ እስካገኝሽ ውስጤ እንዲረጋጋ ስልክሽን
ክፈችው ቀይረሽ ከሆነም ቁጥሩን ላኪልኝ እባክሽ ምኞቴ!"ይላል።
ካካካካ አይ ጓደኛዬ ለካ ፍቅር እንዲህ አዝረክርኮሻል ካካካ በፅናት
መጥተኽብኝ እንጂ የእውነት ታሳዝነኝ ነበር ክክክክ በቅን ልቦና
ከለመንክ ስልኩም ይላክልህ ይሆናል ጠብቃ በቃ ካካካ " እያለ
ሲያላግጥ ስልኩ ጠራ ሲመለከተው ሚኪ ነው " ባንተ ቤት
ትክክለኛዋን ምኛት ፌስቡክ ላይ ያገኘሀት መስሎህ ዜናውን
ልታበስረኝ መሆኑ ነው እስቲ ይሁንልህ"። አለና ስልኩን አነሳው
"ሄሎ ብሩኬ ወንድሜ ፀሎታችሁ ረድቶኛል ምኛትዬ በፌስ ቡክ
አወራችኝ ጎንደር ነው ያለችው ስልኳን እንድትልክልኝ ጠይቂያት
እስክትልክ እየተጠባበኩ ነው ደስ አይልም !አለው ጬክ ብሎ
ልቡ በደስት እየዘለለች።
" ዋው ደስ ይላል እንጂ በጣም ደስ ይላል ግን ሚኪዬ ልቧን
ሰብረኸዋልና አሁን ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆነች ስልኳን ላንተ
ለመላክ ይተናነቃት ይሆናል። እንደኔ ከሆነ ግዜ ባታጠፋ ይሻላል
አሁኑኑ ወደ ድሬ ኤርፖርት ሂድና ትኬት ቁረጥ በዚህ መሀል ስልኳን
ከላከችልህ እሰየው አንተ ግን መፍጠን አለብህ" አለው።
"ልክ ነህ ብሩኬ እንዳልከኝ አደርጋለሁ የት እንዳለች ካወኩኝ
ቡሀላ ልቀመጥ ብልስ መች ያስችለኛል አሁኑኑ ሄጄ ትኬት
ቆርጣለሁ የደረስኩበትን እና ያለሁበትን ሁኔታ እየደወልኩ
አሳውቃሀለሁ። ሲለው ብሩኬ " በጣም ጥሩ አሁኑኑ ሂድ "ብሎት
ስልኩን ዘጋና መሳቅ ጀመረ።
ምኛት ትንቢተ ከሄደች ቡሀላ ከአንድ ሰአት በላይ ፍራሹ ላይ
ተቀምጦ አጠገቡ ካለው ለሱ ከሚታየው ጓደኛው ጋር ሲሳሳቅና
ሲጨቃጨቅ እዛው በረንዳው ላይ እንደተደበቀች ስታደምጠው
በሚያወራው ነገር አንዴ ስታዝን አንዴ ስትገረም አንዳንዴ ደሞ
የሚለው ነገር ከአቅማ በላይ ሆኖ ሊያስቃት ሲሞክር አፋን ይዛ
ላለመሳቅ ስትታገል ቆየች።
በመሀል የመሳይ ድምፅ እየቀነሰ እየቀነሰ መጣና ከነጭራሹ ጠፋ
። ብድግ ብላ እበሩ ጠርዝ ላይ ተለጥፋ ስታዳምጥ አተነፋፈሱ
መሳይ መተኛቱን አሳወቃት። " ሳይተኛ አይቀርም "አለችና በቀስታ
ድምፅ ሳታሰማ እና ብዙም ሳትበረግደው በሩን በመክፈትሹክክ
ብሏ ገባች።
በሷ እና በመሳይ ፍራሽ መሀል ከጥግ እስከ ጥግ የተወጠረውን
መጋረጃ ገለጥ ስታደርገው...
ይቀጥላል....
✎ ክፍል 45 ... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
⚡️ቻናላችንን #ሼር በማድረግ ሌላ ምርጥ ምርጥ ታሪኮችን ይመልከቱ ያንብቡ
┄┄┉┉✽»🌺✿🌺»✽┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨💚: @menta_libochee
እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመንታ ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ
🌹❀ ክፍል44 ❀🌹
.
.
.
ከደቂቃዎች ቡሀላ ብሩኬ በምኛት ስምና ፎቶ ወደ ከፈተው የፌስ
ቡክ አካውንት መልክት ደረሰ።
ብሩኬ ከፍቶ ሲመለከተው ሚኪ ነው ።
ለመሳቅ ባኮበኮበ ፊቱ የሚኪን መልክት ማንበብ ጀመረ•••
"ምኛትዬ በመጀመሪያ ነብሴ በጭንቀት በተወጠረችበትና
በዋተተችበት ሰአት በመልክትም ቢሆን ካንቺ ያገናኘኝን ፈጣሪዬን
አመሰግነዋለሁ።
አየሽ ምኞቴ ፈጣሪ በአንደበታችን ሳይሆን በልባችን የምንናገረውን
ነው የሚያደምጠው በስሜት የምንተገብረውን ስተት ሳይሆን
የልባችንን ክፋት እና ቅንነት ያስተውላልና ነው ባንቺ ላይ
የፈፀምኩትን በደል በስሜታዊነት እንጂ በትክክለኛው ማንነቴ
ከሀዲ እና ጨካኝ ሆኜ እንዳልበደልኩሽ ተረድተሽ በደሌን ቆጥረሽ
በኔ ላይ እንዳትጨክኚ ልብሽን ያራራልኝ።
በድጋሚ ከላይ የለበስነውን ፣ያከማቸነውን ሀብት አልያም ስምና
ዝናችንን ሳይሆን ልብን የሚመለከተውን ፈጣሪ አመሰግነዋለሁ።
" የኔ ስስት እሄን መስማት እንደሚያሳምምሽ ብረዳም ሁሌም
አፈቅርሻለሁ። በአሁኑ ሰአት በሰራሁት ስራ ተፀፅቼ አንቺን ፍለጋ
ሀገርሽ ድሬ ዳዋ ነው ያለሁት ። ይቅር በይኝ ምኛትዬ ብዘገይም
ምን ያህል እንደማፈቅርሽና ውስጤን ማንበብ የማልችል ስሜት
የሚነዳኝ ችኩል ሰው እንደነበርኩ የተረዳሁት ደብዳቤሽ የደረሰኝ
ቀን ነው።
እንኳን ጎንደር በአለማችን ላይ የትኛውም አህጉር ብትሆኚ አንቺን
መፈለግ አይደክመኝም።
ግን እባክሽ ጎንደር መጥቼ እስካገኝሽ ውስጤ እንዲረጋጋ ስልክሽን
ክፈችው ቀይረሽ ከሆነም ቁጥሩን ላኪልኝ እባክሽ ምኞቴ!"ይላል።
ካካካካ አይ ጓደኛዬ ለካ ፍቅር እንዲህ አዝረክርኮሻል ካካካ በፅናት
መጥተኽብኝ እንጂ የእውነት ታሳዝነኝ ነበር ክክክክ በቅን ልቦና
ከለመንክ ስልኩም ይላክልህ ይሆናል ጠብቃ በቃ ካካካ " እያለ
ሲያላግጥ ስልኩ ጠራ ሲመለከተው ሚኪ ነው " ባንተ ቤት
ትክክለኛዋን ምኛት ፌስቡክ ላይ ያገኘሀት መስሎህ ዜናውን
ልታበስረኝ መሆኑ ነው እስቲ ይሁንልህ"። አለና ስልኩን አነሳው
"ሄሎ ብሩኬ ወንድሜ ፀሎታችሁ ረድቶኛል ምኛትዬ በፌስ ቡክ
አወራችኝ ጎንደር ነው ያለችው ስልኳን እንድትልክልኝ ጠይቂያት
እስክትልክ እየተጠባበኩ ነው ደስ አይልም !አለው ጬክ ብሎ
ልቡ በደስት እየዘለለች።
" ዋው ደስ ይላል እንጂ በጣም ደስ ይላል ግን ሚኪዬ ልቧን
ሰብረኸዋልና አሁን ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆነች ስልኳን ላንተ
ለመላክ ይተናነቃት ይሆናል። እንደኔ ከሆነ ግዜ ባታጠፋ ይሻላል
አሁኑኑ ወደ ድሬ ኤርፖርት ሂድና ትኬት ቁረጥ በዚህ መሀል ስልኳን
ከላከችልህ እሰየው አንተ ግን መፍጠን አለብህ" አለው።
"ልክ ነህ ብሩኬ እንዳልከኝ አደርጋለሁ የት እንዳለች ካወኩኝ
ቡሀላ ልቀመጥ ብልስ መች ያስችለኛል አሁኑኑ ሄጄ ትኬት
ቆርጣለሁ የደረስኩበትን እና ያለሁበትን ሁኔታ እየደወልኩ
አሳውቃሀለሁ። ሲለው ብሩኬ " በጣም ጥሩ አሁኑኑ ሂድ "ብሎት
ስልኩን ዘጋና መሳቅ ጀመረ።
ምኛት ትንቢተ ከሄደች ቡሀላ ከአንድ ሰአት በላይ ፍራሹ ላይ
ተቀምጦ አጠገቡ ካለው ለሱ ከሚታየው ጓደኛው ጋር ሲሳሳቅና
ሲጨቃጨቅ እዛው በረንዳው ላይ እንደተደበቀች ስታደምጠው
በሚያወራው ነገር አንዴ ስታዝን አንዴ ስትገረም አንዳንዴ ደሞ
የሚለው ነገር ከአቅማ በላይ ሆኖ ሊያስቃት ሲሞክር አፋን ይዛ
ላለመሳቅ ስትታገል ቆየች።
በመሀል የመሳይ ድምፅ እየቀነሰ እየቀነሰ መጣና ከነጭራሹ ጠፋ
። ብድግ ብላ እበሩ ጠርዝ ላይ ተለጥፋ ስታዳምጥ አተነፋፈሱ
መሳይ መተኛቱን አሳወቃት። " ሳይተኛ አይቀርም "አለችና በቀስታ
ድምፅ ሳታሰማ እና ብዙም ሳትበረግደው በሩን በመክፈትሹክክ
ብሏ ገባች።
በሷ እና በመሳይ ፍራሽ መሀል ከጥግ እስከ ጥግ የተወጠረውን
መጋረጃ ገለጥ ስታደርገው...
ይቀጥላል....
✎ ክፍል 45 ... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
⚡️ቻናላችንን #ሼር በማድረግ ሌላ ምርጥ ምርጥ ታሪኮችን ይመልከቱ ያንብቡ
┄┄┉┉✽»🌺✿🌺»✽┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨💚: @menta_libochee