ዛር ያለባት ሃገር ማጉራት የለመደች፣
በነጋ በጠባ "ደም አምጡ" ትላለች።
ይሄን ያየ ልጇም
ተነድፎ በክፋት ታሞ በከንቱነት፣
ይገብርላታል
የመንትያውን ነፍስ የወንድሙን አንገት።
ያው... አንካሳ ዘመን
ያው... ጉድፋም ትውልድ
ፍቅሩ የይስሙላ አካሂያዱ የግድ፣
ነውር ነው አያውቅም
በሃዘኑ ሲያሾፍ በሞቱ ሲቀልድ።
ወ....ግ...ድ!!!
ብራ ይሁን እና
የምስራቃችን በር የአድማሱ ገመገም፣
በቃችሁ ይበለን
በሃገሬ መሬት
በሃበሻ ሰማይ ላይ ሞት አይደጋገም።
መተከል🌑🌒😢😢 ኧረ በቃችሁ በለን የሰዉ ልጅ አንገት ከዶሮ አንገት የቀለለባት ሀገር...ከርመን መርዶ ብቻ...በሰዉ ደም ኪሱን የሚያደልብ..በሰዉ ደም የሚያተርፍ...በሰዉ ደም ኪሳራዉን የሚያሰላ ስግብግብ ተከበን ነፍሳችን ተጨማዳ ተኮማትራ አለቀች።....ግን ለምን...? ካልገደሉ ህይወት የለም...? እኛ ሀበሾች ግን መች ነዉ እንዲህ ሰይጣንን ማስናቅ የጀመርነዉ...?
የሚገርመኝ አሁንምኮ እንደሰኩራለን...አሁንምኮ ኢትዮጵያዬ የፍቅር ሀገር እንላለን...የቱ ጋር ነዉ ፍቅራችን...አብሮህ አንድ ማእድ ላይ የተመገበዉን ሰዉ..አንተ ትብስ ተባብለህ ኑረህ ቀን ሲመጣ ለማትረባ ክፍያ ተቀይረህበት ወንድምህን አጋድመህ እያረድከዉ ነዉ ፍቅር..? ቤተሰቡን መበተንህ ነዉ ፍቅር...ሚስቱን እና አንድያ ልጁን ደፍረህ ነዉ ፍቅር..? እዉነት በእራሳችን እንፈር ጭራቆች ሁነናል....ዲያቢሎስ ነዉ መሪያቸዉ የምንላቸዉ እነዛ ነጮች እንኳን የሰዉን ደም እንደኛ አያፈሱምኮ...አሁን ላይ ከእኛ የተሻለ ዲያቢሎስ የትም የለም...ዛር እና ዉቃቢያችን ከረም ይልና ደም እፈልጋለሁ ይለናል ከርመን እንገላለን ደም እንገብራለን።..
ሃሳቡ የተመቸው ቤተሰብ ይሁነን
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥