እንዴት አልወድሽም ከዚያች እፅ በኋላ••••
•
ስሜ ብቻ ያ ለግብር~መሰናከያ ነው አንዳች መጥፎ እጣ
ፃድቅ ጠልፎ የሚጥል~ከፃድቅ 'ርስቱ ገነት አንዳይወጣ
ነብያቱ ሁሉ ቅዱስ ያደርጉና~የድል መዝሙራቸው "ምን አረግንሽ ሔዋን ?"
የመርገም ጨርቅ ሆነ~ስራችን በሙሉ በስምሽ እርግማን
ይሔንን መሸከም ~ለሴት ዘር ይከብዳል
ከከለዳውያን የእሳት ነድ እጥፍ~ነፍስ አጥንት ያነዳል
•
ስሜን አዳንሽልኝ!!
•
የኢሳያስን ግርማ~ፈርቶ ቆም ያላለ
ከደግ አብርሀም ቤት~አዝኖለት ያልዋለ
ሲሔድ የነበረ~ሲያስለቅስ የኖረ
ትህትናሽ ጣለው~እግርሽ ስር አደረ
አመሰግናለሁ~ደግሞ እወድሻለሁ
ከማንም ከምንም~የዳነው ስሜ ነው
•
እንዴት ያለ አምላክ~ለዛ ሁሉ ፃድቅ ምህረት የነፈገ
ያ የጨከነ መልክ~ደስ ላሰኘው ልብ ጥቂት ያልፈገገ
ምን ቢያገኝ ደስ አለው~አንዴት ያለ መባ
የሺ ዘመንን ሰው~ይሁን በጄ ብሎ ገነት የሚያስገባ ?
•
ስምሽ ይገርመኛል ~ብቻ ስሜ ዳነ !
በጠሉኝ ብሉያን ለፅድቅ ተለመነ
ሴትነቴ አበበ ቀና አረገኝ ክብርሽ
ከአዳምስ በላይ~እንዴት እኔ አልወድሽ ?
•
ከዚያች እፅ በኋላ ላየው ያልደፈርኩት ሰማይ ኮከብ ሆነ
አመሰግናለሁ~ ማርያም በሚል ስም ሴትነቴ ዳነ!!
ቤተልሔም ታችበል
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
ሼር @sheelff
ሀሳብ አስተያየት @yeneta
•
ስሜ ብቻ ያ ለግብር~መሰናከያ ነው አንዳች መጥፎ እጣ
ፃድቅ ጠልፎ የሚጥል~ከፃድቅ 'ርስቱ ገነት አንዳይወጣ
ነብያቱ ሁሉ ቅዱስ ያደርጉና~የድል መዝሙራቸው "ምን አረግንሽ ሔዋን ?"
የመርገም ጨርቅ ሆነ~ስራችን በሙሉ በስምሽ እርግማን
ይሔንን መሸከም ~ለሴት ዘር ይከብዳል
ከከለዳውያን የእሳት ነድ እጥፍ~ነፍስ አጥንት ያነዳል
•
ስሜን አዳንሽልኝ!!
•
የኢሳያስን ግርማ~ፈርቶ ቆም ያላለ
ከደግ አብርሀም ቤት~አዝኖለት ያልዋለ
ሲሔድ የነበረ~ሲያስለቅስ የኖረ
ትህትናሽ ጣለው~እግርሽ ስር አደረ
አመሰግናለሁ~ደግሞ እወድሻለሁ
ከማንም ከምንም~የዳነው ስሜ ነው
•
እንዴት ያለ አምላክ~ለዛ ሁሉ ፃድቅ ምህረት የነፈገ
ያ የጨከነ መልክ~ደስ ላሰኘው ልብ ጥቂት ያልፈገገ
ምን ቢያገኝ ደስ አለው~አንዴት ያለ መባ
የሺ ዘመንን ሰው~ይሁን በጄ ብሎ ገነት የሚያስገባ ?
•
ስምሽ ይገርመኛል ~ብቻ ስሜ ዳነ !
በጠሉኝ ብሉያን ለፅድቅ ተለመነ
ሴትነቴ አበበ ቀና አረገኝ ክብርሽ
ከአዳምስ በላይ~እንዴት እኔ አልወድሽ ?
•
ከዚያች እፅ በኋላ ላየው ያልደፈርኩት ሰማይ ኮከብ ሆነ
አመሰግናለሁ~ ማርያም በሚል ስም ሴትነቴ ዳነ!!
ቤተልሔም ታችበል
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
ሼር @sheelff
ሀሳብ አስተያየት @yeneta