STUDENTS NEWS ®


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


#student_NEWS🙌
🔰እንኳን ደና መጡ 🔰
⚫ለተማሪዎች በቀላሉ የትምህርት መረጃዎችን, መፅሀፎችን
📌ኖቶችን
📌 ትምህርታዊ ቪዲዮዎች
📌ሁሉንም በቀላሉ እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ቻናል ነው።
📚 students news Official Channel 🇪🇹

@student_newssss
@student_newssss
@student_newssss

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ምክር ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች

የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች እንኳን በጉጉት ስትጠብቁት ለነበረው ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ሳምንት በሰላም አደረሳችሁ። ይህ ለእናንተ ወሳኝ ጊዜ ነው። እስካሁን ትምህርታችሁን እያጠናችሁ ቆይታችኋል። መልካም ነው። ነገር ግን በፈተና ወቅት የምታከናውኗቸው ተግባራትም የጥናታችሁን ያህል ውጤታችሁ ላይ ተጽዕኖ አላቸው። ስለዚህ በዚህ ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባችሁና ምን ማድረግ እንደሌለባችሁ ጠንቅቃችሁ ማወቅ ይጠበቅባችኋል። ለዚህም ይረዳችሁ ዘንድ የሚከተሉትን ምክሮችን ከወዲሁ ተረድታችሁ ለመተግበር ዝግጁ ሁኑ!

⓵ በዋዜማው ስልክ መዝጋትና ከሚረብሹ ነገሮች ራስን ማራቅ ያስፈልጋል። ስልካችሁን መዝጋት ሀሳባችሁን ሊሰርቁ ከሚችሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች መራቅ ይገባችኋል። በዚህ ወቅት ትኩረታችሁን ፈተናችሁ ላይ ብቻ አድርጉ፤

⓶ በቂ እንቅልፍ ተኙ። በፈተና ዋዜማ ለማንበብ ብላችሁ በፍጹም አታምሹ። ባጭሩ በዚህ ቀን ተጨማሪ ሰዓት ከማንበብ ይልቅ ተጨማሪ ሰዓት መተኛት የተሻለ ዉጤት አለው። በቂ እንቅልፍ አለመተኛት በፈተና ወቅት ለድብርትና ለራስ ምታት ሊዳርግና ሥራችሁን ሊያበላሽ ይችላል። ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት ከባድ ምግቦችን አለመመገብ፤ ብዙ ቡና አለመጠጣት፤ እና ሌሎች አነቃቂ ነገሮችን አለመውሰድ ይመከራል፤

⓷ ጠዋት ማልዶ መነሳት: በጊዜ ተነስቶ መዘጋጀት ከመቻኮል ጋር ተያይዞ ከሚመጣ መታወክ ያድናል። በተጨማርም ወደፈተናው አዳራሽ በጊዜ ለመድረስ ያስችላል፤

⓸ ቁርስ በአግባቡ መብላት: በፈተና ወቅት ቁርስ አለመብላት አእምሮአችን የሚፈልገውን ያህል ኃይል እንዳያገኝ ስለሚያደርግ ለማሰብ አቅም እንዲያንስ ያደርጋል። ስለዚህ ቀለል ያሉ ምግቦችን ተመግባችሁ መሄድ ይኖርባችኋል። ከባድ ምግቦችን መመገብ ደግሞ አእምሮአችን ምግብ የመፍጨት ሥራ ላይ ብቻ እንዲወጠር ስለሚያደርግ ድካምና እንቅልፍ ያመጣል፤

⓹ ወደ መፈተኛ ቦታው ፈተናው ከሚጀምርበት ሰዓት በፊት ቀድሞ መድረስ ያስፈልጋል። ይህም ለመረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው፤

⓺ ከቤት ስትወጡ የፅህፈት መሳሪያዎቻችሁንና የመታወቅያ ካርዳችሁን መያዛችሁን እርግጠኛ ሁኑ። ይህም ከመንገድ ከመመለስና ከማርፈድ ያድናችኋል። ትርፍ እርሳሶችን እና የእርሳስ መቅረጫዎች መያዝ በጣም አስፈላጊ ነው፤

⓻ ወደ ፈተና አዳራሽ ከመግባት በፊት ወደ መፀዳጃ ቤት መሄድ መልካም ነው። ምናልባት የፈተናው ሰዓት ረዥም ቢሆንና ሽንት ቢይዛችሁ መጨናነቅን ያመጣል። አቋርጣችሁ መውጣት ላይፈቀድላችሁ ይችላል፤

⓼ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ ስማችሁን በአግባቡ መጻፋችሁን እርግጠኛ ሁኑ። አንድ ፊደል እንኳን ብትሳሳቱ ኋላ የት/ት ማስረጃችሁ ላይ ስለሚቀመጥ ለማስቀየር ዋጋ ያስከፍላል፤

⓽ መመሪያዎችን (instructions) በአግባቡ ማንበብና መተግበር ያስፈልጋል። በእያንዳዱ ፈተና ወረቀት ላይ ወይም የፈተናው ክፍሎች ላይ የሚሰጡትን መመሪያዎች በአግባቡ ማንበብና መተግበር ይኖርባችኋል፤

⓾ አትደንግጡ! በደንብ ተንፍሱ! ብዙ ኦክስጂን ወደ ውስጣችን ማስገባት ብዙ ምግብ እንዲቀጣጠልና ኃይል እንዲመረት ስለሚያደርግ ጉልበትና ድፍረት ይጨምርላችኋል፤

⓫ መልስ መመለስ ከመጀመራችሁ በፊት እያንዳንዱ የፈተና ክፍል ስለያዛቸው የጥያቄ አይነቶች ገረፍ ገረፍ እያደረጋችሁ ብታዩ መልካም ነው። ይህም የተሰጣችሁን ሰዓት በጥያቄው ክብደት ልክ ከፋፍላችሁ ለመጠቀም ያግዛችኋል፤

⓬  አንዱ ጥያቄ ከከበዳችሁ ዝለሉት፤ አንድ ጥያቄ ላይ ተጠምዳችሁ ብዙ ጊዜ የምታጠፉ ከሆነ ቀጥለው ለሚጠብቋችሁ ጥያቄዎች ጊዜ ሊያጥራችሁ ይችላል። ስትዘሉት ግን የጥያቄ ወረቀቱ ላይ ምልክት ማድረጋችሁን እንዲሁም መልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ ከተሰጡት አማራጮች አንዱን መልስ በግምት ማጥቆራችሁን አትርሱ። አጥቁሮ ማለፍ ምናልባት በኋላ የተሰጠው ጊዜ ቢያልቅና ወደ ጥያቄው መመለስ ቢያቅታችሁ መልስ መስጫ ቦታው ባዶ ሆኖ እንዳይቀር ያደርጋል፤

⓭ ቶሎ ለመውጣት አትቸኩሉ፤ ምንም አይጠቅማችሁም፤ ሰዓታችሁን አሟጥጣችሁ መጠቀማችሁን፤ ሁሉንም ጥያቄዎች በአግባቡ መመለሳችሁንና ማጥቆራችሁን አረጋግጡ። ጊዜ ቢተርፋችሁ ጥያቄዎቹን ለመከለስ ተጠቀሙበት፤

⓮ ያልገባችሁ ማንኛውንም ነገር ሲኖር ፈታኞችን ለመጠየቅ አትፍሩ (ከመልስ በስተቀር😉)፤

⓯ ልክ የፈተና ወረቀቱን ከመለሳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የዚያ ትምህርት (subject) ነገር ማክተሙን በመገንዘብ ለቀጣዩ ፈተና እራስን ማዘጋጀት ይገባል። እንጂ፤ ስላለፈው ፈተና እያሰላልሰሉ መጨነቅ ለቀጣዩ ፈተና በምታደርጉት ዝግጅት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል።

መልካም ፈተና


➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

◉⇲ @student_newssss ⇲◉
◉⇲ @student_newssss ⇲◉


ለ2ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ፦

- ብሔራዊ ፈተናው ከሐምሌ 19 እስከ 30 ቀን 2015 ዓ/ም ድረሰ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

- ለብሔራዊ ፈተናው የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 16 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ ይሆናሉ።

- የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ ከ869 ሺህ በላይ ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

- ፈተናው ለመውሰድ 869 ሺህ 765 ተፈታኞች በኦንላይን ተመዝግበዋል።

- ለፈተናው የተመዘገቡት 503,812 የሶሻል ሳይንስ እንዲሁም 365,954 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ናቸው።

- የፈተና አስፈጻሚዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ምልመላ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተከናውኗል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት #student_newssss ቴሌግራ
ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
👇👇👇👇👇👇👇
@student_newssss
@student_newssss
@student_newssss


#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምርቃት ስነ-ስርዓት በቀጣይ ሳምንት ያካሒዳል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የሁሉም ካምፓሶች የምርቃት ስነ-ስርዓት በተመሳሳይ ጊዜ ሐሙስ ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ አሳውቋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት #student_newssss ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
👇👇👇👇👇👇👇
@student_newssss
@student_newssss
@student_newssss

Показано 3 последних публикаций.

13

подписчиков
Статистика канала