Dr. Mehret Debebe:
“እምቢ” ማለት ለምን ያስቸግረናል?
አንዴ ያለፈ ጊዜ ለዘለአለም ላይመለስና ዳግም እድል ላይሰጥ ሄዷል፡፡ ጊዜአችንን በሚገባ ለመጠቀም ከሚያስችሉን ጥበቦች መካከል “እሺ” በምንለውና “እምቢ” በምንለው ነገር መካከል መለየት አንጋፋው ነው፡፡ አንዳንዴ ግን ለሁሉም ነገር “እሺ” ወደ ማለት የመገደድ ሕይወት ውስጥ ስንገባ ራሳችንን እናገኘዋለን፡፡ ውጤቱም ከአላማችንና ከፍላጎታችን ውጪ በሆኑ ነገሮች ስንባክን ጊዜን ማባከን ነው፡፡ ይህ የሚሆነው ለምንድን ነው?
ሁሉን ሰው የመርዳ ዝንባሌ፡- አንዳንድ ሰዎች እርዳታ የጠየቃቸውን ሰው ሁሉ መርዳት እንዳለባቸው ይሰማቸዋል፡፡
ክፉ መስሎ የመታየት ፍርሃት፡- የአንዳንድ ሰዎች እምቢ ማለት ያለመቻል ምንጩ “ሰዎች ክፉ ነው ብለው ያስቡኛል” የሚል መሰረት የለሽ ፍርሃት ነው፡፡
ከቡድን የመገለል ፍርሃት፡- “የቡድን መንፈስ” ከባድ የሆነ በሰዎች ላይ የመገደድን ስሜት የሚያመጣ ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ሰው በዙሪያው ከሚገኙት ወዳጆቹ መለየትን የሚፈራ ከሆነ የቡድኑ አባላት ለሚያቀርቡለት ሃሳብ ሁሉ ወደመስማማት ዝንባሌ ሊያመራ ይችላል፡፡
ግጭትን ፍርሃት፡- አንዳንድ ሰዎች የጠየቁንን ነገር በሙሉ ፈቃደኝነት ተስማምተን ካልተገበርን የመቆጣትና የመናደድ ባህሪ ስላላቸው ግዳጅ ውስጥ ይከቱናል፡፡
እድል ያመልጠኛል የሚል ፍርሃት፡- ምናልባት ለተጠየከው ነገር ሁሉ በእሺታ የምትስማማው አንድ እድል ያመልጠኛል ብለህ የምትሰጋ ሰው ስለሆንክ ይሆናል፡፡ ይህኛው ሰው ዛሬ ለጠየቀኝ ጥያቄ እምቢ ካልኩት ነገ ከእሱ ማግኘት የምፈልገውን ለማግኘት አልችልም የሚል ጫና እንደ ማለት ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች “እምቢ” የሚባልን መልስ መስማት አይፈልጉም፡፡ ስለዚህ፣ የሚችሉትን መንገድ ተጠቅመው የእነርሱን ሃሳብ እንድታስፈጽም ጫና ያሳድሩብሃል፡፡ ከዚህ በታች የምንመለከተው እንደዚህ ያሉ ሰዎችን እንዴት እንደምንለያቸውና በምን መልክ ልንቀርባቸው እንደምንችል ነው፡፡
• “ሸንጋዮች” - አንድ አንድ ሰዎች እንድታደርግላቸው የሚፈልጉትን ነገር ለማስደረግ ወይም ደግሞ እንድትሄድላቸው ወደሚፈልጉት አቅጣጫ ለመውሰድ ብዙ የማሞካሻ ቃላትን ሊደረድሩልህ ይችላሉ፡፡
• “ወቃሾች” - አንዳንድ ሰዎች ለሌላው ሰው ሁሉ ጊዜ ሲኖርህ ለእነርሱ ብቻ ጊዜ እንደሌለህና ከአንተ ብዙ ጠብቀው የጠበቁትን ስላላገኙ እንዳዘኑ ይነግሩህና በጥፋተኝነት ስሜት ከመቱህ በኋላ ስለተወቀስህ ሃሳባቸውን እንድትፈጽም ግፊት ያደርጉብሃል፡፡
• “አደናቃፊዎች” - አንዳንድ ሰዎች፣ “ለዛሬ ብቻ ይህንን ብታደርግ ምን ትሆናለህ” በሚል ቃል ካወጣኸው እቅድና መስመር እንድትወጣና ወደ እነርሱ ሃሳብ ዘንበል እድትል በመጫን ከመንገድህ ያደናቅፉሃል፡፡
• “ነጭናጮች” - አንዳንድ ሰዎች ሁል ጊዜ ለሰው የሚደርሱና የሰው ነገር ግድ የሚላቸው እነሱ ብቻ እንሆኑና አንተም ሆንክ ሌላው ሰው ለእነሱ ግድ እንደሌላችሁ በመነጫነጭ ከዚያ ንጭንጫቸው ለመዳን ስትል የመገደድ ስሜት እንዲሰማህ ያደርጉሃል፡፡
• “ጉልበተኞች” - አንዳንድ ሰዎች በአጭሩ ጉልበተኞች ናቸው፡፡ ዛቻን፣ ቁጣንና የማስፈራራትን ቃላት በመጠቀም ሊያጨናንቁህና የሚሉትን ነገር አድርገህላቸው ከዛቻቸው እፎይ እንድትል መንገዱን ሊያጠቡብህ ይሞክራሉ፡፡
መሰረታዊ እይታዎች
• ላላመንክበት ነገር እሺ ማለት የለብህም፡፡ ይህንን አስታውስ፣ አንድን ነገር ከልብህ ካላመንክበት ከውጪ በመጣብህ ግፊት ምክንያት ብቻ ያንን ነገር ማድረግ የለብህም፡፡
• ላላመንክበት ነገር እምቢ ማለትን ስትለምድ ራስህን ማስከበር እንደምት ጀምር አትዘንጋ፡፡ ሰዎች የሚያከብሩህ ራስህን ስታከብር ነው፡፡ ራስህን የማክበርህ አንዱ ምልክት ደግሞ ካመንክበት ነገር አንጻር የመኖር ሁኔታ ነው፡፡
• እርግጠኛ ላልሆንክበት ነገር ጊዜን መውሰድ ልመድ፡፡ ሰው ሁሉ ለሚጠይቅህ ጥያቄ እዚያው መልስ መስጠት የለብህም፡፡ ውስጥህ እርግጠኛ ላልሆነበት ነገር በቀጠሮ ማለፍን ልመድ፡፡
• የውስጥ ስሜትህን አድምጥ፡፡ ለአንድ ነገር እሺ ካልክ በኋላ በውስጥህ ግን የመገደድና የመጨቆን ስሜት ከተሰማህ፣ ቀድሞውኑ እምቢ ማለት እንደነበረብህ አስብና ከዚያ ልምምድ ተማር፡፡
• ኃይለ-ቃልን አስወግድ፡፡ ላላመንክበት ነገር እምቢ ለማለት የግድ ኃይለ-ቃል መጠቀም ወይም ክፉ መሆን የለብህም፡፡ ቀላል አቀራረብን መልመድና ከሰጠኸው ምላሽ ላለመወላወል መወሰን አለብህ፡፡
• “የሚያልቅ” ምክንያት አትስጥ፡፡ አንድን ነገር ላለማድረግ ስትፈልግ፣ “አሁን አሞኛል” ካልክ ሰውየው ነገ እስኪሻልህ ጠብቆ ይመለሳል፡፡ ይህ አላቂ ምክንያት ይባላል፡፡ በተቃራኒው ግን ነገሩን ለማድረግ ፍላጎት እንደሌለህ በጥበብ ከመለስክለት ጉዳዩ እዚያ ላይ ያበቃል፡፡
• የሚቀበልህና የሚወድህ ሰው ለጠየቀው ጥያቄ እሺም አልከው እምቢ አንተን ከመቀበል እንደማይከለክለው እወቅ፡፡ ይህንን ማወቅ ተቀባይነትን ላለማጣት ለመጣው ጥያቄ ሁሉ እሺ ከማለት ይጠብቅሃል፡፡
የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ
(ለበለጠ እውቀት መጽሐፉን በገበያ ላይ ያገኙታል)
== በቅንነት ሼር በማድረግ አዳርሱ == @DrMihretDebebe
@words19