#መመኪያዮ አንተ ነህ
መመኪያዬ አንተ ነህ የነፍሴ መዳኛ
ተመለከት ወደእኔ አትስጠኝ ለዳኛ
ሕይወቴን ለአንተ /2/ ብያለው
አምላክ የእኔ ጌታ የት አገኝሀለሁ፡፡
ከበደሌም አንጻኝ ደግሞሞ ከኃጢአት
በመንፈስ ይታደስ መላ ሰውነቴ
ሕይወቴን ላንተ ---------
አቀበቱ ልቤ በጭንጫ ላይ ትእቢት
አሸብርቆ ነበር አልፈርስም መስሎት
ሕይወቴ ለአንተ -------------
የጾም ንጉሥ መምጣት ሰለተነገረ
መደልደል አለበት እየተሰበረ
ሕይወቴን ለአንተ ----------------
ሶስናን ያደንካት ከሐሰት ምስክር
እኔንም አድነኝ ካልታሰበ ነገር
ሕይወቴን ለአንተ --------------
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
★
@mezmurtenat ★