እነሆ… ተጀምሯል‼
==============
(የመረጣችሁበትን ስክሪን ሹት ኮመንት ላይ ላኩት፤ እናጠለቅልቀው፤ ዘመቻውን እንቀላቀል!)
||
✍ 10 ሚሊዮን ብር የሚያስሸልመው ውድድር ድምፅ መስጫው መንገድ ታውቋል። ትናንት በዚህ ፖስት (
https://t.me/MuradTadesse/38825) በነገርኳችሁ መሠረት የአሚን ጠቅላላ ሆስፒታልን ባለቤት ዶ/ር ሙሐመድ ሽኩርን እንመርጣለን። እውነት ለመናገር ዶ/ር ሙሐመድ ሽኩር ይህንን ውድድር ካሸነፈ ሙሉ አስር ሚሊዮኑን ብር ለእናቶች ማዋለጃና ለጨቅላ ህፃናት ሕክምና አውላለሁ ባይል ኖሮ የምመርጣቸው ሌሎች ተወዳዳሪዎች ነበሩ።
ምክንያቱም ብሩ ወደ ኪሱ የሚገባ ቢሆን ያለውን በረካህ ያድርግለት እንጂ በአንፃሩ ለሌሎች ወጣቶች ቢሆን ይሻላል። ግን ለእናቶችና ለህፃናት መታከሚያ ሙሉውን አውላለሁ ብሎ ቃል ስለገባና እኔም በተጨባጭ እንኳን የተሸለመውን ሠርቶ ያገኘውንም ለሚስኪኖች ድጋፍ ሲያውል ስለታዘብኩ፤ በእናትና በህፃናት አይጨከንም ብዬ እነርሱን ብር አውጥቼ መርዳት ባልችል እንኳ ዶ/ር ሙሐመድን በመምረጥ መርዳት እንደምችል ስላወቅኩ ወደ 9355 SMS ላይ BIW03 ብዬ በመላክ መርጨዋለሁ።
እናንተም ለእናትና ህፃናት አትጨክኑም ብዬ ትመርጡት ዘንድ ጋበዝኳችሁ።
ስትመርጡ በፓጄጅ ስለማይቻል ቢያንስ 3 ብር ባላንስ ይኑረው ስልካችሁ።
ከዛ ሚሴጅ ላይ ግቡና 9355 ላይ BIW03 ብላችሁ ጻፉና ላኩት።
ባይሆን BIW በሚለውና 03 በሚለው መካከል ስፔስ (ክፍት ቦታ) መኖር የለበትም። BIW የሚለው በsmall letter biw ሳይሆን ሁሉም በካፒታል ሌተር BIW ነው። በትክክል መላካችሁን የምታረጋግጡት፤ BIW03 የሚለውን ወደ 9355 ከላካችሁት በኋላ «You have voted for ( Dr Mohamed shikur ). Thank you for your participation. Abbay TV 'Ethiopia's Best'» የሚል መልዕክት ወዳውኑ ይደርሳችኋል። ከአንድ በላይ ሲም ካላችሁ፣ ወይም መደጋገም ከፈለጋችሁ፣ ወይም ባላችሁ ቤተሰብ ስልክ ሁሉ መላክ ከፈለጋችሁ፣ ካርድ ለሌላቸው እየሞላችሁ … ምረጡት። ድምፃችን እንዳይበታተንና አንድ ቦታ ላይ አድምተን ድምፅ እንድንሰጥ ወጥሩ ቅመሞች።
መልዕክቱን በተለያዩ ገፆችና ግሩፖች አሰራጩት።
መታከሚያ ያጡ ሚስኪን እናቶችና ህፃናት ያሸንፋሉ፤ ኢንሻ አላህ! ያው የኔ ገፅ ቅመሞች በንቃትና በእንዲህ አይነት የኸይር ተሳትፎ አትታሙም። እንኳን በዚህች በቀላሏ ከኪሳችሁም ሚሊዮኖችን አዋጥታችሁ በተደጋጋሚ ለሚስኪኖች ሰድቃችሁ አሳይታችኋል። አላህ ይቀበላችሁ!
||
t.me/MuradTadesse