ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞች ❖


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


እንኳን ደህና መጡ 🙏
በቻናላችን ላይ በቀላሉ ❖ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችና ትምህርታዊ ፅሁፎችን ያገኛሉ።
.
✞ ባለማህተቦችን ወደ ቻናላችን ይጋብዙ!
.
ቻናል
@metshaf
@Orthodox_question
@Orthodox_film
@Orthodox_book
.
ግሩፕ
@Orthodox25
@Orthodox_tewahdo_group
.
ቦት
@EOTC_library_bot
@Orthodox2_bot

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


✝✝ #ማርያም_ማርያም ✝✝

ከእናቴ ማኅፀን ሾልኬ ስወጣ
ማርያም እንዳላችሁ ወደ ዓለም ስመጣ
ደግሞም በጊዜዬ የተጠራሁ ለታ
ተመልሼ ስሄድ ወደ ሰራኝ ጌታ
ያኔ የጭንቁ ቀን ስሟን የጠራችሁ
ዛሬም በረፍቴ ቀን ስሟን ዘክራችሁ
እንደ አመጣጤ እባካችሁ ላኩኝ
#ማርያም እያላችሁ ወዳጆቼ ሸኙኝ።

@orthodox_poem

@metshaf
@all_books_robot








Репост из: Vamos fixed game
✝ እንኳን ለቅዱስ ዑራኤል አመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን! ✝




Репост из: Vamos fixed game

#እግዚአብሔር_መልካም_ነው።

እግዚአብሔር መልካም ነው 
በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው 
ከገነት ሲሰደድ አዳም አባታችን 
ሞት ነግሶብን ሳለ በእኛ በሁላችን 
ቃል እንደገባለት ተወልዶ ሊያድነን
በመከራ ጊዜ መሸሸጊያ ሆነን

አብርሃም ከካራን ከእናት ከአባቱ ቤት 
ከነአን ሲገባ ሲሰደድ በእምነት 
ከተሰጠው ተስፋ አንዳች ሳይጎልበት 
እንደ ምድር አሸዋ ዘሩን አበዛለት

በሐዘን በችግር በመከራ ጊዜ 
ጭንቀቴን የሚያርቅ ነው የፍሴን ትካዜ 
የቀደመው እባብ ሰላሜን ሲነሳኝ 
እግዚአብሔር መልካም ነው ሐዘኔን አስረሳኝ 
የቀደመው እባብ ሰላሜን ቢነሳኝ 
ክርስቶስ ኢየሱስ ሐዘኔን አስረሳኝ 


@metshaf
@Orthodox25
@Orthodox_book
@Orthodox_question




Репост из: Vamos fixed game
​​#ቅዱስ_ገብርኤል

እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!!

በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል ነው፡፡ ይህ ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት የሚታሰብበት ዕለት ነው።
@metshaf
@EOTC_library_bot




Репост из: Vamos fixed game

እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው አብርሃም አባ_ሲኖዳ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

ሐምሌ 7 ሥሉስ ቅዱስ ለአብርሃም የተገለጠለት በቤቱም የተስተናገዱበት ዕለት ነው።

@metshaf




Репост из: Vamos fixed game

#እመቤቴ ማርያም እለምንሻለው


እመቤቴ ማርያም እለምንሻለው
በለቅሶ በዋይታ ፊትሽ ወድቄአለው
እመቤቴ ስሚኝ ተማጽኜሻለው

ሐዘኔን ጭንቀቴን ለማን እነግራለው
ችግሬን ጉዳቴን ለማን አዋያለው
እመቤቴ ስሚኝ ተማጽኜሻለው

ሐዘኑ በዛብኝ ፈተናው ከበደኝ
እንደምን ልቻለው እኔስ ብቻዬን ነኝ
የዐማኑኤል እናት ፈጥነሽ ድረሽልኝ

በጣም ተንገዳገድኩ ልወድቅ ነው እኔ
እመ አምላክ ደግፊኝ ቁሚልኝ ከጎኔ
ምንም አጋር የለኝ ከአንቺ በቀር ለእኔ

✞ ኦርቶዶክሳዊ ግጥም
@metshaf
@Orthodox_book
@Orthodox_question
@Orthodox25




Репост из: Vamos fixed game

በንስሐ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደር እና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም።

አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ




Репост из: Vamos fixed game

ወዳጆች ሆይ! ማፈር የሚገባን ኃጢአት ስንሠራ እንጂ ንስሐ ስንገባ አይደለም፡፡ ኃጢአት ሕመም ነው፤ ንስሐ ደግሞ መድኃኒቱ ነው፡፡ ከኃጢአት ቀጥሎ ሐፍረት አለ፤ ከንስሐ ቀጥሎ ግን በጌታ የኾነ ደስታ አለ፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ይህን ቅደም ተከተል አዛብቶብን በኃጢአት ስንደሰት በንስሐም እናፍራለን፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ







Показано 20 последних публикаций.

340

подписчиков
Статистика канала