ለፋኖ ደሳለው ስጦት ወርቁ የፊታውራሪነት ማዕረግን ስለመስጠት!
የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ቀጠናዊ ትስስር መምሪያ ኃላፊ እና የታቦር ተራራ ብርጌድ ዋና አዛዥ ፋኖ ደሳለው ስጦት ወርቁ ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ/ም ጀብዱ ፈጽሞ መሰዋቱ ይታወቃል::
የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር የሰው ሀብት መምሪያ ኃላፊ እና የታቦር ተራራ ብርጌድ የሰው ሀብት ዘርፍ ኃላፊ ፋኖ አረቡ ታደሰም በዚሁ ዕለት ከፋኖ ደሳለው ስጦት ጎን ተሰልፎ አስገራሚ ተጋድሎ ፈጽሞ ፋኖ ደሳለው በጠላት ጥይት ሲቆስል ለማውጣት ሲሞክር በተተኮሰ ጥይት ተመትተው ሁለቱም ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።
በተድባበ ማርያም ቀጠና ተሮ ሜዳ እና አንበሳ ማደሪያ ላይ የጠላትን አንገት ቆልምመውት ዲሽቃ ለመማረክ እና የጠላት ሰራዊት መቶ አለቃን በእጅ ለመያዝ የጨበጣ ውጊያ ላይ በነበሩበት ቅጽበት በጀግንነት የተሰውት እነዚህ ሁለት ጀግኖች የፈፀሙት የጦር ሜዳ ጀብዱ በልዩ ሁኔታ ለትውልድ እንድተላለፍ ለማድረግ የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር የክብር ማዕረግ ለመስጠት ወስኗል::
በዚህም መሰረት ከዛሬ ታህሳስ 12 ቀን 2012 አመተ ምህረት ጀምሮ ፋኖ ደሳለው ስጦት ወርቁ ፊታውራሪ ደሳለው ስጦት ወርቁ ተብሎ በታሪክ እንድወሳ በሚል ውሳኔ አስተላልፈናል።
ከፊት ለፊት ጠላት ጋር በመጋፈጥ ግንቦት 23 ቀን 2016 አመተ ምህረት ከላላ ከተማ ውስጥ ከአድማ ብተና ብሬን የማረከው ይህ ተአምረኛ ጀግና በአማራ ሳይንት ግምባር ሁለት ጊዜ ታቦር ተራራ ብርጌድ ከጠላት ብሬን ሲማርክም እንደሁልጊዜው ከፊት ተሰልፎ ጀብዱ ፈጽሟል።
ፊታውራሪ ደሳለው ስጦት ከሰራዊቱ ፊት የመገኘትና የመሰለፍ ባህሪ ስላለው ይህን ባህሪውን ገላጭ ሆኖ ስላገኘነው የፊታውራሪነት የክብር ማዕረግ ልንሰጠው ችለናል።
በተጨማሪም ክፍለ ጦራችን ለፋኖ አረቡ ታደሰ የግራዝማችነት ማዕረግ መስጠቱን ለማሳወቅ እንወዳለን።
ከፊታውራሪ ደሳለው ጎን ሆኖ ተአምር በሚባል መልኩ ጠላትን ከተድባበ ማርያም ቀጠና በማባረሩ ሂደት የጎላ አስተዋጽኦ የነበረው ይህ ጀግና ግራዝማች አረቡ ታደሰ ተብሎ እንድጠራ ስናሳውቅ የሚዲያ ባለሙያዎችና የታሪክ ፀሀፊዎች ይህንን ከግምት እንድያስገቡ በማስታወስ ጭምር ነው::
የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር!
ታህሳስ 12/2012 ዓ/ም
https://t.me/andeamharamediahttps://t.me/andeamharamedia