💙 ምኞት
እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመንታ ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ
🌺 ክፍል45 🌺
.
.
እንዳሰበችው መሳይ አንዲት ጉርድ ፎቶ በእጁ ይዞ ደረቱ ላይ
ልጥፍ እንዳረጋት እንቅልፍ ጥሎታል።
ቀስ ብላ ፍራሹን ከተሻገረች ቡሀላ ወደ መደበቂያ እቃ ቤቷ
ከመግባቷ በፊት መሳይ ይዞ የተኛው ፎቶ የኖርዶስ ሊሆን
እንደሚችል ስለገመተች ማየት ፈለገች ደሞ እንዳይነቃ ፈራች።
ድምፅ ላለማሰማት እየተጠነቀቀች በቀስታ ፍራሹ ላይ በርከክ
አለችና ከእጁ ላይ የፎቶዋን ጫፍ ይዛ ጎተት ስታደርጋት ለቀቀላት
ወድያው ገልብጣ ስትመለከተው እንደጠረጠረችው የኖርዶስ ፎቶ
ነበር " እውነትም ቆንጆ ነሽ ናርዶስ ግን ከኔ አትበልጭም አደል?
አለች ፎቶው ላይ እንዳፈጠጠች ፈገግ ብላ ዘወር ስትል ከፍራሹ
አጠገብ የመሳይ የኪስ ዋሌት መሬት ወድቋል።
ተጨማሪ ፎቶ ሊኖር እንደሚችል ስለገመተች አንስታ በመክፈት
ስትመለከት ኖርዶስ በዋሌት መጠን እና በጉርድ የተነሳቻቸው
ዘጠኝ ፎቶዋች አገኘች አንዱን ገልበጥ ስታደርገው "የኔ ናርዴስ
መጣሽም ቀረሽም እስከምሞት አፈቅርሻለሁ ያንቺው እብድ አፍቃሪ
መሳይ ይላል።
ሌሎቹንም በየተራ እየገለበጠች ጀርባቸውን ስትመለከት አንድ
ሌላ ፌቶ ላይ የተፃፈው•••
ላንቺ ተፈጥሪያለሁ በምድር ሂወቴ አንቺን አፈቅሪያለሁ ባንቺ
እራሴን ጠልቻለሁ ባንቺ አብጃለሁ በልቤ እንደያዝኩሽ ወደ
መቃብር እወርዳለሁ ይላል ። ሚኪ ትዝ አላት እምባዋ ከሁለት
አይኖቿ ቁልቁል መውረድ ጀመረ።
ሚኪ ጎንደር ደርሶ "መጥቻለሁ ምኛትዬ ያለሽበትን ንገሪኝ እና
ልምጣ እባክሽ የኔ ስስት ብሎ መልክት ላከ ።
ብሩኬ የሚኪን መልክት ቢመለከቱውም መልስ አልሰጠውም ዝም
አለው ሚኪ መልክት ደጋግሞ ቢልክም መልስ ስላላገኘ
በጭንቀትና በብስጭት ለሰአታት ከቆየ ቡሀላ " እባክሽ ስስቴ
ልታገኝኝ ካልፈለግሽ ወደ መጣሁበት ልመለስ ቁርጡን ንገሪኝ"
ብሎ ሲፅፍ ተመልሶ ወደ አዲስ አበባ ሊመጣ ነው ብሎ
የደነገጠው ብሩክ አሰብ አደረገና መልክቱ በደረሰው በምኛት ስም
በከፈተው የፌስ ቡክ አካውንት "ሚኪ እንደዛ ገፍትረህ የጣልከኝን
ሴት እኔን ፍለጋ ጎንደር መምጣትህን በምን ልመን? ብሎ ላከለት።
እሱ ከሆነ ችግሩ የኔ ስስት ኦን ላይን ሆነሽ ትንሽ ጠብቂኝ ብሎ
ወድያው በአከባቢው ወደ ነበረው ፋሲለደስ በማቅናት አከባቢውን
በደንብ በሚያሳይ ሁኔታ እራሱን አስገብቶ እየቀረፀ ቀጥታ ቪድዬ
እንድትመለከትና እንድታምነው ለማድረግ ሞከረ ።
ብሩክ ቪድዬውን እየተመለከተ እስኪበቃው ከሳቀ ቡሀላ •••
" በል ፈተናውን አልፈኻል እኔ ያለሁት ጎንደር ሳይሆን መቀሌ ነው።
የእውነት እየፈለከኝ እንደሆነ ማወቅ ነበረብኝ። የእውነት
እምትፈልገኝ እምታፈቅረኝ ከሆነ መቀሌ ና" ብሎ ላከለት ሚኪ
መቀሌ የደረሰው ምንም እንቅልፍ የሚባል ነገር ባይኑ ሳይዞር
ነበር ። ከመቀሌ የመጨረሻ ፈተናውን አልፈሀል አዳማ ና የእውነት
ከአዳማ ተያይዘን ነው ወደ አዲስ አበባ የምንሄደው በሚል ሰበብ
ወደ አዳማ እንዲመጣ ካደረገው ቡሀላ አዳማ መጥቼለሁ ምኛቴ
ብሎ ሲልክ •••
በዛው የምኛት ፌስ ቡክ አካውን ባክህ ነቀምቴ ነኝ ብሎ ሲልክለት
እንደእብድ አደረገው እጅጉን የመታከት እና ተስፋ የመቁረጥ
ስሜት ውስጥ ገባ ብቻውን እያወራ በእግሩ ብዙ ተጓዘ ።
እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ ምኛት በጤናዋ እያረገችው ነው ብሎ
መቀበል አልቻለም።
ድንገት አእምሮው ውስጥ የተፈጠረው ነገር ብቻውን በየመንገዱ
ያስለፈልፈው ጀመር ። ከፀቦች ሁሉ ክፉ ወደሆነው ፀብ ውስጥ
ከተተው።
ከራሱ ጋር ፀብ ፈጠረ ሚኪ አንድ ሰው ሆኖ እያለ በምኛት ጉዳይ
ላይ ሁለት ቦታ ተከፍሎ ሙግት ገጠመ •••
"ይቺ ልጅ እማ እሄን ሁሉ ነገር የምታረገው በጤናዋ አይደለም
አብዳለች አልያም እብደት ጀማምሯታል" የሚል አስቀያሚ ሀሳብ
ድንገት ሹክ ሲልበት ሳያስበው ጆሮው ላይ ጥይት የተተኮሰበት
ያክል ነበር መሀል መንገድ ላይ እርምጃውን በመግታት ደርቆ
የቀረው።
"ኧረ በፍፁም እሄ የኔ ሀሳብ የወለደው እንጂ እሷ ጤነኛ ነች
በማለት ለራሱ ሀሳብ እራሱ ምላሽ ሰጠ"
" እስቲ አስበው ተመልሳ የምትገባበት ቤት የለላትን ልጁ
በወላጆቿ ሞት በሀዘን የቆሰለው አእምሬዋ ሳያገግም አምጥተህ
እዛ ኦና ኬንደሚንየም ውስጥ ስትወረውራት ባታብድ ነበር
ሚገርመው አንተ ከሀዲ ነህ ተቀበል! ያለው መሰለው ከዚህ
ውስጡ ተፈጥሮ ጎራ ለይቶ ከሚፋጨው ሀሳብ ወዴት ሮጦ
እንደሚያመልጠው ግራ ገባው ።
ሰው ሲሞግተን፣ ፣ የሚረብሸንን ሀሳብ እያነሳ ሲያስጨንቀን ፣
እንዲህ ሆኖ ቢሆንስ እያለ በስጋት ሲንጠን ሰውየውን እንሸሸው
ከሱ ጋር ማውራት እናቆም አልያም እሱ በተገኘበት ቦታ አንገኝ
ይሆናል ።
ልባችን ህሊናችንና አእምሮአችን በሀሳብ ተከፋፍለው መስማማት
ሲሳናቸው በውስጣችን ለሰው የማይሰማ ጦርነትና ጩኸት
ሲፈጠር ምን መሸሻ አለን ሰው ከራሱ ወዴት ይሸሻል?ሰው ከራሱ
ወዴት ሮጦ ያመልጣል ? ሚኪም መሸሸጊያ ያሳጣው የሀሳብ
ማእበል ሲንጠው ከመናጥ ውጪ ማምለጫ አልነበረውም ።
ሞባይሉን አወጣና ፌስቡክ ከፍቶ መልክት መፃፍ ጀመረ መልክቱን
ቀለል አድርጎ ለመጀመር አሰበ••
"ምኞቴ እየተበቀልሽኝ ባልሆነ ከበደሌ አንፃር ምንም ቢደርስብኝ
ምንም ብሆን ቅጣቴን ለመቀበል ዝግጁ ብሆንም ይቅርታ
የማያጥበው የበደል እድፍ የለምና ይቅርታ ከጠየኩሽ ቡሀላ እሄን
ያክል በኔ ላይ የጨከነ ልብ ኬት አገኘሽ ምኛትዬ ?
አሁንስ ፈራሁ የምትይኝ እና እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ ሌላ ነገር
እንዳስብ አደረገኝና ፈራሁ ምኛትዬ።
እኔ ምንም ልሁን እሄን ሁሉ ነገር የምታደርጊው በንፁህ እና
በጠኔኛ አእምሮሽ ከሆነ ይሁን ግድ የለም የኔ ድካም ተኝቼ ስነሳ
ይጠፋል ፈጣሪዬን አደራ እምለው በኔ ምክንያት ተኝተሽ ስትነሺ
የማይጠፋ የማይተው የአእምሮ በሽታ ጥዬብሽ እንዳይሆን ፈራሁ
አምጥቼ ስጥልሽ በደሌን መቋቋም አቅቶሽ ተሸንፈሽ እንዳይሆን
ሰጋሁ ምኛትዬ ። ሁሉም ቀርቶብኝ ጤነኛ መሆንሽን ብቻ
አረጋግጭልኝ ስስቴ ቀውስሻል እያልኩሽ አይደለም ነብሴ ሰላምና
እረፍት እንድታገኝ ደና መሆንሽን ብቻ ንገሪኝ ምንም አልሆንኩም
ሰላም ነኝ ግን ላገኝህ አልፈልግም ብቻ በይኝ የኔ ፍቅር
እባክሽ!"ብሎ መልክት ላከ....
ይቀጥላል........
✎ ክፍል 46 ... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
⚡️ቻናላችንን #ሼር በማድረግ ሌላ ምርጥ ምርጥ ታሪኮችን ይመልከቱ ያንብቡ
┄┄┉┉✽»🌺✿🌺»✽┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨💚: @menta_libochee
እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመንታ ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ
🌺 ክፍል45 🌺
.
.
እንዳሰበችው መሳይ አንዲት ጉርድ ፎቶ በእጁ ይዞ ደረቱ ላይ
ልጥፍ እንዳረጋት እንቅልፍ ጥሎታል።
ቀስ ብላ ፍራሹን ከተሻገረች ቡሀላ ወደ መደበቂያ እቃ ቤቷ
ከመግባቷ በፊት መሳይ ይዞ የተኛው ፎቶ የኖርዶስ ሊሆን
እንደሚችል ስለገመተች ማየት ፈለገች ደሞ እንዳይነቃ ፈራች።
ድምፅ ላለማሰማት እየተጠነቀቀች በቀስታ ፍራሹ ላይ በርከክ
አለችና ከእጁ ላይ የፎቶዋን ጫፍ ይዛ ጎተት ስታደርጋት ለቀቀላት
ወድያው ገልብጣ ስትመለከተው እንደጠረጠረችው የኖርዶስ ፎቶ
ነበር " እውነትም ቆንጆ ነሽ ናርዶስ ግን ከኔ አትበልጭም አደል?
አለች ፎቶው ላይ እንዳፈጠጠች ፈገግ ብላ ዘወር ስትል ከፍራሹ
አጠገብ የመሳይ የኪስ ዋሌት መሬት ወድቋል።
ተጨማሪ ፎቶ ሊኖር እንደሚችል ስለገመተች አንስታ በመክፈት
ስትመለከት ኖርዶስ በዋሌት መጠን እና በጉርድ የተነሳቻቸው
ዘጠኝ ፎቶዋች አገኘች አንዱን ገልበጥ ስታደርገው "የኔ ናርዴስ
መጣሽም ቀረሽም እስከምሞት አፈቅርሻለሁ ያንቺው እብድ አፍቃሪ
መሳይ ይላል።
ሌሎቹንም በየተራ እየገለበጠች ጀርባቸውን ስትመለከት አንድ
ሌላ ፌቶ ላይ የተፃፈው•••
ላንቺ ተፈጥሪያለሁ በምድር ሂወቴ አንቺን አፈቅሪያለሁ ባንቺ
እራሴን ጠልቻለሁ ባንቺ አብጃለሁ በልቤ እንደያዝኩሽ ወደ
መቃብር እወርዳለሁ ይላል ። ሚኪ ትዝ አላት እምባዋ ከሁለት
አይኖቿ ቁልቁል መውረድ ጀመረ።
ሚኪ ጎንደር ደርሶ "መጥቻለሁ ምኛትዬ ያለሽበትን ንገሪኝ እና
ልምጣ እባክሽ የኔ ስስት ብሎ መልክት ላከ ።
ብሩኬ የሚኪን መልክት ቢመለከቱውም መልስ አልሰጠውም ዝም
አለው ሚኪ መልክት ደጋግሞ ቢልክም መልስ ስላላገኘ
በጭንቀትና በብስጭት ለሰአታት ከቆየ ቡሀላ " እባክሽ ስስቴ
ልታገኝኝ ካልፈለግሽ ወደ መጣሁበት ልመለስ ቁርጡን ንገሪኝ"
ብሎ ሲፅፍ ተመልሶ ወደ አዲስ አበባ ሊመጣ ነው ብሎ
የደነገጠው ብሩክ አሰብ አደረገና መልክቱ በደረሰው በምኛት ስም
በከፈተው የፌስ ቡክ አካውንት "ሚኪ እንደዛ ገፍትረህ የጣልከኝን
ሴት እኔን ፍለጋ ጎንደር መምጣትህን በምን ልመን? ብሎ ላከለት።
እሱ ከሆነ ችግሩ የኔ ስስት ኦን ላይን ሆነሽ ትንሽ ጠብቂኝ ብሎ
ወድያው በአከባቢው ወደ ነበረው ፋሲለደስ በማቅናት አከባቢውን
በደንብ በሚያሳይ ሁኔታ እራሱን አስገብቶ እየቀረፀ ቀጥታ ቪድዬ
እንድትመለከትና እንድታምነው ለማድረግ ሞከረ ።
ብሩክ ቪድዬውን እየተመለከተ እስኪበቃው ከሳቀ ቡሀላ •••
" በል ፈተናውን አልፈኻል እኔ ያለሁት ጎንደር ሳይሆን መቀሌ ነው።
የእውነት እየፈለከኝ እንደሆነ ማወቅ ነበረብኝ። የእውነት
እምትፈልገኝ እምታፈቅረኝ ከሆነ መቀሌ ና" ብሎ ላከለት ሚኪ
መቀሌ የደረሰው ምንም እንቅልፍ የሚባል ነገር ባይኑ ሳይዞር
ነበር ። ከመቀሌ የመጨረሻ ፈተናውን አልፈሀል አዳማ ና የእውነት
ከአዳማ ተያይዘን ነው ወደ አዲስ አበባ የምንሄደው በሚል ሰበብ
ወደ አዳማ እንዲመጣ ካደረገው ቡሀላ አዳማ መጥቼለሁ ምኛቴ
ብሎ ሲልክ •••
በዛው የምኛት ፌስ ቡክ አካውን ባክህ ነቀምቴ ነኝ ብሎ ሲልክለት
እንደእብድ አደረገው እጅጉን የመታከት እና ተስፋ የመቁረጥ
ስሜት ውስጥ ገባ ብቻውን እያወራ በእግሩ ብዙ ተጓዘ ።
እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ ምኛት በጤናዋ እያረገችው ነው ብሎ
መቀበል አልቻለም።
ድንገት አእምሮው ውስጥ የተፈጠረው ነገር ብቻውን በየመንገዱ
ያስለፈልፈው ጀመር ። ከፀቦች ሁሉ ክፉ ወደሆነው ፀብ ውስጥ
ከተተው።
ከራሱ ጋር ፀብ ፈጠረ ሚኪ አንድ ሰው ሆኖ እያለ በምኛት ጉዳይ
ላይ ሁለት ቦታ ተከፍሎ ሙግት ገጠመ •••
"ይቺ ልጅ እማ እሄን ሁሉ ነገር የምታረገው በጤናዋ አይደለም
አብዳለች አልያም እብደት ጀማምሯታል" የሚል አስቀያሚ ሀሳብ
ድንገት ሹክ ሲልበት ሳያስበው ጆሮው ላይ ጥይት የተተኮሰበት
ያክል ነበር መሀል መንገድ ላይ እርምጃውን በመግታት ደርቆ
የቀረው።
"ኧረ በፍፁም እሄ የኔ ሀሳብ የወለደው እንጂ እሷ ጤነኛ ነች
በማለት ለራሱ ሀሳብ እራሱ ምላሽ ሰጠ"
" እስቲ አስበው ተመልሳ የምትገባበት ቤት የለላትን ልጁ
በወላጆቿ ሞት በሀዘን የቆሰለው አእምሬዋ ሳያገግም አምጥተህ
እዛ ኦና ኬንደሚንየም ውስጥ ስትወረውራት ባታብድ ነበር
ሚገርመው አንተ ከሀዲ ነህ ተቀበል! ያለው መሰለው ከዚህ
ውስጡ ተፈጥሮ ጎራ ለይቶ ከሚፋጨው ሀሳብ ወዴት ሮጦ
እንደሚያመልጠው ግራ ገባው ።
ሰው ሲሞግተን፣ ፣ የሚረብሸንን ሀሳብ እያነሳ ሲያስጨንቀን ፣
እንዲህ ሆኖ ቢሆንስ እያለ በስጋት ሲንጠን ሰውየውን እንሸሸው
ከሱ ጋር ማውራት እናቆም አልያም እሱ በተገኘበት ቦታ አንገኝ
ይሆናል ።
ልባችን ህሊናችንና አእምሮአችን በሀሳብ ተከፋፍለው መስማማት
ሲሳናቸው በውስጣችን ለሰው የማይሰማ ጦርነትና ጩኸት
ሲፈጠር ምን መሸሻ አለን ሰው ከራሱ ወዴት ይሸሻል?ሰው ከራሱ
ወዴት ሮጦ ያመልጣል ? ሚኪም መሸሸጊያ ያሳጣው የሀሳብ
ማእበል ሲንጠው ከመናጥ ውጪ ማምለጫ አልነበረውም ።
ሞባይሉን አወጣና ፌስቡክ ከፍቶ መልክት መፃፍ ጀመረ መልክቱን
ቀለል አድርጎ ለመጀመር አሰበ••
"ምኞቴ እየተበቀልሽኝ ባልሆነ ከበደሌ አንፃር ምንም ቢደርስብኝ
ምንም ብሆን ቅጣቴን ለመቀበል ዝግጁ ብሆንም ይቅርታ
የማያጥበው የበደል እድፍ የለምና ይቅርታ ከጠየኩሽ ቡሀላ እሄን
ያክል በኔ ላይ የጨከነ ልብ ኬት አገኘሽ ምኛትዬ ?
አሁንስ ፈራሁ የምትይኝ እና እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ ሌላ ነገር
እንዳስብ አደረገኝና ፈራሁ ምኛትዬ።
እኔ ምንም ልሁን እሄን ሁሉ ነገር የምታደርጊው በንፁህ እና
በጠኔኛ አእምሮሽ ከሆነ ይሁን ግድ የለም የኔ ድካም ተኝቼ ስነሳ
ይጠፋል ፈጣሪዬን አደራ እምለው በኔ ምክንያት ተኝተሽ ስትነሺ
የማይጠፋ የማይተው የአእምሮ በሽታ ጥዬብሽ እንዳይሆን ፈራሁ
አምጥቼ ስጥልሽ በደሌን መቋቋም አቅቶሽ ተሸንፈሽ እንዳይሆን
ሰጋሁ ምኛትዬ ። ሁሉም ቀርቶብኝ ጤነኛ መሆንሽን ብቻ
አረጋግጭልኝ ስስቴ ቀውስሻል እያልኩሽ አይደለም ነብሴ ሰላምና
እረፍት እንድታገኝ ደና መሆንሽን ብቻ ንገሪኝ ምንም አልሆንኩም
ሰላም ነኝ ግን ላገኝህ አልፈልግም ብቻ በይኝ የኔ ፍቅር
እባክሽ!"ብሎ መልክት ላከ....
ይቀጥላል........
✎ ክፍል 46 ... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
⚡️ቻናላችንን #ሼር በማድረግ ሌላ ምርጥ ምርጥ ታሪኮችን ይመልከቱ ያንብቡ
┄┄┉┉✽»🌺✿🌺»✽┉┉┄┄
𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨💚: @menta_libochee