📚 ኒቆዲሞስ - የዐብይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት።
✒ ''እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። (ዮሐ 3:3-6)
ጌታችን ወደዚህ ምድር መጥቶ የምስራቹን ቃል ሲያውጅ እስራኤላውያን የተቀበሉት በተደበላለቀ ስሜት ነበር። በአንድ በኩል ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ሲገዛ ስለነበር ከሮማውያን ቅኝ ግዛት ነጻ የሚያወጣቸው መሲህ ይፈልጋሉ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ቀንበር ስለደከመ ተስፋ በመቁረጥ ተዳክሞ ነበር፡፡ መሲህ ቢመጣ እንኳ ይመጣል ብለው የሚጠብቁት ጦር ይዞ ሰራዊት አስከትሎ ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ስለዚህም ነው ክርስቶስን መሲህ ነኝ ብሎ ሲመጣ ለመቀበል ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡
ምክንያቱ ደግሞ ጦር ሳይዝ ሰራዊት ሳያስከትል እንዲሁ ባዶ እጁን አርነት ላወጣችሁ መጥቻለሁ እያለ ደጋግሞ ተናግሯልና ነው፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛው እስራኤላዊ የክርስቶስን መሲህነት ቢጠራጠርና ባይቀበለውም፣ በፍጹም እምነት እስከ መጨረሻው የተከተሉትም ነበሩ፡፡
ለዚህም ትልቅ ማሳያ የሚሆነን ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አይሁዳዊ ነው፡፡
ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህን ታላቅ ሰው ለማዘከር የዐቢይን ጾም ሰባተኛ እሁድ በእርሱ ስም ሰይማ ታከብረዋለች። ተከታዮቿ ምዕመናንም የእርሱን አሰረ ፍኖት እንዲከተሉ ትመክራለች ታስተምራለችም፡፡
=> ኒቆዲሞስ ማነው?
፩. ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ነው 《ዮሐ 3-1》
፪. ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ነው《ዮሐ 3-1》
፫. ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ነው《ዮሐ 3-10》
፬. ኒቆዲሞስ ምሁረ ኦሪት ነው 《ዮሐ 7-51》
=> ኒቆዲሞስ ምን አደረገ?
ለምስጢረ ጥምቀት መገለጥ ምክንያት ሆነ 《ዮሐ 3:1-21)
አዋቂ ነን የሚሉትን አሳፈራቸው 《ዮሐ 7-51》
ጌታን ለመገነዝ በቃ 《ዮሐ 19-38》
=> ከኒቆዲሞስ ምን እንማር?
አትኅቶ ርእስ ጎደሎን ማወቅ የእውነት ምስክር《ስምዐ ጽድቅ》መሆን ትግሃ ሌሊት እስከ መጨረሻ መጽናት በአጠቃላይ ከኒቆዲሞስ ህይወት ብዙ ቁምነገሮችን እንማራለን፡፡
የኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ መምጣት ለምስጢረ ጥምቀት ትምህርት መገለጥ ምክንያት እንደሆነ ሁሉ በቅዳሴው በኪዳኑ በሰዓታቱ በማኅሌቱ መገኘትና መሳተፍ ረቂቅ የሆነው ሰማያዊ ምሥጢር ፍንትው ብሎ አንዲገለጥልን ምክንያት ነውና በምሥጢራት በመሳተፍ ራስን ዝቅ በማድረግ ለታላቅ ክብር እንድንበቃ የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን፡፡
የዕለቱ ምስባክ፦ "ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ። አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕልየ። ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመ ሕያው"። መዝ17፥3-4። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ3፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር