One Love


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


❤️#ye fker kana❤️
❣ #ye fker kana
❣ #ye fker kana
❣ #One Love One Harte
❣One Love One Harte ❣
One Love one Harte
Join Join Join @one_love_one_heart12👈
. 📩 comment @lastboydagi

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций






















Chebsi Mood🍻🍻🍻

@one_love_one_heart12
@one_love_one_heart12

Comment
📩
@lastboydagi




የሚያልፈሰፍስ ነውና ለበደለህ ሰው ቅያሜህን ግለጥለት ፤
ቂመኝነት በክፉ መሸነፍ እንጂ ጀግንነት አይምሰልህ ።
ከህሊናህና ከመንፈሳዊ አማካሪህ ሳትመክር ምንም ነገር
አትወስን ፤ አጥርተህ ሳትሰማ ቃል አትግባ ። መከራ ካልደረሰ
በቀር ባል በሌለበት ቤት ውስጥ ከሚስቲቱ ጋር ብቻህን
አትቀመጥ ።
የሚበልጥህ ልኩራብህ እንዳይልህ ፣ ያነሰህ ልድረስብህ
ብሎ እንዳያጠፋህ የሀብትህን ልክ እንዳታወራ ፤ በገዛ አፍህ
ባንዱ ትከብራለህ ባንዱ ትቀላለህና።
በጣም በማክበርህ እንዳታመልከው ፤ በጣም በመናቅህ
እንዳታዋርደው ሠው እንዳንተ መሆኑን እወቀው ።
የእኔ መናገር ምን ይለውጣል? ብለህም ስህተትን አትለፍ ፤
የእኔ አስተዋፅኦ ምን ይጠቅማል ? ብለህም ስጦታህን አትጠፍ፣
መልካም ቃል ከስጦታ ይበልጣልና መልካም ቃል ተናገር፤
ማንኛውም ስጦታ ከልመና ወንበር አያስነሣም ። የተስፋ ቃል
ግን እንደሚያስነሣ አውቀህ ለሰዎች የተስፋ ቃል ስጣቸው ።
ትምህርት ለዕውቀት ያዘጋጃል እንጂ ዕውቀትን አይጨርስም
። ዕውቀትህን የምትይዝበትን ሥነ-ሥርዓት ግን ያሳይሃል ።
አእምሮህን ለማረቅ ትምህርት ፣ ሰውነትህን ለመግዛት
ትዕግስት ፣ ከማንም ጋር ለመኖር ሥነ-ሥርዓት ያስፈልግሃል ።
ለህሊናህ እረፍት ግን እምነት ያሻሃል ። ተከታይ ለማበጀት
ደግሞ ግልጽ መሆንና ታማኝነት ግድ ይልሃል ።
አንተው እውነትን ጠልተሃት ዘመኑ እውነትን ጠልቷል አትበል
። ዘመን እኔና አንተ ነን ፤ በራሱ ክፉና ደግ የሆነ ዘመን የለም።
መልካም ምክር ብትሰማ ሕይወት ቀላል ይሆንልሃል ።
ትክክለኛም ውሳኔ ከመልካም ምክር ነውና..!!
አንብበው ለወዳጅዎ ካላካፈሉት እንዲሁም የተሰማዎትን ካልፃፉ
ሲበዛ እራሥ ወዳድ ነዎት ማለት ነው!!!!

Share share share 👈
Join Join Join🙏🙏🙏
@one_love_one_heart12
@one_love_one_heart12
@one_love_one_heart12

Comment
📩
@lastboydagi


ጠቃሚ ምክር ለእርስዎ!
ይሄን ፅሁፍ ማንበብ 100 መፅሐፍት እንደማንበብ ነው!
★★★
በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ
፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣
ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ
ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር
የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል።
ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል
ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ
ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው
ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።
የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ
ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ
። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣
የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ
አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ
ጥሩ ነው አትበል ።
ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ
እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ
የመጣህበትን አትዘንጋ ።
የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት
ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን
ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ
ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው።
ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ
። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ
የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ።
ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም
ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣
ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ
አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም
ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ
ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።
ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው
ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል
አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ
የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር
አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ
መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው
ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ
አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን
በዝግታ ፈፅመው ።
እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ
እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ
እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም
እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ
ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት
አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ
፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ።
ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት
እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ።
በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን
የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና
ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።
የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤
የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።
ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ
ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ
መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ።
ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!
መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት
ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ
ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ
አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም
ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤
ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ።
ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም
ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት
ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ
ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው
ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ።
ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም
የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ
የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ።
ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው
ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን
ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት
ተጠንቀቅ ።
ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት
ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም።
ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው።
ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣
ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ።
በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ
ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።
የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ
እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ
ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን
እርዳቸው !!
ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ
፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ
ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን
ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት
ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ
ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።

ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው
ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው
የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ
ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን
እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና
በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል።
እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣
መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣
ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም
የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት
አትጠብቅ ።
የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ
እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ
ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን
እርዳቸው ።
ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት
እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው
መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ
ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣
ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።
ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ
፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ
ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን
ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት
ጠባይ ነውና ። ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ
እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።
ቂም አፍን የሚያመር ፣ ልብን የሚያነቅዝ ፣ ተግባርን
Join Join Join🙏🙏🙏
NEXT 👇👇👇👇👇👇
@one_love_one_heart12













Показано 20 последних публикаций.

147

подписчиков
Статистика канала