አንድነት
~~~~~~
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኁሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ፡፡
============================
َበአላህ የእምነት ገመድ ተያያዙ አትለያዩም﴿ (አል ኢምራን 103)
የአንድነት መሰረቶቹም ቢሆኑ ፍጹም ግልጽና የማያሻሙ አንኳር ነጥቦች ናቸው::
አላህን በብቸኝነት ማምለክ እንዲሁም በእርሱ ላይም ማንንም አለማጋራት አለቀ ደቀቀ::
ይህንን ነጥብ ስታብራራው ግን ብዙ ይበልጥ አንድነትን የሚያጠናክሩ ጉዳዮችን ትዳስሳለህ::
ስለዚህ አወጣህም አወረድክም በዚህ ምሰሶ ዙሪያ የጠብታ ልኬት ክፍተት ከተፈጠረ በ'ይፈርሳል' ስጋት በየዋህነት ከተዳፈነ አንድ በእርግጠኝነት መናገር የምችለው ነገር አለኝ:: እርሱም ዛሬ ይህንን መሰረት አስመልክቶ ስንዝር የተለያየንባቸው ነጥቦች ነገ አጋጣሚውን ሲያገኙ የምስራቅና የምዕራብን ክፍተት ያህል እንደሚያራርቁን ተረዳ::
በመሆኑም የአንድነታችንን መዘውር የሳቱ እሳቤዎች ጋር በፍጹም አንድ አንሆንም (ፍላጎት ሳይሆን እጣ ፈንታችን ነውና) ባይሆን እንደ ወጉ እንደ ልማዱ ነጥቦችን እየፈተሽን እንወያይባቸዋለን እየሞረድን እየቀረጽን ክፍተቶችን እናጠባለን ብሎም እናጠፋለን::
በተፈተሹና በተሞረዱ ቁጥር ዳር እና ዳር የሚመስሉ ግንዛቤዎቻችን ይበልጥ አንድነትን እያጎሉ ይመጣሉ::
ስለዚህ አንድ አይነት አመለካከት እንድናዳብር በተጠየቅንበት አጀንዳዎች ላይ 'ኸረ እንዳንበታተን ብለህ አትበል ምክንያቱም ይሔንን የጥሜት ፊረቆች አካሄድ ነዉ በዋነኛነት የኢኽዋኖች ::
ይልቁንም ሀሳብህን አቅርብ እምነትህን አሳይ ምናልባትም ከመዘውሩ የሸሸኸው አንተ ብቻ
ልትሆን ትችላለህና ::
በግርድፉ እንዲህ ልበል በተውሂድ ላይ መወያየታችን መሰረታዊ ስህተቶችን መጠቆማችን እንዲሁም ሽርክና ዘመዶቹን በስፋት መዳሰሳችን ፍጹም አንድነት የሚያጎናጽፉን ነጥቦች ናቸውና አትስጋ ኢኽዋኖች እንደ ሚሉት አንድነት የሚንድ አይደለም ይሔ እዉነታኛ አንድነት የሚያጎናጽፉ ነዉ ::
ዳሩ ከዚህ ውጪ የተመሰረተ አንድነት ለባለቤቱ እያደር ብቸኝነትን እንጂ አያወርሰውም ስለዚህ አሏህ በተዉሂድ በሱና አንድ ሆኑ አለን እንጂ ከአሏህ ዉጭ የሚገዛ ከእሱ አንድ አንድ ሆኑ ብሎ አላዘዘንም ነቃ የአሏህ ባረያ ትክክለኛ አንድነት በተዉሂድ ብቻ ነዉ ::
~~~~
እውነትን ከልብ በመሻት ለማስረጂያ እጅ በመስጠት እንዲሁም ስሜታዊነትን በማስወገድ የሚደረግ ውይይት ፍቱን መድሀኒት ነው ህይወት ከቆመው ህዝብ ጋር ብቻ ሳይሆን በጀነት ከታጩ ሙታኖች ጋርም በማይበጠስ የአንድነት ገመድ
ያስተሳስረናልና
አሏህ እዉነተኛ አንድነት ይሰጠን በተዉሂድ በሱና አንድ ያርገን ከጠሞ አጥማሚዎች አሏህ ይጠብቀን እነሱም አሏህ ይምራቸዉ ፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
"""""""""""""""""""""""
July / 8 / 2019
ሀምሌ / 1 / 2011
✍ከወንድም meqsud muhammed
#አሰላሙ_ዐለይኩም
t.me/meqsud_ibn_muhammed