Tesfaab Teshome


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ስነፅሁፍ
ታሪክ
ቀልድ
ፓለቲካዊ ጉዳዮች
ስፖርት
በፅሑፍ እና በድምፅ ተዋሕደው ይቀርብሎታል!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ሰላም ቤተሰቦች ሰሞኑን ስብራት የተሰኘ ተከታታይ ልብወለድ እያቀረብኩላችሁ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ልብ ወለዱ ሚቀጥል ሲሆን ይህ ሲገባደድ ነገ መቼ ነው የተሰኘ ይቀጥላል፡፡ ከርሱ ቀጥሎ ደግሞ ሽሽት ይቀርባል፡፡

እርስዎም በስራዬ ማበረታቻ እንዲሆነኝ ወደ ቻናሉ 5 ሰው እንዲጋብዙልኝ በቅንነትና ቤተሰባዊ ስሜት እጠይቃለሁ፡፡

ይህን እንደምታደርጉ ስለማውቅ አስቀድሜ እያመሰገንኩ ይህን መልእክት ለ5 ወዳጅዎ እንዲልኩልኝ በድጋሚ አሳስባለው፡፡

ለመቀላቀል
👇
@tfanos @tfanos


ስብራት ክፍል አምስት

ሴትነት ላንቺ ምንድነው ብትሉኝ መልሴ "ሴትነት መጨቆን ነው" የሚል ይሆናል፡፡ ሴት ለመጨቆን የተፈጠረች ምስኪን ፍጡር ትመስለኛለች፡፡

የሴትነት የመጀመሪያ ተመስሌቴ እናቴ ናት፡፡ አለም ላይ ከማንም ቀድሜ ያወኩት እርሷን ነው፡፡ የአለምንም መልክ እና ባህሪ ያወኩት በእናቴ በኩል ነው፡፡

አባቴ ለእኔ የትኛውም ወላጅ ሚመኘው አይነት ወላጅ ሚመኘው አይነት ጥሩና አፍቃሪ አባት ነው፡፡ ለእናቴ ደግሞ የሰይጣን ቁራጭ! ጥሩ አባት ቢሆንም ክፉ ባልም ነው፡፡

በልጅነቴ በየለቱ እናቴ ስትነፋረቅ አያታለው፡፡ በየለቱ ታለቅሳለች፡፡ ፊቷን የተመለከተ የተፈራረቀበትን የመከራ ብዛት በቀላሉ ይገነዘባል፡፡ በአባቴ ጭካኔ የተነሳ የተጎሳቆለ ማንነቷን የተመለከተ ሁሉ ማልቀስ ይቃጣዋል፡፡

የሚያስቀያት የጀርባ ህመም መንስኤው ባሏ ነው፡፡ የፊቷ ብልዝ የአባቴ ጉልበተኝነት ማረጋገጫ ማህተም ነው፡፡ ያረጁ ልብሶቿና ጎዶሎ ማጀቷ የስስታምነቱ ውጤት ናቸው፡፡ በራስ መተማመኗን ያጣችውና በሰው ፊት ለመቆም ምትሸማቀቅ የሆነችው በገዘፈ አውሬነቱ የተነሳ ነው::

ይህንን ማን አስተዋለ? እናትና አባቴ ፀባቸው ከፍ ሲል ለመሸምገል ሚመጡ አስታራቂ ተብዬዎች እናቴ መካራውን የመሸከም ግዴታ እንዳለባት በገደምዳሜ ይነግሯታል፡፡ በአባቴ በደል ላይ ከሚፈርዱቱ በላይ እናቴን ባለመታገሷ የተነሳ ሚኮንኗት ብዙ ናቸው፡፡

ይህ ሁሉ የሆነው ሴት ስለሆነች አይደል? በማህበረቡ ያልተፃፈ ህግ መሠረት ሴት ብትጨቆን ጭቆናውን የመሸከም ግዴታ አለባት!!!

ይህ ትዝብቴ ሴትነትን የመጨቆን ምክንያት አድርጌ እንዳስብ አስገድዶኛል፡፡ በልጅነቴ ተምሳሌቴ የነበረችው እናቴ በሴትነቷ የተነሳ የጭቆና ቀንበርን ስትሸከምና ስትሰበር ተመልክቻለሁና በሴትነት መሸማቀቅ ጀመርኩ፡፡ ለረጂም ጊዜ የሴትነት መገለጫዬ በሆኑቱ ጡቶቼና ቂጤ አፍር ነበር፡፡


እንደ ቤተሰብ ረዥሙን ዘመን የኖርነው በአንድ ክፍል የኪራይ ቤት ስለነበር የ12ና 13 አመት ልጅ ሳለው የናትና አባቴን ወሲብ የማየት እድሉ ገጥሞኛል!!

አባቴ ብዙ ጊዜ ከኔጋር መሬት ላይ አንጥፈን ምንተኛ ቢሆንም ሲቀነዝርበት ወደ እናቴ ይሄዳል፡፡ አላማው ወሲብ እንደሆነ ስለማውቅ የተኛው መስዬ በንቃት እከታተላለሁ፡፡ አልጋው ሲያቃስት እኔም መጋል እጀምራለሁ፡፡ ሊኖራቸው የሚችለውን ወሲባዊ ደስታ ሳስብ ሙቀቴ ይጨምራል፡፡ አሳዛኙና አስቂኙ ነገር ግን በነጋታው አባቴ ሰበብ ፈልግ እናቴን ይደበድባታል፡፡

አንድም ቀን እናቴ በር ዘግቶ ከማልቀስ ውጪ ለአባቴ ፀበኛ ባህሪ ተመጣጣኝ ምላሽ ሰታው አታውቅም፡፡ ይህን ሳስተውል ሴትነት መጨቆን ማለት እንደሆነ አመንኩ፡፡

ይህ ሁሉ ቢሆንም አባቴ ለእኔ ልዩ ነበር፡፡ መሬት ላይ አንጥፎ ከእኔ ጋር ሲተኛ የሆነ አይነት ግለት ይሰማኛል፡፡ ለእናቴ ጥሩ ባል ባይሆንም ለኔ ለብቸኛ ልጁ ጥሩ አባት ነውና አፈቅረዋለው፡፡

የሆነ ወቅት ላይ ደግሞ ከአባቴ ጋር ስለመባለግ ማሰበ ጀመርኩ፡፡ ከእናቴ ጋር አልጋ ለይቶ እኔ አጠገብ ሲተኛ ደስ ይለኝ ስለነበር በሃይል አቅፈዋለው፡፡ እንዲነካካኝና እንዲስመኝ እመኛለሁ፡፡

በአፍላነቴ ከአባቴ ጋር መባለግን ያለልክ እመኝ ነበር...

ይቀጥላል

(ተስፋአብ ተሾመ)
ለመቀላቀል
@tfanos
@tfanos


በባምባሲ ወረዳ በጸጥታ አካላትና በህብረተሰቡ መካከል በተፈጠረ ያለመግባባት የሶስት ግለሰቦች ህይወት አለፈ!‼️

በባምባሲ ወረዳ በጸጥታ አካላትና በህብረተሰቡ መካከል በተፈጠረ ያለመግባባት የሶስት ግለሰቦች ህይወት ማለፉን የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ያሲር አብዱልማጅድ እንደገለጹት፥ ችግሩ የተከሰተው የጸጥታ አካላቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የማስተግበር ስራ ላይ እንዳሉ ነው።የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ እንዳስረዱት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተጣለ ወዲህ የፖሊስ አካላት ህብረተሰቡ ተራርቆ ከበሽታው እራሱን እንዲጠብቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፥ ችግሩ በተከሰተበት በመንደር 47፣ 48 ና 46 ቀበሌዎች መካከል የሚገኘው የገበያ ቦታ በሽታው እስኪገታ ድረስ እንዲቆም ከህዝቡ ጋር ውይይት የተደረገ ቢሆንም መልሰው ጠዋት መገበያየቱን እንደቀጠሉበት ተናግረዋል።

ይህንንም ችግሩን ለመፍታት የወረዳው ፖሊስ ተልኮ ሙከራ ቢደረግም ከአቅም በላይ ሆኖ ስለቀጠለ በቀን 26/09/2012 ዓ/ም የወረዳና የአሶሳ ዞን አመራሮች በቦታው ተገኝተው ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።

በውይይቱ ወቅትም ገበያችንን በኮሮና በሽታ ሰበብ ለሶንካ ቀበሌ ሊሰጥብን ነው፤ መሬት የምናርሰው የለንም ይሰጠንና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ተነስተው መግባባት ላይ መደረሱን አስረድተዋል።ይሁንና ውይይት በተደረገበት እለት በብዝሃ ህይወት በተከለለው አንበሳ ጫካ አካባቢ የሚያርሱ ግለሰቦች ቤት እየተቃጠለ ስለሆነ ድረሱልን የሚል በ26/09/2012ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 አካባቢ ጥሪ ሲደርሰን የፖሊስ አካላትን ወደቦታው የላክን ሲሆን ከቁጥጥር ውጭ ሲሆንብንና የፖሊስ አካል ሲመታብን ተጨማሪ ልዩ ኃይል በማከል ለመቆጣጠር እየተሰራ ባለበት ወቅት በተፈጠረ ግብግብ የሶስት ግለሰቦች ህይወት እዳለፈ ተናግረዋል።በዚህም የመንደር 47 እና 48 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ የ3 ሠዎች ህይወት አልፏል።የ3 ሠዎች ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ አዛዡ ገልጸዋል።

©የክልሉ መ/ኮ/ቢሮ
@Tfanos
@tfanos


ስብራት ክፍል አራት

ዛሬ ከሰለሞን ጋር እንዋሰባለን፡፡ ከሶስት ወር በፊት ከሰለሞን ጋር ልንዋሰብ ተቃጥረን የከተማችን ውድ ሆቴል ከፍል ውስጥ ተገናኘንና ለጉድ ተሳሳምን፡፡ ሲስም ጎበዝ ነው፡፡ አስገራሚ ብቃቱ ደግሞ ልብ መስቀልን ይችልበታል፡፡

ከሰለሞን ጋር በግለት ብንሳሳምም አልተዋሰብንም ነበር፡፡ ልንጀምር ስንል ኮንዶም ከኪሱ አወጣ፡፡
ኮንዶም በጣም እጠላለው፡፡ ሰው እንዴት በላስቲክ ያደርጋል? ግለት ውስጥ ያለ ሰው ወደ ገደለው መግባት ሲጠበቅበት በመሃል ኮንዶም ለመቅደድና ለማጥለቅ ሲሞክር........... ኤጭ!

ሰለሞን በኮንዶም ማድረግ እንደማልፈልግ ስነግረው ሊበጣጠስብኝ ፈልጎ የነበረ ቢሆንም ማምረሬ ሲገባው በባዶ ሊያደርግ ተስማማ፡፡ በባዶም አልሰጥህም አልኩት፡፡ በቃ እኔ እንዲህ ነኝ፡፡

በነገራችን ላይ ሰለሞን የአክስቴ ልጅ ባል ነው፡፡ በኔና በአክስቴ ልጅ መካከል የ6 ወር ልዩነት ብቻ ያለ ሲሆን ሁለት ልጆችን ወልዳለች፡፡ ይሄ ነገር ደግሞ ቅናት እንደፈጠረብኝ መዋሸት አልፈልግም፡፡ ራሴን ከርሷ ጋር አነፃፅርና የመጣል ስሜት ይሰማኛል፡፡

ባሏን በወጥመዴ ያስገባሁት ውስጤ ያለውን የመበለጥ ስሜት እንዲሸፍንልኝ በመፈለግ ነው፡፡

ዛሬ ከሰለሞን ጋር እንዋሰባለን!! በርግጥ እርካታን አላገኝ ይሆናል፡፡ ግን እንዋሰበላን፡፡

ይሄን እያሰብኩ ቴሌቪዥን ስጎረጉር ሃይማኖታዊ ቻናል ተደነቀረብኝና ጥቂት ተከታተልኩ፡፡

በቴሌቪዥኑ የአንዲት ሴት ህይወት ይተረካል፡፡ የሴትቱ ገመና ይነገድበታል፡፡ ..... እንባ ተናነቀኝ፡፡

ብዙ የሃይማኖት አባቶች ብሽቆች ናቸው፡፡ የሃጥአንን ንስሃ ይነግዱበታል፡፡ ቁስላቸውን ያተርፉበታል፡፡ ውደቀታቸውን ስብከት ያደርጉታል፡፡

የ18 አመት ልጅ እያለው ለአንድ ሰባኪ ነኝ ባይ ገመናዬን ነገርኩት፡፡ ሰባኪው ከአባቴ ጋር ቅርርብ ያለውና አዘውትሮ ወደ ቤታችን ሚመጣ ሰው ነው፡፡ የአባቴን ሚስጥሮች ያውቃል፡፡ እናቴም እንደጥሩ ወዳጅ ትቆጥረዋለች፡፡ እኔ ግን ገመናዬን የነገርኩት ከቤተሰባችን ጋር ባለው የመቀራረብ ስሜት አይደለም፡፡ ሰባኪ ስለሆነ እንጂ!!!

የሃይማኖት ሰባኪ ሲባል መለሰተኛ እግዚአብሔር አድርጌ ስለማስብ ለሁሉም ችግሮች መፍትሔ ሚያመጣ ይመስለኝ ነበር፡፡ ለሰባኪው ያለሁበትን ሴሰኝነት ላወጣቸው የሞከርኳቸውን ወንዶች ብዛት ራሴን በሬሴ ለማርካት ማደርገውን ጥረት ድንግልናዬን ለአጎቴ ልጅ ማስረከቤን ወዘተ ወዘተ ለሰባኪው ነገርኩት፡፡

ሰባኪው ሲሰማኝ ከቆየ በኋላ ራሴን የሰይጣን ማደሪያ ለማድረግ መፍቀዴን ነገረኝና ልቤን በንግግር ጦር ወጋው፡፡
"....ሰይጣን እኛ ካልፈቀድንለት በስተቀረ በኛ ላይ ስልጣን የለውም፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ ዲያቢሎስን ተቃወሙ ከናንተም ይሸሻል ማለቱን አስታውሺ"
ሰባኪው በለፈለፈ ቁጥር በመናገሬ መፀጸት ጀመርኩ፡፡

ለሰባኪው ገመናዬን በነገርኩት በሶስተኛ ቀን ቤተክርስቲያን ስሄድ መድረክ ላይ ታሪኬን ሲያወራ ሰማሁት፡፡ "....... ወገኖቼ ይህች ልጅ ራሷን የሰይጣን ማደሪያ አድርጋለችና በዚህ ልምምድ ውስጥ ገባች፡፡ ምናልባት በድርጊቷ ጊዜያዊ ደስታ ታገኝበት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ትል እንኳን ወደማይሞትበት እሳቱ ለሰከንድ ወደ ማይጠፋበት ወደ ታላቁ የእሳት ባህር ትጣላለች፡፡ በሃጥያቷ የተነሳ ገሃነብ ትገባለች...."
ህዝቡ ከንፈር ይመጣል፡፡ ትቼ ወጣው፡፡ ላለመመለስ ትቼ ወጣው፡፡ ዳግመኛ የቤተክርስቲያንን ደጅ ላለመርገጥ ምዬ ትቼ ወጣው፡፡

ኑዛዜዬን ነገደው፡፡ ንስሃዬን ሸቀጠው፡፡

አንዳንዴ ገመናችንን የገለጥንላቸው ይሰላቁብናል፡፡ በቁስላችን ዘይት ያፈሱበታል ብለን ያሰብናቸው ሚጥሚጣ ይነሰንሱበታል፡፡ እንጨትም ይሰዱበታል፡፡ ስብራታችንን ይጠግኑታል ያልናቸው የተሰበርንበት ቦታ ላይ ይቀጠቅጡናል፡፡ ንስሃችንን ይነግዱበታል፡፡

ይቀጥላል፡፡
(ተስፋአብ ተሾመ)

ተቀላቀሉ
👇
@tfanos
@tfanos


አስገድዶ ደፋሪን አምስት አመት መቅጣት ምን አይነት ግምድል ፍርድ ነው?




ውሃ

ከሰማይ የመጣ ነው፡፡ ሲዘንብ ያለምክንያት አይደለም፡፡ በረሃውን አረስርሷል፡፡ ምድር ታፈራ ዘንድ አድርጓል፡፡ ረሃብ በጥጋብ እንዲለወጥ ከመሬት ማህፀን ፍሬን አውጥቷል፡፡

መልክና ጣእም የለውም ይሉታል፡፡ ዳሩ ግን በጥም የተነሳ ሊሞቱ ያሉትን ጥም ይቆርጣል፡፡ ያረካቸዋልም፡፡ ቅርፅ አልባ ቢባልም ከትንሽ እስከ ትልቁ ድረስ በሁሉም ውስጥ ያለመገደብ ይገባል፡፡

ያነፃል፡፡ የቆሸሸ ቢኖር ሊያነፃው ዘንድ ጉልበት አለው፡፡ ማንም በእድፋምነቱ የተጨነቀ በመቆሸሹ ያፈረ ቢኖር ውሃው ያነፃል፡፡

ይሸከማል፡፡ ግዙፉ መርከብ ከነግሳንግሱ በላዩ ቢሆን ከበደኝ ሳይል እስከወደቡ ድረስ ይወስደዋል፡፡ መርከቡን ከነምናምኑ ሚሸከም ሃይል!

ደግሞም ጠራርጎ ሚወስድ ጉልበታም ነው፡፡ ደራሽ ሆኖ ሲመጣ ማንም አያስቆመውም፡፡ ሁሉንም ጠራርጎ ይወስድ ዘንድ ጉልበቱ አለው፡፡

ይህ ውሃ ደመናም ይሆናል፡፡ የብርቱ ፀሃይን ጉልበት ሚያሸንፍ ደመና! ሃሩርን መሸሽ ሚፈልጉ በአቅማቸው ምንም ማድረግ ማይችሉ እንኳን በደመናው የተነሳ ከፀሐዩ ንዳድ ይድናሉ፡፡

ውሃው ፍሬን ሊሰጥ ዝናብን ሊያበቅል ከሰማይ ቢመጣም ከምድር ወደ ሰማይም ተመልሷል፡፡ ውሃ ነውና መዝነብን ብቻ ሳይሆን በትነት ወደ ላይ መውጣትንም ያውቅበታል፡፡

(በነፃ የሆነው ውሃ እጅግ ውድ ነው)

ሰማዩን እያየሁት ነው፡፡ ሰማዩ ላይ ዳግመኛ እንደሚዘንብ ምልክትን እየሰጠ ነው፡፡

ዳግመኛ ይዘንባል!!

(ተስፋአብ ተሾመ)

@Tfanos
@tfanos


ስብራት ክፍል ሶስት

የአጎቴ ልጅ በጣቱ ድንግልናዬን ከወሰደው ለቀናት በተዘበራረቀ ስሜት ውስጥ ነበርኩ፡፡ ፀፀት ትንሽነት መናቅ ባለጌነት ተፈራርቀውብኛል፡፡

ከዝብርቅ ስሜቴ በአግባቡ ሳልወጣ ለሁለተኛ ጊዜ ከአጎቴ ልጅ ጋር ባለኩ፡፡

እንደመጀመሪያው ቀን ተላፋኝ፡፡ ጡቶቼን ነካካቸው፡፡ ሳመኝ...... መጋል ስጀምር ጣቱን ወደ ሴትነቴ ሰደደው፡፡ አስቆምኩትና "ከፈለክ ኖርማል የሆነ ሴክስ እናድርግ እንጂ በጣትህ አታድርገኝ" አልኩት፡፡ ፈገግ አለ፡፡ ትርጉሙ ማይገባ ፈገግታ፡፡

እንደ አዲስ መሳሳም ጀመርን፡፡ ትንንሽ ጡቶቼን ጨመቃቸው፡፡ ወደ ውስጤ እንዲገባ እስክመኝ ድረስ ግዬ ነበርና "በናትህ አድርገኝ" አልኩት፡፡

ገና ማድረግ ከመጀመራችን ግን ስሜቴ ትቶኝ ሄደ፡፡ በጣም ያማል፡፡ የተሰነጠኩ ያህል ተሰማኝ፡፡ ስቃዬን በሚያሳብቅ ድምፅ "በናትህ አቁም" አልኩት፡፡ በናትህ እናድርግ እንዳላልኩት በናትህ አቁም አልኩት፡፡ ትንሽዬ ደም የወጣኝ ሲሆን ህመሙ በስለት የመጨቅጨቅ ያህል ነበር፡፡

ከዛን ለት በኋላ በተደጋጋሚ ለመዋሰብ ሞክረን የምናውቅ ቢሆንም ህመሙን አልችለውምና በስቃይ ውስጥ ሆኜ አስቆመዋለው፡፡

እውነት ለመናገር ዛሬም ቢሆን የዛን ሰሞኑን ያህል ባይሆንም ያመኛል፡፡

ደስታን ፍለጋ የጀመርኩት ህይወት ስቃይን መውለዱን ሳስብ እድለ ቢስነት ይሰማኛል፡፡ ለሌሎች የእርካታ ምንጭ የሆነው ህይወት ለእኔ የህመም ምንጭ መሆኑን በቀላሉ መቀበል አልችልምና የተሻለ ነገር ባገኝ ብዬ እየደጋገምኩ እሞክራለሁ፡፡

ሙከራው በህይወት ነው የሚደረገው፡፡ ህይወትን እንደ ቤተ ሙከራ ከማድረግ ሚበልጥ ምን መጥፎ ነገር አለ?
በህይወት መሞከር ቀሚስ ለመግዛት ለክቶ ሳይበቃ ቢቀር የመተው ጉዳይ አይደለም፡፡ እኔ ግን ከዛ በታች አቀለልኩት፡፡ በህይወት ሞክሮ መክሸፍ የሆነ ምርምር አድርጎ መክሸፍ ማለት አይደለም፡፡ በአንዲት የህይወት ሙከራ የሳተ ቁስልን ያተርፋል፡፡ ደጋግሞ የሳተ ደግሞ ደጋግሞ ይቆስላል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ለቁስላችን መድሃኒት ይሆናል ያልነው ሌላ ህመምን ይፈጥርብን ይሆናልና በህይወት መሞከር ከባድ ነው፡፡ አለሞመክርም ደግሞ ከባድ ነው፡፡

በህይወቴ ደጋግሜ ሞክሬያለው፡፡ እርካታ ለማግኘት እኔም እንደሴቶቹ ደስታኛ ለመሆን ደጋግሜ ሞክሬያለሁ፡፡

ደስታ ፍለጋዬ ህመምን ወልዶብኛል፡፡ የእርካታ መሻቴ ቁስልን አትርፎልኛል፡፡ ከሌሎች ሴቶች እኩል መሆንን ተመኝቼ ከሁሉም በታች ሆኛለሁ፡፡

አንድ ለት ከአጎቴ ልጅ ጋር ለመዋሰብ ሞክረን እንደተለመደው አሞኝ "በናትህ አቁም" አልኩትና እየተነጫነጨ ተወኝ፡፡ አለቀስኩ፡፡ ማልረባ ሴት እንደሆንኩኝ ተሰማኝና አለቀስኩ፡፡ እንደህፃን ተነፋረኩ፡፡

"ምናልባት ያንቺ ችግር መገረዝሽ ይመስለኛል" አለኝ እንደዋዛ፡፡
"አለም ላይ የተገረዝኩት እኔ ብቻ ነኝ?"
"አለም ላይ ያሉቱ ሁሉ ሁሉ ምን እንደሚሰማቸው አናውቅም፡፡ ደግሞ አንዱ ላይ የከፋ ችግር ያላመጣው ሌላው ላይ ችግር አያመጣም ማለት አይደለም"
**** *
ያጎቴ ልጅ ያስገረዙኝ አያቶቼ ላይ ያሴረባቸው መስሎ ተሰሜኝና ተናደድኩ፡፡ በለጋ እድሜዬ ወሲብ ያስጀመረኝ እርሱ ሆኖ ሳለ ጥፋቱን ወደሌላው ለማላከክ የሚጥር መስሎ ተሰማኝ፡፡

ምክኒያቱ ምንም ሆነ ምን ዛሬም ድረስ በወሲብ መርካት አልችልም፡፡

በወሲብ ካለመርካት ሚበልጠሸ ስቃይ እንደሌለ እወራረዳለሁ፡፡

ይቀጥላል፡፡
(ተስፋአብ ተሾመ)

@tfanos
@tfanos


ተቃርኖ

ግዙፉ ጎሊያድ በጠጠር መመታት
ስለተሸነፈ
የውድቀት ታሪኩ መፅሃፍ ላይ ተፃፈ

አንዳንድ ያልታደሉ ከነገድሎቻቸው
ፈፅሞ ሲረሱ
ሌሎች ይኖራሉ በመሸነፍ ታሪክ
ዘውትር ሲታወሱ፡፡

#አጭሬ
(ተስፋአብ ተሾመ)

@tfanos
@tfanos


“ከኮሮና ቫይረስ መከሰት በኃላ በ2 ወራት ውስጥ በአባቶቻቸው ጭምር 101 ህፃናት ተደፍረዋል”- ወ/ሮ አልማዝ አብርሃም የአ/አ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ


ስብራት ክፍል ሁለት

የምሽቱን የመዋሰብ ቀጠሮዬን እዬሰብኩ ካፌ ገብቼ ማኪያቶ አዘዝኩ፡፡ ማታ ማታ ማታ የወሲብ ቀጠሮ ሲኖረኝ ቀኑን ሙሉ ማሳልፈው የሚኖረኝን ምሽት እያሰብኩ ምራቄን በመዋጥ ነው፡፡

ዛሬም እንደልማዴ ካፌ ገብቼ ማኪያቶ አዘዝኩና የምሽቱን ሁኔታ በአእምርዬ መሳል ጀመርኩ፡፡ ስንላፋ ስንሳሳም ስንተሻሽ ስንዋሰብ............
ማሰቡ ሚፈጥርብኝ የሆነ አይነት ግለት አለ፡፡

ማኪያቶ እስኪቀርብ ድረስ ጠረጳዛው ላይ ካለው የስኳር ማስቀመጫ ላይ ስኳር መቃም ጀመርኩ፡፡

ልክ እንደ ህፃን ጣፋጭ ነገር እወዳለሁ፡፡ መሞቻሽ ጣፋጭ ነው ቢሉኝ እንኳን ለጣፋጭ ያለኝ ፍቅር እንደማይጎድል እወራረዳለሁ፡፡

ማኪያቶው እስኪርብ ድረስ ከፊቴ ያለውን ስኳር እየቃምኩ ወደ ትላንትናዬ ተጓዝኩ፡፡

ገና 15 አመት እንኳን በቅጡ ሳይሞላኝ ነበር መባለግን የተለማመድኩት፡፡ አንድ ለት ቢያንስ በ5 አመት የሚበልጠኝ የአጎቴ ልጅ በልፍያ አሳቦ ጡቶቼን ይነካካቸው ጀመር፡፡ ዝም አልኩት፡፡ ጨመቃቸው፡፡ አሁንም ዝም አልኩት፡፡ ወደ ከንፈሬ ተንደረደረ ከንፈሩን ጎረስኩት፡፡

ገና መብቀል የጀመሩትን ትንንሽ መፍረጥ እስኪቀራቸው ድረስ መጨማመቅ ሲጀምር ምይዘውን ምጨብጠውን አጣው፡፡

ሠውነቴ እሳት መትፋት ቀርቶታል፡፡ የርሱም ሰውነት እንደኔው ሰውነት ግሏል፡፡ የለበስኩትን ቲ ሸርት ከፍ ሊያደርግ ሲሞክር ተባበርኩት፡፡

በቁጥጥሩ ስር መሆኔን ያወቀው የአጎቴ ልጅ እንደ እናቱ ጡት ሁሉ የኔም ጡቶች ይጠባቸው ጀመር፡፡
አበድኩለት፡፡ ቀባጠርኩ፡፡ አለሜን ሳትኩ...........

መረስ የጀመረ ፓንቴን ሲያወልቅ እንኳን አላስታወስም ነበር፡፡ በጣቱ ወደ ሴትነት ጓዳዬ ገባ፡፡

ከዛስ?...... ደስታዬ ህመምን ማስከተል ጀመረ፡፡ መጀመሪያ አከባቢ ደስ ሚል አይነት ህመም ነበር፡፡ ቀጥሎ ግን ከደስታ ወደ ጭንቀት ተሸጋገርኩ፡፡ በህመም ስሜት ሳለው ፈሳሽ ሲወጣኝ ታወቀኝ፡፡ የአጎቴ ልጅ ድንግልናዬን በጣቱ ወሰደው፡፡
** *

"ይቅርታ ማሽን በመቀዝቀዙ ነው የቆየሁት" አለችኝ አስተናጋጇ ያዘዝኳትን ማኪያቶ ጠረጴዛው ላይ እያስቀመጠች፡፡

ከ10 አመት የኀሊት ጉዞዬ የመለሰችኝ አስተናጋጅ የታደለ መቀመጫ አላት፡፡ "ይሄኔ በብዙ ወንዶች ትወሰብ ይሆናል" አልኩ በልቤ፡፡

በወሲብ ህይወቷ እርካታን ታገኛለች ብዬ ማሰቤ የፈጠረብኝ ቅናት እያስፈገገኝ ማኪያቶዬን ቀመስኩት፡፡ ይመራል፡፡ ሁለት ማንኪያ ስኳር ጨምሬ ሞከርኩት ያው ነው፡፡ ስኳር ደገምኩ አልተሻሻለም፡፡ ለአራተኛ ጊዜ ስኳር ጨምሬ ሞከርኩት አልጣፍጥሽ አለኝ፡፡ እየተበሳጨው ድጋሚ ሞከርኩት አሁንም አይጣፍጥም፡፡

አስናጋጇን ጠራዋትና "ስኳር ብላችሁ ነጭ አፈር ነው እንዴ የሰጣችሁን?" አልኳት፡፡ በግርታ አየችኝ፡፡ "ማኪያቶውን ቅመሺው" አልኳት፡ ግራ መጋባቷ የጨመረ መሠለ፡፡
እንድትቀምሰው አግባባዋትና ቀምሳው ፈገገች፡፡
"በጣም ስኳር በዝቶበታል እኮ" አለችኝ፡፡
ቀመስኩት፡፡ ግን ቅድም ስቀምሰው እንደነበረው ነው፡፡
"ታዲያ እን ለምን አልጣፈጠኝም?"
"አንቺ ማኪያቶ ከመቅረቡ በፊት ብዙ ስኳር መቃምሽ ነው እንዳይጣፍጥሽ ያደርገው፡፡" አለችኝና ሄደች፡፡

"ማኪያቶ ከመቅረቡ በፊት ስኳር ስለቃምኩ ማኪያቶው አልጣፍጥ አለኝ" የአስተናጋጇን ንግግር ለራሴ ደገምኩት፡፡

አንዳንድ ጊዜ መፍጠን ክፉ ነው መሠለኝ፡፡ አንዳንዴ መቸኮል ከማርፈድ በላይ ዋጋ ያስከፍላል፡፡
ስኳሩን ቀድሜ ባልቀምሰው ኖሮ ማኪያቶው ጣእም አልባ አይሆንም ነበር፡፡ መፈላሰፍ ቃጣኝ፡፡

ስለ መፍጠንና መዘግየት ብዙ አሰብኩ፡፡

ከልጅነት እድሜዬ ብዙውን በቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ስላሳለፍኩ ስለ ኢየሱስ ብዙ ሰምቻለሁ፡፡ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ልይዙትና ሊገሉት ሲመጡ ይሰወርባቸው ነበር፡፡ ለምን? ሊሞት አይደለም የመጣው? መሞቱ የግድ እንደሆነ እያወቀ ከገዳዮቹ ፊት ለምን ተሰወረ?

የኢየሱስ ሽሽት ምክንያት ጊዜ ነው፡፡ ያለ ጊዜ ቢሞት መለኮታዊ አጀንዳ ይናጋል፡፡

ለኢየሱስ በጊዜ ውስጥ ማለፍ ዋጋ ነበረው፡፡

አንዳንዴ መቅደም ከመዘግየት እኪል አደገኛ ሊሆን ይችላል፡፡

ስፈላሰፍ ማኪያቶው ቀዝቅዞ ነበርና በአንድ ትንፋሽ ጨለጥኩት.......

ከማኪያቶ መጠጫው ቂጥ ያልተማሰለ ብዙ ስኳር አለ........


ይቀጥላል፡፡
(ተስፋአብ ተሾመ)

ይቀላቀሉ፡፡
👇
@Tfanos
@tfanos


አንዳንድ ቦቆሎ ከጤፍ ማህፀን ዱቄት ሚገኝ አይመስለውም፡፡

(በመጠን የማሰብ ልክፍት)

@Tfanos
@tfanos


ስብራት

በወሲብ መርካት ካለመቻል ሚበልጥ ስቃይ የለም፡፡

በየለቱ ራሴን በራሴ ለማርካት እሞክራለሁ፡፡ ዳሩ ግን እርካታዬ የጠዋት ጤዛ ነው፡፡ ደስታዬ አርቴፊሻል ነውና ከቅፅበታት በኋላ ትቶኝ ይሄዳል፡፡

ወሲባዊ ፊልሞችን ለብቻዬ እመለከታለሁ፡፡ የፊልሞቹ ሱሰኛ ነኝና በየለቱ ወሲባዊ ፊልሞችን ከኢንተርኔት አወርጄ ሲመሽ የክራይ ቤቴን በር ዘግቼ ማየት እጀምራለሁ፡፡

የወሲብ ፊልሞቹን ሳይ ሙሉ ለሙሉ እርቃን ሆኜ ነው፡፡
በየመሃሉ ጡቶቼን በስሜት ተሞልቼ እጨሜቃለሁ፡፡ ከዛም እምብርቴን ቀጥሎም ብልቴን በስሜት እፈትጋለሁ፡፡
በስሜት ተሞልቼ እስክረጥብ ድረስ ብልቴን እፈትጋለሁ፡፡ ይህን በየለቱ አደርገዋለሁ፡፡
* **

በዚህ ልምምድ ውስጥ ከገባው 10 አመት ያልፈኛል፡፡ ልምምዴን ስለማልወደው ልተወው ብፈልግም አይሰምርልኝም፡፡ ሌላው ቢቀር ደህና ወሲብ ስለማድረግ በየለቱ ብመኝም ሰምሮልኝ አያውቅም፡፡

የትኛውንም ወንድ ጠልፌ መጣል ምችል ውብ እንደሆንኩ አውቃለሁ፡፡ በዛ ላይ ደግሞ የወንዶችን ደካማ ጎን ስለማውቅ እንደውሻ እንዲከተሉኝ አደርጋለሁ፡፡
እውነት ለመናገር አንዲት ሴት በወንድ ለመፈለግ ሴት መሆን ብቻውን በቂዋ ነው፡፡ ውብ ከሆነች ደግሞ ወንድን ባሪያዋ ለማድረግ እድሉ አላት፡፡ ውበቷ ላይ ጥቂት ብልሃትን ከጨመረችበት ደግሞ ሴት አምላክ ትሆናለች፡፡
ከልምዴ እንደማውቀው ብዙ ወንዶች ሳይታወቃቸው ሴቶችን ማምላክ ጀምረዋል፡፡ እኔ ለመመለክ ባልታደል እንኳን በቀላሉ ወንዶች ሎሌ እንዲሆኑኝ ማድረግ ምችል ውብ ነኝ፡፡

ከብዙ ወንዶች ጋር በጋለ ስሜት ተሳስሜ አውቃለሁ፡፡ ከንፈሬ ሲጎረስ የጡቴ ጫፍ ሲሳም ጭኖቼ ስር ጣቶች ሲተራመሱ በስሜት እግልና ከመች መች እንደምዋሰብ ማሰብ እጀምራለሁ፡፡ አሳዛኙ ነገር ግን የወንድ ልጅ ብልት ገና ብልቴን ሲነካው ያ ግለቴ ገደል ይገባል፡፡

ትላንት ደግሞ ከመንደራችን ቁጥር አንድ ሴት አውል ጋር ደስ በሚል ሁኔታ ስንሳሳም ቆይተን ከጋልኩ በኋላ በሴኮንዶች ስሜቴ ተነነ፡፡

በስሜት ጫፍ ውስጥ ሳለን ጭኖቼ ስር ገባና ይልሰኝ ጀመር፡፡ የማህፀኔን ከንፈሮች መሳም ከመጀመሩ ሽምቀቅ አልኩ፡፡
ደካማ ሴት እንስራ ተሸክማ አቀበት ስትወጣ ሸክሙ ከብዷት ፈሷ ቢያመልጣትና ይህን ክስተት ሰዎች ቢያዩባት ሚሰማት መሸማቀቅ ተሰማኝ፡፡ ስሜቴ በቅፅበት ገደል ገባ፡፡

የውሸት በስሜት ግለት ውስጥ ያለው ለማስመሰል ሞከርኩ፡፡ መዋሰብ ስንጀምር ከእርካታ ይልቅ ህመም ከደስታ ይልቅ ስቃይ ይሰማኝ ነበርና አቃሰትኩ፡፡

ነገር ግን ማቃሰቴን በስሜት ከፍታ ውስጥ እንደመገኘት ቆጠረው፡፡ ህመሜን እንደ እርካታ አሰበውና ይበልጥ ያሳምመኝ ገባ፡፡

"ስንቱ ነው ህመምና ደስታችን የሚምታታበት? የእርካታና የሃዘን እንባችንን ሚለው ማን ነው?"

ይቀጥላል
(ተስፋአብ ተሾመ)

ተቀላቀሉ
👇
@tfanos
@tfanos


አለት

በደካማ በትር በተመታ ጊዜ
ምንጭ ውሃ የሚያፈልቅ
ብርቱ ነኝ የሚለው በተጋጨው ጊዜ
ፈፅሞ የሚያደቅ፡፡

#አጭሬ
(ተስፋአብ ተሾመ)

@Tfanos
@tfanos


የመፅሐፍ ጥቆማ ቻሌንጅ

ወዳጄ #ተስፋ አባተ (ትሁቱ) በፌስቡክ የወደድኩትን አንድ መፅሐፍ እንድጠቁም አደራ ባለኝ መሠረት የዮሴፍ ቢ ስራ የሆነውን የአፍሪካ ፍልስፍና የተሰኘ መፅሐፍ ልጠቁም ወደድኩ፡፡

ይህ የፍልስፍና መፅሐፍ በህይወቴ ከወደድኳቸው ጥቂት መፅሐፍት መካከል ሲሆን የአፍሪካዊያንን የፍልስፍና መሠረት ታሪክን አጠቅሶ ይመረምራል፡፡

አፍሪካዊያን ስነልቦናችን ምንድነው? ከሌላው አለም ሚለየን አስተሳሰብ የትኛው ነው? ከኛ ጋር ሚገጥምና ሚያሳድገን ምንን መሠረት ያደረገ ርእዮተ አለም ነው? ሚያጠፋንስ ምን አይነት ርእዮተ አለም ነው?

እኒህንና ሌሎችን መሠረታዊ ጥያቄዎችን ዮሴፍ ቢ በፍልስፍና መነፅር ለመቃኘት ሞክሯል፡፡

አንብቡት ታተርፉበታላቹ፡፡

@Tfanos
@tfanos


መሪር ሐቅ

ዘመናት ሳታክት ከደከምከው በላይ
ማምሻውን የከወንከው ሽራፊ ስህተትህ
ጎልቶ ነው የሚታይ፡፡

ዘመንህን በሞላ እልፍ ጊዜ ወድቀ
አእላፍ ጊዜ ረክሰ
በመቋጫህ ዘመን እግሮችህ ከፀኑ
እንባህ ከታበሰ
የቀደመው መድከም መዛል ተዘንግቶ
የፍፃሜህ ድልህ ጎልቶ ይዘመራል
ውድቅትህ ተረስቶ!!!!

(ተስፋአብ ተሾመ)

@tfanos
@tfanos


በሱዳን ጦር እና ኢትዮጵያ ታጣቂዎች መካከል “አልቃድሪፍ” አካባቢ ከባድ ጦርነት መጀመሩን ሮይተርስ ዘገበ!!
****
ባለፉት 3 ቀናት በሱዳን ጦር እና ኢትዮጵያ ታጣቂዎች መካከል ድንበር ላይ ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀነራል አሚር መሃመድ አል ሃሰን አስታወቁ።ቃል አቀባዩ ይህን የተናገሩት በሃገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ነው።
ለታጣቂዎቹ የኢትዮጵያ ጦር ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።በዚህም ውጊያ አንድ የሱዳን ጦር መኮንን ጨምሮ በርካታ ወታደሮች መገደላቸው እና መቁሰላቸው ታውቋል።
ውጊያው እየተካሄደ ያለው አልቃድሪፍ ተብሎ በሚጠራው ድንበራማ አካባቢ ነው።አካባቢው ከዚህ ቀደም በእርሻ ቦታ ምክንያት ተደጋጋሚ ግጭቶች ይስተዋሉበታል።

@Tfanos
@tfanos


"ከታሪኩ ማይማር ህዝብ ስህተቱን እንደ እንስሳ ሲደጋግም ይኖራል"

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

@tfanos
@tfanos


ደራሲ መለስ ዘናዊ

ሰውዬው ከፖለቲከኛነቱ በተጨማሪ ደራሲ ነበር፡፡ግር የመል ቢሆንም መለስ ዜናዊ የልብ ወለድ ደራሲም ጭምር ሲሆን ሁለት የልብ ወለድ መፅሐፍት አሳትሟል፡፡

መፅሐፍቶቹ "ገነቲና እና መንኳኳት ያልተለው በር" ሲሰኙ ተስፋዬ የኀላሸት በሚል የብእር ስም ነው ለህትመት የበቁት፡፡
(እዚህ ጋር ሰውዬው ስም የመለወጥ ውቃቢ አለበት ይሆን ብሎ ሚጠይቅ ተሳሳተ አይባልም:: ከቤተሰብ የወረሰው የመጀመሪያ ስሙ ለገሰ እንደሆነ ቢታወቅም በፖለቲካው አለም መለስ በስነጽሁፉ ደግሞ ተስፋዬ ሚሉ ስሞችን ተጠቅሟል፡፡)

ሰውዬው ጋዜጠኛም ሆኖ ያውቃል፡፡ የአዲስ ራእይ መፅሔት ዋና አዘጋጅ በነበረበት ወቅት ታደሰ ገብረወልድ የሚል ስምን ተጠቅሟል፡፡ (ስም የመለወጥ ልክፍት!!)

መለስ ዜናዊ (ስም ለዋዋጩ) እጅግ ትጉ አንባቢ እንደሆነና ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ተኮር መፅሐፍት እንደማያመልጡት ይነገራል፡፡ (ልብ ወለድ ደራሲ እንደመሆኑ ልብ ወለዶችን ያነብ ይሆን?)

ሰውዬው ስም የመለወጥ ልክፍት ስላለበት ጠቅላይ ሚኒስቴር ከሆነ በኋላ በሌላ የብእር ስም ልብወለዶች አሳትሞ ቢሆንስ? (የደራሲነት ውቃቤ በቀላሉ አይለቅማ!!)

ከላይ እንዳነሳነው ከሁለቱ የመለስ ዜናዊ መፅሐፍት መካከል አንዱ "መንኳኳት ያልተለየው በር" ይሰኛል፡፡ ርእሱ ሳቢ ነው፡፡ ሚንኳኳ ግን ያልተከፈተ በር.......
-******** **

መለስ ዜናዊ በፖለቲካው መድረክም ደራሲ ነበር፡፡ በድርሰቱም በርካታ ገፀ ባህሪያትን ፈጥሯል፡፡

(ተስፋአብ ተሾመ)

@Tfanos
@tfanos



Показано 20 последних публикаций.

812

подписчиков
Статистика канала