✍
ልብህ ሲወጣጠር ሲልህ ኩራት ኩራት
ጡንቻህ ሲፈረጥም ሲያሳጣህ ስርዓት
ማንነትህ ዐይተህ ድክመትህ እንድታውቅ
ሆስፒታል ግባና ህመምተኛን ጠይቅ።
ወይ ሀብትህ ቀንሶ ጭንቀት ከወጠረህ
በምንህ ልትኖር ነው ብሎ ከጠየቀህ
የጤንነትህ ሀብት ደረጃው እንድታውቅ
ሆስፒታል ግባና ህመምተኛን ጠይቅ።
ስራ ሲቀዘቅዝ አየሩ ሲጠፋ
ኢኮኖሚው ንሮ ኑሮውም ቢከፋ
ሰላም እንድታገኝ ልብህ እንዲረጋ
ጤንነት እስካለህ ምንም እንዳትሰጋ
ወደ ላይ ታች ሳትል ብዙንም ሳትርቅ
ሆስፒታል ግባና ህመምተኛን ጠይቅ።
ቀብር መዘየር ልብ እንደ ሚያለሰልስ ሁሉ ወደ ሆስፒታል ገብተህ ህመምተኞችን ስትዘየርና ያሉበትን ሁኔታ ስትመለከት የሰው ልጅ ማለት እንዲሁ በአላህ ዕዝነትና ጥበቃ የሚኖር እንጅ ምንም አቅም የሌለው ሸክላ እንደ ኾነ ትረዳለህ። ያለህበት የዓፊያ ፀጋም ምን ያህል ትልቅ እንደ ሆነም ትገነዘባለህ።
🤲ለታመሙት ሁሉ ዓፊያ ይስጣቸው🤲
https://t.me/wrbazer
https://t.me/hamdquante href='' rel='nofollow'>