ስፈልግህ ፈለኩህ እልሀለሁ... ስትናፍቀኝም ናፍቆቴን ከመግለፅ ወደኋላ አልልም። "ይኮራ ይሆን" የሚለው አያሳስበኝም... በመፈቀርህ ከታበይክ እሱ ያንተ ትንሽነት ነው። ዛሬም እንደትላንቱ እልሀለሁ "በኛ ግንኙነት ውስጥ የኔ ስራ አንተን ማመንና ማፍቀር ነው"
ካልታመንክልኝ እኔ አልቀጣህም... የእምነቴን ልክ ስለምታውቀው ህሊናህ ይቅጣህ። ከዳኞች ሁሉ ትልቁ ዳኛ እሱ ነውና ከእስርቤትም አሰቃቂው የህሊና እስር ቤት ነው።
ብጠይቅህ የምትመልስልኝን መልስ አስቤ እፈራና ደግሜ ዝምምም እላለሁ... ይገባኛል ባንተ ህይወት ውስጥ ትልቅ ሚስጥር እንዳለ ግን ያን ለመሸከም ዝግጁ አይደለሁም አንተ ለመናገር እንዳልተዘጋጀኸው ሁሉ ...
አንድ ነገር ግን አውቃለሁ ባንተ ልክ ማንንም አፍቅሬ እንደማላውቅ።
አንተ ከመምጣትህ በፊት እኮ ህመሜን ሁሉ እወደው ነበር... እየንዳንዱ ህመም ወደ ሞት እያንደረደረ እየወሰደኝ እንዳለ ሲሰማኝ፣ ሰዎች ምፅፅ ብለው ከንፈራቸውን ሲመጡልኝ፣ "ይቺ አለች ብላችሁ ነው" እያሉ እርስ በርሳቸው ሲንሾካሾኩ እርካታ ይሰማኝ ነበር። ልሞት ነዋ... ልገላገል... አንተ ከመጣህ በኋላ ግን መኖር አጓጓኝ ህመሜንም ጠላሁት
አሁን ደህና ነኝ በመውደድህ መዓዛ አጥነህ በፍቅርህ አክመህኛል።
ባንተ እርግጠኛ ብሆን... ሁሌም የኔ ብቻ እንደሆንክ ቢሰማኝ ደግሞ የበለጠ ደህና እሆናለሁ።
-------❤-------
@tigiwaaa