#ሰካራሙ_ክፍል_፱{9}
#ቅድስት ቤት ስትገባ ከልጁ ጋር አብረን እየደነሰን ነበረ እሷም በተራዋ እንደኔ ቁጭ ብላ እኛን ማየት ጀመረች
እኔም በልቤ አንቺም በኔ ቦታ ሆናሽ የኔን ህመም ታመሚ ብዬ ከልጁ ጋር
የበለጠ መተሻሸት ጀመርኩ በቅድስት አይን ላይ የቅናት መንፈስ ይታይበታል
እንግዲህ ምንም ማድረግ አይቻልም በዛ ላይ ቅድስት ወንዶችን አብረው
ለመተኛት ብቻ ነው እንጅ ለፍቅር አትፈልግም ስለዚህ ስለ ስሜቷ ብዙም
አለሰብኩም መቼም ከኔ በላይ አትጎዳም ብዬ ዝም አልኩኝ
ግን የሚወዱት ሰው የሌላ ሆኖ ማየት በጣም ከባድ ነው
በዚህ አለም ላይ ብዙ ነገሮችን ለሌላ ሰው አሰልፎ መስጠት ይቻላል የሚወዱትን
ሰው ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠት ግን ከባድ ብቻ ሳይሆን የማይቻል ነገርም ነው
በእኔ እና በጓደኞቼ መካከል ብዙ ልዩነት መኖሩን ገና አሁን ነው እየተረዳሁ
የመጣውት እኔና ጓደኞቼ የተለያየ ባህርይ ያለን አንዱ የአንዱን እቅድ ችግር
ህመም መረዳት የማይችል በደስታ ብቻ አብረን የምንኖር ጓደኛሞች ነን
ታዲያ እንደዚህ አይነት ጓደኝነት በጣም መጥፎ አይደለም? ነው እንጅ
ጓደኝነት ማለት ለካ አንዱ የአንዱን ችግር መቀበል አንዱ ለአንዱ መስዋዕት መሆን
አንዱ ለአንዱ ማሰብ ምንም አይነት ምስጢር አለመደባበቅ ነው
እኔ መጀመሪያ ስሜቴን ለቅድስት ተናግሬ ቢሆን ምናልባት ለልጁ ያላት አመለካከት
ሌላ ይሆን ነበረ አሁን ግን እኔም ለሷ ጠላት እሷም ለኔ ጠላት ለመሆን ተቃርባናል
በዚህ መልኩ የልደት ቀኔ አለፈ በጣም ደስተኛ የሆንኩበት ቀንም ነበረ ነገር ግን
አሁንም ልቤ ውስጥ ብዙ አይነት ጥያቄዎች አሉ
አንዱ እንዳፈቀርኩት ለልጁ መናገር አለብኝ ነው ወይስ ምናልባት ተናግሬ ፍጽሞ
ከሚርቀኝ መታገስ አለብኝ የሚል ነው
ሌላው ደግሞ ለቅድስት ልጁን እንደምወደው መናገር አለብኝ ወይስ በሂደት
ሁሉንም ነገር እራሷ ትወቅ የሚሉት ናቸው
አያችሁ የእኛ የብዙ ሰዎች ችግር ይሄ ነው እኔ አሁን ስሜቴን መደበቅ ምንም
ትርጉም የለውም እንደውም ልጁ ሌላ ህይወት እንዲጀምር በር መክፈት እኮ ነው
ስለዚህ ስሜቴን መንገር እንደለብኝ ተረዳሁ
የውስጤን ለመናገር ወሰንኩኝ
ሰክሮ ሲመጣ የተለመደው ቦታ አብረን መቀመጣችን አይቀርም ስለዚህ ዛሬ ማታ
እነግረዋለሁ ብዬ ዝም አልኩኝ
ቀን እቤት ውስጥ ብቻዬን ቁጭ ብዬ እያለሁ ቅድስት ለብቻዋ መጣች
እንዴት ነሽ አልኩኝ ደህና ነኝ ስትል
ታዲያ ምነው ዛሬ ለብቻሽ አልኳት
በእናትሽ በጣም ጭንቅ ብሎኛል አለች
ምን ሆነሽ አልኳት
ጥሩ ስሜት ላይ አይደለሁም ማታ ለልጁ እንደምወደው ነግሬ እኔ ፍቅረኛ አለኝ
አዝናለሁ አለኝ ብለ አለቀሰች
ምን??
እንዴት?
አንቺ ከመቼ ወዲ ነው ወንዶችን ለፍቅር መቅረብ የጀመርሽው አልኳት
ባክሽ እኔ መጀመሪያውኑ ማፍቀርን ጠልቼ ሳይሆን የምወደዉን ወንድ አጥቼ ነበረ እንደዛ እሆን የነበረው
አሁን ገና ወንድ አገኘሁ ብዬ ደስ ብሎኝ ነበረ አሁን እሱም የሌላ ሁኗል አለችኝ
እባክሽን አንድ ነገር አድርጊልኝ እኔ በቃ አልቻልኩም ማበዴ ነው ስትል
በልቤ ውይይይይይ እኔን ብሎ መፍትሔ ፈላጊ እኔ ለራሴ ማበዴ ነው አልኩና
ይቅርታ ቅድስት በዚህ ጉዳይ መግባት አልፈልግም አልኳት
እንዴ ለምን? ቆይ ጓደኛዬ አይደለሽም እንዴ?
አዎ ነኝ ግን በቃ አልችልም የልጁ ፀባይ በጣም ከባድ ነው ባይሆን አንቺ እራስሽ
ሞክሪ አልኳት
አያችሁ አይደል? ድብቅ መሆኔ ምን አይነት ችግር ውስጥ እንዳስገባኝ
ለማታ የያዝኩት እቅድ አሁኑኑ ተዉኩት
ልቤ ማቅ ለበሰ
አይኖቼ በእምባ ተሞሉ
አይምሮዬ ተረበሸ
ልቤ ከመጠን በላይ ደሙን መርጨት ጀመረ
የእኔ እንደምወደዉ መንገር
በፍጹም አስፈላጊ አይደለም ተስፍ የሌላት ሴት ሆንኩኝ
ማታ አከባቢ ልጁ እንደለመደው ሰክሮ መጣ
.
ይቀጥላል
http://t.me/USA2A