💞እህቴ ሆይ ንቂ💞!!
ፈገግታ እያበዛ በአስመሳዩ ጥርሱ
ወደድኩሽ እያለ በቅቤ ምላሱ
ፍቅሩን ሲገልፅልሽ ቃላትን ቀምሞ
እመኚኝ እያለ ሲነግርሽ ደጋግሞ
እንዳትሸወጂ ብልጥ ሁኚ አደራ
ፍቅርን አይገልፀውም የቃላት ድርደራ
ያንች ያልሆነን ሰው ፍፁም አታፍቅሪ
በሀሳብ መንምነሽ ከንቱ እንዳትቀሪ
ከኔ አያልፍም ብለሽ ምኑንም ሳታውቂ
የፍቅር አባዜ ጠልፎሽ እንዳትወድቂ
ደግሜ ልንገርሽ እህቴ ሆይ ንቂ
ከእንድህ አይነት ነገር በጭራሽ ራቂ
ለምኑም ለሁሉም አትጨናነቂ
አላህ ባለ ግዜ ይሆናል እወቂ
ያንን ቀን በተስፋ ከጌታሽ ጠብቂ!!!
💧💧💧💧💧💧💧💧💧
👇👇👇 join &share
@umuhilal1
ፈገግታ እያበዛ በአስመሳዩ ጥርሱ
ወደድኩሽ እያለ በቅቤ ምላሱ
ፍቅሩን ሲገልፅልሽ ቃላትን ቀምሞ
እመኚኝ እያለ ሲነግርሽ ደጋግሞ
እንዳትሸወጂ ብልጥ ሁኚ አደራ
ፍቅርን አይገልፀውም የቃላት ድርደራ
ያንች ያልሆነን ሰው ፍፁም አታፍቅሪ
በሀሳብ መንምነሽ ከንቱ እንዳትቀሪ
ከኔ አያልፍም ብለሽ ምኑንም ሳታውቂ
የፍቅር አባዜ ጠልፎሽ እንዳትወድቂ
ደግሜ ልንገርሽ እህቴ ሆይ ንቂ
ከእንድህ አይነት ነገር በጭራሽ ራቂ
ለምኑም ለሁሉም አትጨናነቂ
አላህ ባለ ግዜ ይሆናል እወቂ
ያንን ቀን በተስፋ ከጌታሽ ጠብቂ!!!
💧💧💧💧💧💧💧💧💧
👇👇👇 join &share
@umuhilal1