✤✤ እንኳን ለማኅሌተ ጽጌ አደረሳችሁ፤
ምንም እንኳን በመጽሐፈ ገጽ (Facebook) ጽሑፎችን ማቅረብ ከጀመርን በርካታ ዓመታት ብናስቈጥርም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጽሐፈ ገጽ(Facebook) ፋና ወጊ ኾነን ሥርዐተ ማኅሌትን ይዘን መቅረብ ከጀመርን ግን 11ኛ ዓመታችን ኾነ፤ እንደ መድኀኔዓለም ፈቃድም ዘንድሮም 11ኛ ዓመታችን (የ1ኛ ዙር ዓመት ሙሉ የማኅሌተ ጽጌ ሥርዐተ ማኅሌትና በዓመት ውስጥ የሚገኙ የክብረ በዓላት ሥርዐተ ማኅሌትን ይዘንላችሁ እንቀርባለን፡፡)
✤ የማኅሌት ቁመት የላይ ቤትና የታች ቤት ኾኖ እንደየአድባራቱ ይትበሃል የሚቆም እንደመኾኑና ማኅሌተ ጽጌ በኹሉም አድባራት በደመቀ ኹኔታ ስለሚቆም የላይ ቤቱንም ኾነ የታች ቤቱን በአንድነት አቅርበንላችኋል፤ የላይ ቤት የምትቆሙ አድባራት ‹‹ዘግምጃ ቤት›› የሚለውን፤ የታች ቤት የምትቆሙ ‹‹ዘጎንደር በዓታ›› በሚል አስቀምጠንላችኋል፡፡ ደብራችን ቀጨኔ ደብረ ሰላም የላይ ቤት የሚቆምበት ደብር እንደመኾኑ ላይ ቤቱን እያስቀደምን ታች ቤቱን አስከትለን አስቀምጠናል፡፡ የላይ ቤት የሚቆምባቸው አድባራት የታች ቤቱን እየዘለሉ፤ የታች ቤት የሚቆሙ አድባራት የላይ ቤቱን እየዘለሉ እንዲጠቀመቡት ኹሉንም አዘጋጅተነዋል፡፡ የላይ ቤትና የታች ቤት በአንድነት የሚቆሙት ቀለም ሲኾን ግን ‹‹ዘግምጃ ቤት ወዘበዓታ›› ብለን አስቀምጠነዋል፡፡
/በማኅሌት በምትቆሙ ጊዜ በጸሎታችሁ ደብራችንን ደብረ ሰላምንና ሰ/ት/ቤታችንን ፍኖተ ሕይወትን እና በውስጧ ያሉ አገልጋዮቿን አስቡልን፡፡
✤ ልዩ አዋጅ ዘወርኃ ጽጌ ✤
✤ ወርኃ ጽጌ 40 ቀናት ነው፤ መስከረም 26 ተጀምሮ ኅዳር 5 ያልቃል፤ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ነው፡፡
✤ የማኅሌተ ጽጌና የሰቈቃወ ድንግል ደራሲ አባ ጽጌ ድንግል ነው፡፡ ገዳሙም ትልቅና ሰፊ የኾነ የፍልፍል ዋሻ ሲኾን ወሎ ወግዲ ወለቃ ወንዝ አጠገብ በረሃ ላይ (ከጋሥጫ ገዳም የ4 ሰዓት የእግር መንገድ) ይገኛል፡፡
✤✤ በየዓመቱ ሳይመረገዱ ያመይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ፤
1) ከማኅሌተ ጽጌ፦ ጽጌ አስተርአየ (የመጀመሪያው ሳምንት)፣ በከመ ይቤ መጽሐፍ፣ ትመስል እምኪ ማርያም፣ ዘኒ ስብሐተ ወዘኒ ማኅሌተ፣ ኢየሐፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ እና ኅብረ ሐመልሚል (የመጨረሻው ሳምንት)ናቸው፡፡
2) ከሰቈቃወ ድንግል፦ በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ፣ ብክዩ ኅዙናን፣ እስከ ማዕዜኑ እግዝእትየ እና አብርሂ አብርሂ ናቸው፡፡
✤ ከማኅሌተ ጽጌ ውስጥ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እና ክበበ ጌራ ወርቅ በየሳምንቱ (በኹሉም ዓመታት) ይመረገዳሉ፤ ዚቁ ግን በዓሉን በተመለከተ ይኾናል፡፡
✤ ከላይ ካየናቸው ውጪ የሚገኙት የማኅሌተ ጽጌና የሰቈቃወ ድንግል ክፍሎች ግን በየሰባት ዓመት አንዴ ነው የሚመረገዱት፡፡
✤ የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው፤
✤ የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ እንድትጠቀሙበት ኹሉንም አስቀምጠነዋል፡፡
@Nigatu5