الجَنَّةُ غَالِيَةٌ
ጀነ፞ት ውድ፞ ናት!!
ከሰላሳ አመታት በፊት የመሬት ዋጋ እጅግ በጣም ርካሽ ስለ ነበር እድሜያቸውን የገፉ አዛውንቶች ያኔ እድሉ ተመቻችቶላቸው ሳይጠ፞ቀ፞ሙበት በማለፉ ምክንያት ዛሬ ላይ በፀፀት መንፈስ: "እኔኮ ያኔ በርካታ መሬቶችን መያዝ እየቻልኩና መግዣ ገንዘብም ሳላጣ እንዲሁ በከንቱ እድሉን አሳልፌያለሁ!!" በማለት ብዙ ጊዜ ሲያወሩ ይታ፞ያ፞ሉ።
ምክንያቱም ዛሬ ላይ ትንሽ ስፋት ያላት የመሬት ክልል በመቶሺዎች ወይም በሚሊዮኖች እንጂ የማትገኝ በመሆኗ ነው!!
ያንኔ ርካሽ እያ፞ለ፞ እድሉን ተጠቅመው በርካታ መሬት የሰበሰቡ ሰዎችን እንኒሁ አዛውንቶች ሲያደንቁዋቸውና ሲያወድሷቸውም ይሰ፞ማ፞ሉ።
በመሬት ሰበብ ሚሊዬነር ሆነው ሲያዩዋቸውም የነሱን ቦታ ይመኛሉ!!
•አሳሳ፞ቢ የሆነው ጉዳይ: "ይህ አይነቱ ክስተት ወደፊት ይደ፞ጋገም ይሆን!?" የሚለው ነው!!
መልሱም፦ አዎ! ያውም እጅግ በጣም አስፀፃች በሆነ መልኩ ነዋ!!
እሱም፦ መልካም ስራዎችን ለምሳሌ ያህል ፦ ተውሒይድ፣ ሶላት፣ ሶደቃ፣ ዚክር፣ ሌሎች ችግረኞችን መርዳትና የመሳሰሉ መልካም ስራዎችን፤ ሰዎች ዱንያ ላይ እያ፞ሉ፞ በቀላሉ ለመስራት ምቾቱም፣ አቅሙም፣ ብቃቱም እያ፞ላ፞ቸው፤ እነዚህን ስራዎች ንቀውና አሳንሰው በማየት ሳይሰ፞ነ፞ቁባ፞ቸው ነገ የቂያማ እለት ይመጣሉ።
እዚህ ይንቁት የነበረው ስራ እዚያ ምን ያህል አጅርና ዋጋ እንዳለው ሲገለፅላቸው ደግሞ ጥግ የደረሰ ፀፀት ይሰማቸዋል!!
በሁለቱ አስፀፃች ሁነቶች መካከል ያለው ልዩነት ሲብራራ ይህን ይመስላል፦
•ዛሬ ጊዜ የመሬት ዋጋ ቢንርም ማግኛ መንገዱ ግን ሊሆን የማይችል ነገር አይደለም!! (ሊገኝ ይችላል)።
•ይህኛው ሁኔታ ግን ከዚህ በጣም የተለየ ነው። ምክንያቱም፦ የመልካም ስራ ዋጋ በቂያማ እለት ግልፅ ሆኖ ለሰዎች ቢታ፞ይ፞ም ማግኛ መንገዱ ግን ሊሆን የማይችልና የተዘጋ ነገር ነው!!
•የመጀመሪያው ሰውዬ: «ዋ እኔ! መሬት ርካሽ እያለ ምነው ገዝቼ በነበር» በማለት ሲመኝ፤
•የቂያማው ሰው ደግሞ:
(يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي)
(«ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ» ፡፡) ይላል!!
ስለዚህ ወንድሜ! ዛሬ መልካም ስራዎችን ለመስራት ምቾቱና ብቃቱ ኖሮህ፤ ስራዎቹም ቀላል ሆነውልህ ስታያቸው እንዳትሸወ፞ድ!!
የነገ የኣኺራ ዋጋቸውንም ርካሽ አድርገህ እንዳታስብ!!
ይልቁንም ዋጋቸውና ምንዳቸው ከባድ ነው፤ ይህን የሚያውቁት የዱንያን ጠፊነት እርግጥ ብለው፤ ለነገው ዘላለማዊ ህይወታቸው በጥሩ "ኒይያ" የሚለፉት ናቸው።
جعلنا الله وإياكم مِن عباده الصالحين و مِن رِجالِ أعمالِ الآخرة.
አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ከመልካም ባሮቹና ለዱንያ ሳይሆን ለኣኺራ ከሚነግዱት ቱጃ፞ሮች ያድርገን።
(ከዐረብኛ ፅሁፍ የተወሰደ)
✍️አቡ ዐብዲላህ አስ ـ ሰለፊይ
غَفَرَ اللهُ لَه ولِوالدَيهِ ولِجميعِ أُسْرَتِه.https://
t.me/mesjidalteqwawenabo