"አንዴ ነው " ይሉኛል ፣ "በፍቅር መጎዳት"
"አንዴ ነው" ይሉኛል ፣ "ባመኑት መከዳት።"
እኔ ግን አላምንም!
ካለፈ ህይወቴ ፣ አላውቅም ተምሬ
አውቃለሁኝና
ብዙ ተጎድቼ ፣ ብዙጊዜ አፍቅሬ፡፡
።።።
በፍቅር መንገድ ላይ ፣ ተክዤ ተጉዤ
የማውቃቸው ሁሉ
የሸለሙኝን መልክ ፣ ጠባሳ ልብ ይዤ
አንቺ ጋራ ስደርስ...
ልብሽና ልቤ ፣ እንደተሳሳበ
እንዳዲስ ሳፈቅር...
ወደ ነፍሴ ምድር ፣ ጥያቄ ዘነበ፡፡
።።፣
ቆይ ስንቴ ነው መውደድ ፣ ስንቴ ነው መጎዳት
ቆይ ስንቴ ነው ማመን ፣ ስንቴ ነው መከዳት?
ለስንት ጊዜ ነው?
ሲሄዱ መራገም ፣ ሲመጡ መመረቅ?
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?
እርሜ ነው እያሉ ፣ በመሃላ መታረቅ?
ቆይስንት ጊዜ ነው?
መተው መርሳት ሲቻል፣ በማስታወስ ማፍቀር
ስንቴ ነው መታቀፍ ፣ ስንቴ ነው መገፍተር?
።።።
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?!
በብቸኝነት ውስጥ ፣ በአብሮነት መቀጣት?
ለካንስ ለካንስ
ለመንገደኛ ልብ
ተራ ጥያቄ ነው ፣ መሄድና መምጣት!
አቦ ወግጅልኝ!
መልስነው በራሱ
ለተራ ጥያቄ ፣ ተራ መልስ ማጣት!!!
Join & Sheri
👇👇👇
@naniyene
@naniyene @naniyene
@papa_ye
"አንዴ ነው" ይሉኛል ፣ "ባመኑት መከዳት።"
እኔ ግን አላምንም!
ካለፈ ህይወቴ ፣ አላውቅም ተምሬ
አውቃለሁኝና
ብዙ ተጎድቼ ፣ ብዙጊዜ አፍቅሬ፡፡
።።።
በፍቅር መንገድ ላይ ፣ ተክዤ ተጉዤ
የማውቃቸው ሁሉ
የሸለሙኝን መልክ ፣ ጠባሳ ልብ ይዤ
አንቺ ጋራ ስደርስ...
ልብሽና ልቤ ፣ እንደተሳሳበ
እንዳዲስ ሳፈቅር...
ወደ ነፍሴ ምድር ፣ ጥያቄ ዘነበ፡፡
።።፣
ቆይ ስንቴ ነው መውደድ ፣ ስንቴ ነው መጎዳት
ቆይ ስንቴ ነው ማመን ፣ ስንቴ ነው መከዳት?
ለስንት ጊዜ ነው?
ሲሄዱ መራገም ፣ ሲመጡ መመረቅ?
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?
እርሜ ነው እያሉ ፣ በመሃላ መታረቅ?
ቆይስንት ጊዜ ነው?
መተው መርሳት ሲቻል፣ በማስታወስ ማፍቀር
ስንቴ ነው መታቀፍ ፣ ስንቴ ነው መገፍተር?
።።።
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?!
በብቸኝነት ውስጥ ፣ በአብሮነት መቀጣት?
ለካንስ ለካንስ
ለመንገደኛ ልብ
ተራ ጥያቄ ነው ፣ መሄድና መምጣት!
አቦ ወግጅልኝ!
መልስነው በራሱ
ለተራ ጥያቄ ፣ ተራ መልስ ማጣት!!!
Join & Sheri
👇👇👇
@naniyene
@naniyene @naniyene
@papa_ye