✏️ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ደብረ ታቦርስ ?
በምዕምዕናን ዘንድ ቡሄ ተብሎም ይታወቃል። ቡሄ ማለት ብርሃኑ የደመቀ የጎላ ማለት ነው ይህም ስያሜ በደብረ ታቦር ጌታችንን ብርሃነ መለኮት ጋር መጋለጥ ጋር የተያያዘ ስያሜ ነው።
ደብረ ታቦር ማለት የታቦር ታራራ ማለት ነው ተራራው ከገሊላ ባህር በስተምሥራቃዊ በደቡብ በኩል ይገኛል ፤ መሳ 4-6 14 ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል
ጌታችን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ደቀ መዛሙርቱ በጠየቀችው ጊዜ አንዳንዶቹ መጥምቁ ዮሐንስ ሌሎች ኤልያስ ነው ሌሎችም ሙሴ ወይም ከነብያት አንዱ ነው ብለውት ነብር
እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ሲላቸው ቅዱስ ጰጥሮስ አንተ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ መልሶለታል ይህ በሆነ በስድስተኛው ቀን ከሐዋርያት መካከል ሦስቱን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወጣ ብዋላ ብርሀነ መለኮቱን ገለጣቸው ሙሴን ከመቃብር ኤልያስን ከብሄረ ሕያዋን ጠርቶ ያመጣቸው ሙሴ ብርሃንን አሳየኝ ብሎት ነብር (ዘጸ 33፦17-23)
ስለ እርሱም ማንነት ግራ ለተጋቡ ጰጥሮስ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት እንደተናገረው የህያወ እግዚአብሔር ልጅ እንጂ ከነብያት አንዱ አለመሆኑና የዘለዓለም ሰዎች በዚህ እንዳይሰናከሉ በተግባር አስተማሯችዋል።
ከዚያም ደመና ጋረዳቸው አብ ከሰማይ የምወደው ልጄ ይህ ነውና እርሱን ስሙት ሲል መሰከረ (ማቴ 17፤2)
🥖 መልካም የ ቡሄ በዓል 🥖