Re....
ሾልኮ ቀለበቱ ፤ ከእጄ የወደቀው
ወሰዳት ብላችሁ ፤ ስትነግሩኝ እኮ ነው
እንዴት ትሞታለች…? ቤቴን ማን ያድምቀው…?
እንዲህ ይጨክናል… ሰው በሚወደው ሰው…?
ግራ ጎኔ ሞልቶ…ክፍተቴ ተከድኖ… ደስታዬ ሳከብር
አምላክ ምን ነክቶት ነው…? ፤ እንዴት ይቀጣኛል
…ከሞት ጋር በማበር፡፡
ይሁን እስቲ ተውት ፤ ሽንፈቴን ልዋጠው
በእግዜር እጅ ሲገባ ፤ ማንም ደካማ ነው
ግን ስታበጃጇት...
ሳጥን አትስሩላት ፤ ለእሷ አይገባትም
ከፈኗም ጨርቅ አይሁን ፤ አዎ አይመጥናትም
ይልቅ ቶሎ በሉ ፤ ቆዳዬን ግፈፉት
በዛ ጠቅልላችሁ ፤ በድኗን ከፍኑት
ከዛም ጉድጓድ ሳይሆን ፤ ልቤ ውስጥ ቅበሯት
አፈር እንዳይነካት ፤ ምስጡ እንዳይበላት
……….. እዛ ነው ሚሻላት
የራሷ ነኝ እኔ ….አካሌም ቤቷ ነው…..
ልቤ ዉስጥ አስተኟት እንዳይቀዘቅዛት።
የግጥም ፍላጎት ካላችሁ ቤተሰብ ሁኑን
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥
ሾልኮ ቀለበቱ ፤ ከእጄ የወደቀው
ወሰዳት ብላችሁ ፤ ስትነግሩኝ እኮ ነው
እንዴት ትሞታለች…? ቤቴን ማን ያድምቀው…?
እንዲህ ይጨክናል… ሰው በሚወደው ሰው…?
ግራ ጎኔ ሞልቶ…ክፍተቴ ተከድኖ… ደስታዬ ሳከብር
አምላክ ምን ነክቶት ነው…? ፤ እንዴት ይቀጣኛል
…ከሞት ጋር በማበር፡፡
ይሁን እስቲ ተውት ፤ ሽንፈቴን ልዋጠው
በእግዜር እጅ ሲገባ ፤ ማንም ደካማ ነው
ግን ስታበጃጇት...
ሳጥን አትስሩላት ፤ ለእሷ አይገባትም
ከፈኗም ጨርቅ አይሁን ፤ አዎ አይመጥናትም
ይልቅ ቶሎ በሉ ፤ ቆዳዬን ግፈፉት
በዛ ጠቅልላችሁ ፤ በድኗን ከፍኑት
ከዛም ጉድጓድ ሳይሆን ፤ ልቤ ውስጥ ቅበሯት
አፈር እንዳይነካት ፤ ምስጡ እንዳይበላት
……….. እዛ ነው ሚሻላት
የራሷ ነኝ እኔ ….አካሌም ቤቷ ነው…..
ልቤ ዉስጥ አስተኟት እንዳይቀዘቅዛት።
የግጥም ፍላጎት ካላችሁ ቤተሰብ ሁኑን
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥