📖 ቁርአን ለሁሉም የመጣ ፤ ሁሉንም የሚመለከት መፅሃፍ ነው ። ሰዎችን ዘር ቀለም ሳይመርጥ ሰው ስለሆኑ ብቻ ትልቅ ክብር አጎናፅፏቸው "ወለቀድ ከረምና በኒ ዓደም" ብሎ ሃያሉ ጌታ እነሱን ያነጋገረበት መፅሀፍ ነው🤌 "ሊኡንዚረኩም ቢሂ ወመን በለጝ" በቁርዓኑ እናንተንና ቁርዓኑ የደረሳቸውን ሁሉ ላስጠንቅቅበት ነው በላቸው ይላል ። እንግዲህ ቁርአን ደርሶት ቀይ ይሁን ጥቁር ፤ ሰው ይሁን ጂን "አልቀበልም" ያለ ሁሉ የሚመጥነውን ቅጣት ያገኛል ። በፀጋ የተቀበለ ሁሉ ደግሞ ለወዳጆቹ ያዘጋጀውን ሽልማት ይረከባል ። "ፈዘርኒ ወመን ዩከዚቡ ቢሃዘል ሀዲስ" እኔንና ይህንን ወደ አንተ ያወረድኩትን ንግግሬን የሚያስተባብል ሰው ተወን .. የምንገናኝበት ቀን አለ ። "ሰነስተድሪጁሁም ሚን ሃይሱ ላየዕለሙን" ፣ "ወመን የክፉሩ ቢሂ ሚነል አህዛቢ ፈናሩ መውኢዱህ" ቁርዓንን የካደ ቀጠሮው እሳት ናት!
ረሱል ﷺ «ወደ ቀዩም ፣ ወደ ጥቁሩም ተልኪያለሁ» ይላሉ .. ቀይ ማለት ሰው ፥ ጥቁር ማለት ጂን ነው ያሉ አሉ ። ደግሞ "ያመዕሸረል ጂኒ ወልኢንስ" እያለ እያነጋገረ "ሰነፍሩጙ ለኩም አዩሃ ሰቀላን" ብሏል እሱ ..
ይሄ ቁርአን የደረሰው ሁሉ ሊረዳው ፣ ሊያስተውለው ይጠበቅበታል ። አዋቂዎች ደግሞ አቅም በፈቀደ ለሰው ማድረስ ግዴታ አለባቸው ።
ማዕናውን መተንተን ፣ ህግጋቶቹን ማብራራት ፣ ለሰው ልጆች እንዲደርስ ማድረግ አማና ነው "ለቱበይኑነሁ ሊናስ" ለሰዎች ታብራሩ ዘንድ ግድ ተደርጎባችኋል ይላል ..
ይህን ሲባሉ የመፅሀፉ ባለቤቶች ከጀርባቸው ኋላ ወረወሩት ። ጥቂት ዋጋንም ሸመቱበት (አለማዊ ህይወትን ማለት ነው)
ኢልምን ትተው ወደ ዱንያ ስለዞሩ ፣ ፍቅረ-ነዋይ ስለጠለፋቸው ፣ አለማዊ ስኬትን በማሳደድ ስለተጠመዱ ከአሏህ ጋር ያላቸው ግንኙነት ፈረሰና የእሳት ራት ሆኑ ። እኛም እዛ ጉድጓድ መውደቅ የለብንም ። መፅሀፉን ላይ ላዩን ያነቡታል እንጂ ጠለቅ ብለው አልተጠቀሙበትም ። ገባ ብለው አላስተዋሉትም ።
ያ የአህለል ኪታብ ውድቀት እኛንም እንዳይደርስብን እነሱ የተሳሳቱት ቦታ ላይ መሳሳት የለብንም ። አሏህ እንዳወረደው ፤ ነብዩ እንዳደረሱት ለሰዎች ማድረስ ግዴታ ነው ማለት ነው ።
አሏህ ቀልባችንን ያርስልን ዘንድ ፤ ልባችንን ወደ ቁርዓኑ መለስ ያደርግልን ዘንድ እየለመንነው "መንሷረ አለደርቢ ወሶል" ይላሉ ። መንገድ ይዞ የሚሄድ ሰው መድረሱ አይቀርም!
መንገዱን ጀምረናል .. ስኬቱ የአሏህ ነው ። ተውፊቅና ሂዳያውን ከእኛ ጋር አድርጎልን ልባችንን ለቁርዓኑ ከፍቶ ፣ አካላችንን ትዕዛዙን ለመተግበር አሳክቶ ጀነትንም የምናገኝ ያድርገን🤲
@tedeburr