Positive Mind for success


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


@lozita29

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций














የሰው ልጅ የሚያገኘው የስራውን ሳይሆን የእምነቱን ነው። እምነት ሽርፍራፊ የለውም። የእምነት 99.999% የለም። ማመን በመሉ ልብ ነው። አንድን ነገር በጥርጣሬ ከማድረግ ጨርሶ መተው የተሻለ ነው ፤ ከንቱ ድካም ይሆናልና። ትንሽዬ ጥርጣሬ ትልቁን ስራችንን ስለምታበላሽ የምንሰራውን ሁሉ በእምነት እንስራ። ስንዘራ በእምነት እንዝራ ፤ ያን ጊዜ ብዙ እጥፍ ማጨድ እንችላለን!


የሕይወት ዘይቤ ምርጫ

“የወደፊት ሕይወትህ ምስጢር በየእለቱ በምትለማመዳቸው ልማዶችህ ውስጥ ተደብቀው ይገኛሉ” – Mike Murdock

የየዕለት የሕይወት ዘይቤ ምርጫ ለቀሩት ዋና ዋና ምርጫዎችህ መጋቢና ገባር ስለሆነ በሚገባ ልታስብበት ይገባል፡፡ የየዕለት ውሳኔዎችህ የሕይወትህን ዋና ዋና ምርጫዎች ወይ ያፈርሳሉ ወይም ደግሞ ይገነባሉ፡፡
ለየዕለቱ ገጠመኞች የምንሰጣቸው ምላሾችና ከሰዎችና እንዲሁም ከሁኔታዎች ጋር ያሉን አቀራረቦች ለዋና ዓላማዎቻችንና ምርጫዎችን እንደገባር ወንዞች ናቸው፡፡ በየእለቱ ወደ እኛ የመጣውን ነገር መቆጣጠር ባንችልም ወደየት አቅጣጫ እንደምንወስደው ግን መምረጥና መወሰን እንችላለን፡፡

ወስነን ለመከተል ለመረጥነው የሕይወት አቅጣጫ በየእለቱ መዋጮ የሚያደርጉትን ሁኔታዎች በተለያዩ መልኩ ከፋፍለን ማየት እንችላለን፡፡ ከዚህ በታች ያሰፈርኳቸው ሃሳቦች አንዱ የእይታ አቅጣጫ ሊሆን ይችላል፡፡

1. ለሰዎች የምትሰጠው ምላሽ

በየእለቱ ሰዎች በተለያየ መልኩ ወደአንተ ይቀርባሉ፡፡ የተለያዩ አመለካከቶችን ያንጸባርቃሉ፡፡ በየእለቱ ሰዎች የተለያዩ ስሜቶችን የሚያነሳሱ ሁኔታዎችን ይዘውልህ ወይም ይዘውብህ ይመጣሉ፡፡ እነዚህን የሰዎች ሁኔታ በሚገባ የመያዝን ሁኔታ አስበህበት ትክክለኛውን ምርጫ ካልመረጥክ በአጠቃላይ የሕይወት አቅጣጫህ ላይ ተጽእኖ ማስከተሉ አይቀርም፡፡

2. ለአስቸጋሪ ገጠመኞች የምትሰጠው ምላሽ

በየእለቱ የማትጠብቃቸው ገጠመኞች ወደ አንተ ይመጣሉ፡፡ አንዳንዶቹ መልካም ገጠመኞች ሲሆኑ፣ ሌሎቸ ደግሞ ደስ የማያሰኙ ገጠመኞች ናቸው፡፡ ለእነዚህ ገጠመኞች የምትሰጠውን ምላሽ በሚገባ አስበህ ትክክለኛ ውሳኔ በመወሰን ካልተራመድክ በሕይወትህ አቅጣጫ ላይ ጫና ያደርጋል፡፡ “አንድ እድል ወይም ችግር በሰው ውስጥ አዲስ ነገር አይጨምርም፣ ሰው ውስጥ ያለውን ነው የሚያወጣው” ይባላል፡፡ አስታውስ፣ ለየቀን ገጠመኞች የሚኖርህን ምላሽ የመምረጥ መብት አለህ፤ ምርጫህ ደግሞ ወሳኝ ነው፡፡

3. ለስሜቶችህ የምትሰጠው ምላሽ

ከስሜት ውጪ ውለህም ሆነ አድረህ አታውቅም፡፡ አሁን እንኳን ይህንን ጽሑፍ እያነበብክ ባለበት ሰዓት አንድ ስሜት በውስጥህ እንዳለ እሙን ነው፡፡ ይህ ስሜት ጥሩ ወይም መጥፎ “ሙድ” ውስጥ ይከትሃል፡፡ ይህ ስሜት እንዲሁ አልመጣም፡፡ በዚህ መልኩ በእለቱ የስሜት ውጣ ውረድና ተጋድሎ አለብህ፡፡ ለእነዚህ ስህተቶችህ የምትሰጣቸው ምላሾች የወደፊትህን ይወስናሉ፡፡

4. ለስኬት የምትሰጠው ምላሽ

አንዳንድ ሰዎች ስኬትን እንደ እድል ይቆጥሩታል፡፡ ሌሎች ደግሞ ስኬትን መልካም ባህሪንና ጠንክሮ መስራትን ተከትሎ የሚመጣ ነገር እንደሆነ ያስባሉ፡፡ ይህንንም አመንክ ያንን፣ በሕይወትህ ነገሮች ሲሰምሩና ሲሳኩ የምትሰጠው ምላሽ ለወደፊትህ መዋጮ አለው፡፡ በጦርነቱና በፍልሚያው መካከል እንዳለው ልዩነት እንደማለት ነው፡፡ ጦርነቱ የዋናው ዓላማህ ምሳሌ ነው፤ ፍልሚያው ደግሞ በየእለቱ የምትኖረው ኑሮና ትግል፡፡ አንድ ቀን ስኬት ስላገኘህ (ፍልሚያን ስላሸነፍክ) ዋናው ዓላማህ የደረስክ (ጦርነቱን በድል ያጠናቀክ) መስሎህና ተኩራርተህ ታቆም ይሆን?

(“ምርጫና ውሳኔ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተወሰደ)


ጸሐይንና ጨረቃን አታነጻጽሩ!

የእናንተን ሕይወት ከሌላ ሰው ሕይወት ጋር በፍጹም አታነጻጽሩ፡፡ በጸሐይና በጨረቃ መካከል ምንም አይነት ንጽጽር ሊደረግ አይችልም፡፡ ሁለቱም በየራሳቸው ወቅት ነው የሚያበሩት፡፡

እናንተም እንዲሁ ናችሁ፡፡ ሌላው ሰው በራሱ ወቅት እንደሚያበራ ሁሉ፣ እናንተም በራሳችሁ ወቅት ታበራላችሁ፡፡












👉ምንም አይነት ከፍታ ላይ ያለን ቢሆንም ፣ ለምንወደውና ለምንፈልገው ነገር ግን ፤ ዝቅ ማለታችን አይቀርም !!!








ለስኬታማ ህይወት ልብህ እነዚህ አራት ነገሮች  ሊኖሩት ይገባል፦

1. አመስጋኝ ልብ🙏 ፦ የተሻለ ለማግኛት የሚጥር እና ባለው ነገር ፈጣሪውን የሚያመስገን፤ ትንሽ ነገሮች ውስጥ ያለው ዋጋ የሚያውቅ የሚረዳ፤ ሁሉም በጊዜው እንደሚሆን ጠንቅቆ የሚያውቅ፤ ባጣው ነገር ልቡን ከሚያመው ባለይ በቀረው ነገር የሚደሰት ነው። መማር የማያቆም ልብ አለው።

2. ይቅር የሚል ልብ 😍፦ ትላንትናው ላይ በሆነበት ነገር ቂም ያልያዘ እና ልቡን ዝግ ያላደረገ። በተቻለው መጠን እነዚያ ሰዎች ሰው እንደሆነ የሚገነዘብ ነው። ይሄ ማለቴ ሰው ስህተት ይሰራል ያንን ደግሞ መሻር የማይችለው የህይወት እዉነት እንደሆነ ጠንቅቆ የሚያውቅ። ስለዚህ ይቅር እያለ፤ ይቅርታ እያጠየቀ፤ ከትላንት ስህተት በመሻል የዛሬው ህይወት የሚመራ ነው። ነገ በመነፈቅ ያልተጠናወዘ፤ ትላንት በማሰብ ኖሮ እኮ ትላንት ቀረ የማይል፤ ህይወት አሁን ያለው ነገር በጣም ወሳኝ እንደሆነ በማሰብ ያንን በማጣጣም የሚኖር ነው።

3. ትግስተኛ የሆነ ልብ🫶 ፦ ትግስት እንደ ኮሶ የምትመር እንደ ወይን ጣፈጭ የሆነ ውጤት የምትሰጥ መሆኖን ጠንቅቆ የተረዳ። ነገሮች በጉልበት ከመጣል ይልቅ በትግስት እና በትጋት እንደሚያሸነፍ የሚያውቅ ሰው ነው።

4. የማይሰብር ቅስም ያለው🫀፦  መሞከር የማያቆም፤ ከትላንትናው ስህተት ተምሮ ለዛሬው ስራ የተሻለ ለመሞከር የሚጥር። ነቀፋ እና ትችትን የሚቀበል፤ገንቢ የሆኑ ተግሳፅዎች የሚቀበል፤ ከስድብ ውስጥ ትምህርት የሚወስድ ፤ በደገፊዎች ሙቀት ምን ማድረግ እንዳለበት የማይረሰ፤ አይኑን ህልሙና ግቡ ላይ የሚያደርግ ነው። በተቺዎቹ ስድብ እና ያልተገባ ቃላት ለራሱ ያለው ቦታ እንዳንቀንስ ንግግራቸው ወደ፥ ውስጥ የማያስገባ። ጠንከር አስተያያት የማድመጥ እና የመቀበል አቅም ያለው።



Показано 20 последних публикаций.

237

подписчиков
Статистика канала