⛪️ኦርቶዶክሳዊ ግጥም📜


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


በዚህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ ግጥም እና መነባንብ ለምእመናኑ ይቀርባሉ
በቻናሉ እንዲለቀቅላችሁ ምትፈልጉት ግጥም ካለ እንዲሁም አስተያየት ለመስጠት @asrategabriel ላይ ያናግሩን
.
.
.
.
መንፈሳዊ ቻናሎቻችን
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




Репост из: የግዕዝ ቋንቋ መማርያ
🕯እንኳን ለጻድቁ አባት አባ ተክለሃይማኖት የልደት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ በዓሉን እስመልክቶ ድንቅ እና ተወዳጅ የሆኑትን የተክለሃይማኖት መዝሙራት አቅርበንሎታል ይጋበዙ 🧧

https://youtu.be/xRh0qSRXJJs


📜የወንጌል ገበሬ ጽድቅን ሰጠን ፍሬ📜

እግዚአብሔር...
ሊያድነን ፈልጎ ምህረትን ሲያበዛ
ምክንያት ሲፈጥርልን ለነፍሳችን ቤዛ
ገና ከማኅፀን ወዶ የመረጠው
ለክብር የታጨ ባርኮ የቀደሰው

አባታችን...
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ
ኃጢአትን አክስሮ በይቅርታ የሚክስ
ለእኛ የተፈጠረ የወንጌል ገበሬ
ተደባልቆ እንዳይቀር ብስሉ ከጥሬ
በሃይማኖት መንሹ አበጣጥሮ ለየ
እመነቱን ያጸና በተጋድሎ ያቆየ
ዛሬም...
ቃልኪዳኑ ተርፎ ዓለምን አጥግቧል
ተክለሃይማኖት ብለን የጎደለ ይሞላል
በጻድቁ አባት ጥላ ሁሉም አርፏል
ቃሉ ለማይሻር አምላክ ምን ይሳነዋል?

ምንም!
ነብይን በነብይ ስም የሚቀበል የነብዩን ዋጋ ይቀበላል
ጻድቁንም በጻድቅ የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል
ማቴ 10፥41

✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞

አቅራቢ ፦ ⛪️ኦርቶዶክሳዊ ግጥም📜

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@Orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺




​​📜ለጣዖት አንሰግድም📜

​​በዘመነ ንጉስ ናቡከደነፆር
ለቆመ ጣዖት ሁሉም ይሰግዱ ነበር

ለጣዖት አንሰግድም፡ አሉ ሶስት ህፃናት
ከእሳቱ ይጣሉ፡ በተባሉ ሰዓት
አሁንም አንሰግድም፡ አሉት በኩራት
እግዚአብሔር ያድናል፡ ከእቶኑ እሳት
ባያድነን እንኳ አንሰግድም ለጣዖት።

ተጨንቀው ባሉበት፡ በጠሩህ ሰዓት
ገብርኤል መልዕክ፡ አዳንካቸው ከእሳት
እኔንም አድነኝ ፡ከዚህ አለም ስሜት
ነግሶብኛልና ፡የስጋ ፈተና የስጋየ ምኞት
እግዚአብሔር አድለኝ የአናንያን ፅናት
እግዚአብሔር አድለኝ የአዛሪያን ትጋት
እግዚአብሔር አድለኝ የሚሳኤልን ሀብት
የራማው ገብርኤል፡አብሳሪ ተፍስህት
ክብር ይገባሃል፡ሊቀ መላዕክት
ተራዳኤችን ነህ፡ በቀን በሌሊት
ሰላምነው ፍሰሀ፡ አንተ ባለህበት
ህይወቴን ባርክልን፡ ግባ ወደኔ ቤት
መጋቢ ሀዲስ ነህ፡የሰላም አብሳሪ
የእግዚአብሔር መለአክ ፡ሰይጣንን አሳሪ


እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በአል በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን።
የእግዚአብሔር መላእክ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ
ገብርኤል ከክፉው ሁሉ ይጠብቀን!

✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞

አቅራቢ ፦ ⛪️ኦርቶዶክሳዊ ግጥም📜

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@Orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺


📜ቅዱስ እስጢፋኖስ📜

ድንጋይ እንደ ዝናብ ፣ ሲወርድ የታገሰ፤
ሲወግሩት ይቅር ፣ በል እያለ መለሰ፡፡
ስጋውን ለመግደል፣ እጅጉን ቢለፉ፤
ቀዳሜ ሰማዕት፣ አርገውት አረፉ፡፡

✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞

አቅራቢ ፦ ⛪️ኦርቶዶክሳዊ ግጥም📜

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@Orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺


📜ኪዳነ ምህረት እናቴ📜

አውቃለሁ እኔ ጎስቋላ ነኝ
ምንም ጽድቅ ያልሰራሁኝ
ህይወቴን በሃጢያት ያሳለፍኩኝ
ዛሬም መመለስ የተሳነኝ
ራሴን መግዛት ያቃተኝ
አውቃለሁ አንዳችም ምግባር እንደሌለኝ።

ደንግል በኪዳንሽ ልብሽን ይራራልኝ
እንደ በላኤ ሰብዕ የሚያደርገኝ
አንቺ ግን እንኳንስ ለሰው
አምላክ በአምሳሉ ለፈጠረው
አይደለሽም እንዴ?
ለውሻ እንኳን ያዘንሽ
ውሀ ጽሙንም ያስታግስሽ።

አንድ ቀን በድንገት ቢጠራት
ነፍሴን ለፍርድ ቢያቆማት
አውቃለሁ በስራዋ እንዳትሟገት
በጽድቋም እንዳታገኝ ምህረት።
ግን አንዲት መመኪያ አለቻት
ዋስ ጠበቃዬ ምትላት

ከእሳት ለመዳን ከልቧ ምትጠራት
እርሷም አንቺው ነሽ ኪዳነ-ምህረት
አደራ ድንግል እንዳትተያት
ለነፍሴ መዳን ምክንያት ስለ ሆንሻት።

እኔም እወድሻለሁ ልበል እንደልጅነቴ
ንጽሕት ዘሥጋ ወነፍስ ኪዳነ ምህረት እናቴ😍


✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞

አቅራቢ ፦ ⛪️ኦርቶዶክሳዊ ግጥም📜

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@Orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺


📜እናቴ ስማፀን በስምሽ📜

ድንግል ማርያም ብዬ ስማፀን በስምሽ
በቅድመ እግዚአብሔር ልመናዬን አድርሽ
እኔ ደካማ ነን ኃጢአቴ የበዛ
እኔ ጎስቋላ ነኝ በደሌ የበዛ

ጊዜዬን ያባከንኩ በዋዛ ፈዛዛ
ጊዜዬን ያባከንኩ በከንቱ በዋዛ
እመብርሃን ስልሽ ፈጥነሽ ድረሽልኝ
ልመናዬን ሰምተሽ ቆመሽ ለምኝልኝ
ኃጢአቴ ቢበዛም ይዣለው አንችን
አስምረሻልና በላዔ ሰብን
አንገቴን ቢያስደፋኝ በዝቶብኝ ኃጢአቴ
ምልጃሽን ፈለኩኝ ድንግል ሆይ እናቴ

ያን ክፉ ጨለማ እንዳላይ አደራ
ድንግል ሆይ ከልይኝ ከዲያብሎስ ጭፍራ
እመብርሃን እያልኩ ቆሜ ከደጅሽ
በብርሃን እጆችሽ እንባዬን አብሽ
አለም አታላይ ነች ወደሷ ተሳብኩኝ
ታማልጅኝ ብዬ አንቺኑ ተራብኩኝ


✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞

አቅራቢ ፦ ⛪️ኦርቶዶክሳዊ ግጥም📜

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@Orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺




📜ሚካኤል📜

ዳንኤል ተናገር፣ ባህራን ተናገር፤
ሚካኤል ሲመጣ፣ የሆነውን ነገር፡፡
የአንበሳውን ጉድጓድ፣ ምሰጋና ሞልቶታል፤
የሞቱን ደብዳቤ፣ ህይወት ዘርቶበታል፡፡

የሞት ጽሁፍ ይዤ፣ ወደ ሀገሬ ስሄድ፤
የሚታደግ መላክ፣ ጠበቀኝ ከመንገድ፡፡
ሚካኤል ወዳጄ፣ ፍርዴን ለውጦታል፤
የሞቴን ቀዶ ጥሎ፣ ሰርጌን ደግሶታ
ል፡፡
የዳንኤል ወዳጅ፣ ለኔም ወዳጄ ነው፤
የአንበሶቹን አፍ በሰይፍ የዘጋ ነው፡፡
የኔንም ነካሾች፣ አጥፍቶ በሰይፉ፤
የተራቡ አንበሶች፣ ሳይነኩኝ አለፉ፡፡

✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞

አቅራቢ ፦ ⛪️ኦርቶዶክሳዊ ግጥም📜

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@Orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺




📜ሰላም ተዋሕዶ📜

ሰላም ተዋሕዶ ሰላም ኦርቶዶክስ
የአትናትዮስ ሐውልት የዲዮስቆሮስ
የአዳም መመኪያ የሔዋን ሀገር
አንቺ አይደለሽም ወይ የቅዱሳን ክብር

የአብርሃም ቃልኪዳን የአቤል መስዋዕት
የሔኖክ ሃይማኖት ያዳንሽው ከሞት
አንቺ የኖህ መርከብ ዕፀ መድኃኒት፡፡
በአብርሃም ድንኳን ተወልደሽ ያደግሽ
የይስሐቅ መአዛ ወደር የሌለሽ
የዮሴፍም አፅናኝ ተዋሕዶ ነሽ

የሙሴ ጽላት ነሽ የአሮን በትር
የኢያሱ ሐውልት የጌዲዮን ፀምር
የሳሙኤል ሙዳይ የእሴይ ትውልድ
የዳዊት በገና የሰሎሞን ዘውድ
የታተመች ገነት የምስጢር ጉድጓድ፡፡
ቱሳሔና ሚጠት ውላጤም ጭምር
ያልተቀላቀለሽ ንጽሕቲቱ ምድር
ኢሳይያስም አይቶ በሩቅ መነፅር
ስለ ቅድስና ሆነ ያነቺ ምስክር፡፡

የነ ኤልያስ ቤት የወርቅ መሶብ
ውስጥሽ የተሞላ የምስጢር ምግብ
የኤልሳ ማሰሮ የሕይወት መዝገብ፡፡
ፋራን የምትባይ የእንባቆም ተራራ
ሁሉንም የምታሳይ በቀኝም በግራ
የሕዝቅኤል አልፍኝ ባለ አንድ በራፍ
የማትከፈችው የኬልቄዶን ቁልፍ፡፡

የሕግ መፍለቂያ የነፃነት ቦታ
የሚክያስ ሀገር አንቺ ነሽ አፍራታ፡፡
በውስጥም በውጭም የሌለብሽ እንከን
የሕይወት መዝገብ ነሽ ተዋሕዶአችን
ሐዋርያት ይምጡ ያውሩ ያንቺን ዜና
የሚያውቅ ሲናገር ደስ ያሰኛልና፡፡
ሰማዕታት ልጆችሽ የፃፉልሽ በደም
የሕይወት መጽሐፍ ነሽ የጽድቅ የሰላም


✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞

አቅራቢ ፦ ⛪️ኦርቶዶክሳዊ ግጥም📜

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@Orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺




📜አትናቅ📜

በዘር በወገንህ ከመመካት ራቅ
የፈለገ ቢወድቅ የፈለገ ቢደቅ
ሰው ሆነህ ተፈጥረህ ሰዎችን አትናቅ!
ያደርገዋልና የተዋረዱን ከፍ የከበሩትን ዝቅ

ቢኖርህ አትመካ ፡ሙሉ አካል ከጤና
ምን ትሆን ወደፊት ከቶ አታውቅምና፡፡
አለኝ ብለህ አትናቅ ወርቅ ብር ገንዘብ
ሀላፊ ነው እና ጌታ እንዳይታዘብ።

የሚመካ ቢኖር፡ ኑ ከዚህ አለ ሀይል
በእግዚአብሔር ማዳን ነው በመከራው መስቀል።
አላዛርም ነዌም ደሀውም ሀብታሙም
ክፉው ዘረኛውም ከቶም ያልፋል ሁሉም

በጎ ስራ ገና ይኖራል ዘላለም፡፡
ዘርህ አንተ ምነው ቅማንት ወይ አማራ?
ይህን አትጠየቅ! ስምክን አትጠራ!
( ምነው ታዲያ )
ዘሬን እየጠራህ ማለትህ አህያ
ምርጥ ነን ማለትህ ሰውስ ከኛ ወዲያ!
አህያን ብታውቃት ጌታ ሰጧታል ክብር
የከበረ አምላኳ ተቀምጦባት ነበር፡፡

በአንድ አምላክ ተበጅተን
ከአንድ አዳም ተፈጥረን
ከሰዎች ልዩ ነን ማለትህ ምን ይሆን?
(እርሱ ይወቅልህ)
በዘር በወገንህ ከመመካት ራቅ፣
የፈለገ ቢወድቅ የፈለገ ቢደቅ፣
ሰው ሆነህ ተፈጥረህ ሰዎችን አትናቅ!
ያደርገዋልና የተዋረዱን ከፍ የከበሩትን ዝቅ።

ሉቃ 1÷51-53
ማር 11÷7
ገላ 6÷14

✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞

አቅራቢ ፦ ⛪️ኦርቶዶክሳዊ ግጥም📜

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@Orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺


📜በዓታ ለማርያም📜

በተወለደች፣ በሶስት አመቷ፤
መቅደስ አመጧት፣ እናት አባቷ፡፡
ካህኑ ዘካርያስ፣ ቀኑን ያሳይሀል፤
ባርያውን በሰላም፣ ያሰናብትሁል፡፡

ማን ይመግባታል፣ ብለህ አትጨነቅ፤
ወላዲተ አምላክ፣ መሆኗን ሳታውቅ፡፡
ቅዱስ ሩፋኤል፣ ክንፎቹን ዘርግቶ፤
ይመግባት ነበር፣ ከሰማያት መቶ፡፡
ሙሽራዬ ሆይ፤
ከሊባኖስ ነይ፡፡
ልጄ ስሚኝ ይላል፣ አባትሽ ዳዊት፤
የልዑል ማደርያው፣ ስትሆኚ ታይቶት፡፡

በዓታ ለማርያም፤
ስጪን ፍቅር ሰላም፤



✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞

አቅራቢ ፦ ⛪️ኦርቶዶክሳዊ ግጥም📜

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@Orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺


📜ልደትሽ ልደታችን ነው📜

አንቺ ስትወለጅ ፥እኛም ተወለድን፣
ገና በልጅነት፥ ቤተ መቅደስ ሄድን
ማርያም ስትወለጅ፥ ልደታችን ሆነ፣
እንኳንስ ያመነሽ፥ ያላመነሽ ዳነ።

የአምላክ እናቱ፥ ልደታ ማርያም፣
በግንቦት ተወልደሽ፥ ተምሯል አለም
ልጅሽ ወዳጅሽ፥ ሰላማችን ነው
የልደትሽ ቀን፥ ልደታችን ነው፣
በሄዋን ቢዘጋ፥ የገነት ድንበሩ፤
ባንቺ ተከፈተ፥ የሰማያት በሩ።
ባንቺ ልደት፥ ቀን ሆነ ልደት፣
አዳምም ገባ፥ ወደ ገነት።

የእናት ክብር ታየ፥ ከፍ ብሎ፣
በድንግል ጀርባ ላይ፥ ፋሲካችን ታዝሎ።
ከሴቶቹ መካከል፥ አንቺን ለይቶሽ፣
አምላክ አንቺን ሰጠን፥ እንድንድንብሽ።

ከሴቶች መካከል ብፅይት ነሽና
ደግሞ ከጦር እና ሞቱ ጠብቂን በደህና


✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞

አቅራቢ ፦ ⛪️ኦርቶዶክሳዊ ግጥም📜

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@Orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺






📜ስውር ቅኔ📜

የቤተ ክርስትያን ደጅ ዕለት ተለት ስሜ
በፆም እና ፀሎት በስግደት ደክሜ
አምላኬን ለመንኩት
የሚያስፈልገኝን ሳልደብቅ ዘርዝሬ ነገርኩት

የሚያስፈልገኝ ነገር ቢዘገይም ጊዜ
ነፈከኝ ብዬ በምሬት አንካሴ
ፈጣሪን ወጋሁት
ልቡን አደማሁት
በስርዓት አጥ ምሬቴ
በአጉል ምኞቴ
ልቡ ስለቆሰለ
በደመና መሀል ጌታዬ እንዲህ አለ

‹‹ሁሉን የማቀው እኔ ሆኘ ሳለ
ነፈከኝ ለማለት ምነው ልቦናህ ቸኮለ
ዘርዝረህ የላከውን የልመና ፀሎት
ይመለከተው ዘንድ ዐይኔ ተተከለ
የምትፈልገው እንጅ የሚያስፈልግህ አንድም እንደሌለ
የታዘበው እጄ የጠየከኝን ከማድረግ ተከለከለ
ግና ልጄ አዕምሮህ በደንብ ካሰተዋለ
ባለማድረግ ውስጥም ታላቅ ማድረግ አለ>>


✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞

አቅራቢ ፦ ⛪️ኦርቶዶክሳዊ ግጥም📜

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@Orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺



Показано 20 последних публикаций.

2 012

подписчиков
Статистика канала